Tuesday, January 9, 2018

የመጀመርያው አፍሪካዊ ጄት አብራሪው ስንብት







በኢትዮጵያ የአቪዬሽን ታሪክ ገናና ስም የነበራቸው፣ በአፍሪካ የመጀመርያው ቦይንግ ጄት 720ቢ አውሮፕላን አብራሪነት ቀዳሚ የነበሩት ካፒቴን ዓለማየሁ አበበ (1916-2010) ሥርዓተ ቀብር ቅዳሜ ታኅሣሥ 28 ቀን 2010 ዓ.ም. በጴጥሮስ ወጳውሎስ የካቶሊክ መካነ መቃብር ተፈጽሟል፡፡ ከጎን የሚታየው ካርቱን በሠዓሊና የሪፖርተር ካርቱኒስት ኤልያስ አረዳ የተሣለ ሲሆን፣ ሌሎቹ ፎቶዎች ከፋይልና ከሥርዓተ ቀብሩ የተገኙ ናቸው፡፡ አንዱ ካፒቴን ዓለማየሁ (በግራ) በ1957 ዓ.ም. ከረዳታቸው ጋር በበረራ ወቅት የተነሡት ሲሆን፣ ሌሎቹ በለገሃር መድኃኔ ዓለም ቤተ ክርስቲያን ከጸሎተ ፍትሐቱ በኋላ ብፁዕ ካርዲናል አቡነ ብርሃነየሱስ ሐዘንተኛ ቤተሰቦችን ሲያፅናኑ፣ እንዲሁም በጸሎተ ፍትሐቱ የተገኙት ልዑል ራስ መንገሻ ሥዩም (በቀኝ)፣ ልዕልት ሳራ ግዛው፣ ልዑል በዕደማርያም መኰንን (በግራ)፤ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ካፒቴኖች ከመለያ ልብሳቸው ጋር ይታያሉ፡፡
በሔኖክ ያሬድ

No comments:

Post a Comment