በሔኖክ ያሬድ
‹‹መንገድ
ዓይንህ ይፍሰስ አይባልም ደርሶ
የወሰደውን
ሰው ያመጣል መልሶ››
ይህ
መንቶ ግጥም፣ ሐምሌ 9 ቀን 2003 ዓ.ም. ሀገር ፍቅር ቴአትር ከሁለት አሠርት በላይ በካናዳ የሚኖረው ደራሲ አዳም ረታ
ለመጀመርያ ጊዜ ከሥነ ጽሑፍ ቤተሰብ ጋር በተገናኘበት አጋጣሚ በተሠራጨው ካርድ ላይ የተነበበ ነበር፡፡
ደራሲ
አዳም የመጀመርያውን አጭር ልብ ወለድ መድበሉን ‹‹ማህሌት›› በ1981 ዓ.ም. በአዲስ አበባ ካወጣ በኋላ፣ ባሕር ማዶ ተሻግሮ
በኖረበት ካናዳ ሕይወትን እየኖረና እየደረሰ፣ ከ1997 እስከ 2003 ዓ.ም. ድረስ በቅደም ተከተል ድርሰቶቹን ወደ አዲስ
አበባ እየላከ አሳተመ፡፡ ‹‹ግራጫ ቃጭሎች›› (1997) ‹‹አለንጋና ምስር›› (2001)፣ ‹‹እቴሜቴ ሎሚ ሽታ››
(2001)፣ ‹‹ይወስዳል መንገድ ያመጣል መንገድ›› (2003) አስሳትሞ ከአንባብያን ዘንድ እንዲደርስ አስደረገ፡፡
በእቴሜቴ
ሎሚ ሽታ መግቢያ ላይ፣ ‹‹አዳም ወደረሳነውና ወደምናስታውሰው፣ ወደአከበርነውና ወደናቅነው፣ ወደሸሸነውና ወደምንቀርበው፣
ወደፊራነውና ወደ ደፈርነው ዓለም ይወስደናል፡፡›› ተብሎ ተጽፏልና፤ እስቲ በግንባር ተገኝተህ ከጥበቡ ወዳጆች ጋር ተገናኝ ብሎ
ከመጀመርያው ድርሰቱ ‹‹ማህሌት›› ስሙን የነሣው ማህሌት አሳታሚ ‹‹አዳም ሆይ! የት ነው ያለኸው?›› ብሎ መድረኩን
አዘጋጀለት፡፡ ድዮስጶራው አዳምም ከመድረኩ ተሰየመበት፡፡
በኢትዮጵያ
ባሕረ ሐሳብ መሠረት ሰኔ 26 ቀን 2003 ዓ.ም. የገባው የክረምት ወቅት፣ በቅዱስ ያሬድ ድርሰት (ድጓ) ውስጥ ‹‹ደምፀ
እገሪሁ ለዝናም›› የሚል ኃይለ ቃል ይገኝበታል፡፡ ‹‹የዝናብ ኮቴ ተሰማ›› የሚል ፍች አለው፡፡ የሪፖርተሩ ዜናዊ ይኸንኑ
ደምፀ እገሪሁ ለአዳም (የአዳም ኮቴ ተሰማ፤ ድምፁም ተሰማ) ብሎ ቀጥፎ አቀረበው፡፡ ክረምትና አዳም አንድ ላይ ደረሱም
አለው፡፡
በመድረኩ
ስለ አዳም ረታ የሥነ ጽሑፍ ፈለግ የአተራረክ ስልት ጠቀስ ለውይይት መነሻ ጥናት ያቀረቡ ሙያተኞች ነበሩበት፡፡ በሁለተኛው
ክፍል መሰናዶ ታዳሚዎች ለደራሲ አዳም ካቀረቡለት ጥያቄዎች መካከል ምላሽ ከሰጠባቸው አንኳር አንኳሩን እንዲህ ተሰድሯል፡፡
(ሀ) ስለ አደራረሱ
መጀመርያ
የምረዳው ነገር በምድር ላይ ፍጹማዊ የለም፡፡ ሰው ሆነን ተፈጥረን ፍጹም አይደለንም፡፡ በአካል የምሥላቸው ገፀ ባሕርያት ላይ
ብዙ ጊዜ ሙሉ ለሙሉ ማለትም፣ ፊቷን አሳይህ እንደሆነ፣ ዓይኗን ብቻ ነው እምነግርህ፡፡ የቀረውን በራስህ ምኞት ነው
እምትሞላው፡፡ ድርሰት ስጽፍ እንደግል ታሪክ ልወስዳቸው አልችልም፡፡ ግን በምጽፍበት ወቅት በዚያን ጊዜ ያለኝ ሙድ ምናልባት
የምኖርበት ከባቢ የምንቀሳቀስበት ሁኔታ፣ አመራረጤን ሊቆጣጠር ይችላል፡፡ ግን የግል ታሪኬን አይነካም፡፡ ድርሰቱን ከሠራሁ
በኋላ የራሴ የሚመስል ነገር ካለ ኤዲት አደርጋለሁ፡፡
(ሁ) ስለ ነፋስ መውጫና ስለስሙ
ነፋስ
መውጫ ነበርኩ፡፡ ቃሉን ስሰማ ስሙ ደስ ይለኛል፡፡ ነፋስ መውጫ ደረስኩ፡፡ መዝገቡን እንደ ነፋስ ወሰድኩት፣ ከዚያ በኋላ ሌላ
ቦታ ያየሁትን ነገር አስገብቻለሁ፡፡ የተወለድኩት ግን በአዲስ አበባ ነው፡፡
ተወልጄ
የተሰጠኝ ስም አዳሙ ይባላል፡፡ ትንሽ ኃይለኛ ስለመሰለኝ ለስለስ ለማድረግ አዳም አልኩት፡፡
(ሂ) ስለ አርትዖት
ከጻፍኩ
በኋላ አስቀምጠዋለሁ፡፡ አላስታውስም፡፡ ምናልባት ኤዲት ሳደርግ አንዳንዴ ነገሮችን ልለውጥ እችላለሁ፡፡ የምለውጣቸው ነገሮች
ግን ክፉ አይደሉም፡፡ አንዳንዴ የራሴን ድርሰት ስከልስ የሆነ ክፍተት አያለሁ፡፡ ወይም መሞላት የሚገባው ግን የተዘለለ ክፍተተ
አለ፡፡ የቋንቋ ደካማነት ሊሆን ይችላል፡፡ የክሥተቶች ሰፊ መሆን ሊሆን ይችላል፡፡ ስለዚህ የራሴን ድርሰት ሳይ ለመግለጽ
የምፈልገውን ነገር ምን ያህል ገለጽኩ? ብዬ ስጠይቅ አለመግለጼን እረዳለሁ፡፡ የቀሰቀሱኝ ነገሮች ምንም ያህል ቢቀሰቅሱኝም፣
ቢያጽፉኝም ብቁ አይደሉም፡፡ አንድ ነገር ኢንስፓየር ያደርገኛል [ያነቃቃኛል] ወይስ አያደርገኝም የሚለውን የማውቀው
ስሠራው ብቻ ነው፡፡
(ሃ) ትውስታና ሥዕል
ወደ
ውጭ አገር ስሔድ ትውስታዬን እዚህ ትቼ አልሔድኩም፡፡ አብሮኝ ነው የሔደው፡፡ ዱሮ ሲደረጉ የነበሩ ነገሮችን ስጽፍ ለማስታወስ
እወዳለሁ፡፡ እጽፋለሁ፤ ነገር ግን አስቀምጠዋለሁ፡፡ አሳታሚ መኖሩን የማውቀው ሲወራ ነው፡፡ በጽሑፌ ላይ ሥዕል የምጠቀመው
ምክንያት ሲኖረኝ ብቻ ነው፡፡ በዚህም የሚጎዳ ሰው አይኖርም፡፡ ድርሰቴን ስጽፍ እንደ ‹‹እቴ እሜቴ የሎሚ ሽታ›› ጠንካራ
ግንኙነት እንዲኖራቸው እፈልጋለሁ፡፡
(ሄ) ስለ ተጽዕኖ
እኔ
ራሴ ደራሲ ነኝ፡፡ ከዚህ አኳያ መጻፍ ነው እንጂ ማን ተጽዕኖ አደረገብኝ የሚለውን ጭርሱኑ አላስብም፡፡ ሌላ ደራሲ አላይም፤
ግን አነበዋለሁ፡፡ ከዚያም እተወዋለሁ፡፡ ብዙ ጊዜ ያጋጠመኝ ጥያቄም የማን ተጽዕኖ አለብህ? የሚል ነው፡፡ እኔ ስጽፍ
ስለማልፈራ ተጽዕኖ የሚባል ነገር አይኖርም፡፡ ለእኔ ወረቀቴ፣ እርሳሴና እኔ ብቻ ነን፡፡ ዝም ብዬ እየጻፍኩ፣ እየጻፍኩ አሁን
ካለሁበት ደረጃ ደርሻለሁ፡፡
በ1960
ዓ.ም. እማውቀውን አንድ ሰው ከ30 ዓመት በኋላ ሳገኘው ሁሉም ነገር ተለውጧል፡፡ ሰውዬው መላጣ ነው፣ ሽበት አለው ወዘተ.
በአጠቃላይ ሌላ ሰው ሆኗል፡፡ ይህ እንደሚሆን ስለማውቅ ምነው ምን ሆንክ? ብዬ ላልጠይቀው እችላለሁ፡፡ ከዚህ አኳያ ከሕይወት
ወይም ከፍልስፍና ነው የምቀዳው፡፡
(ህ) ስለ አድናቆት
አንብቤ
የወደደኩት ደራሲ ካለ ሁለተኛ ላየው አልፈልግም፡፡ ምናልባት ቀንቼ ይሆናል፡፡ በአሁኑ ጊዜ ያለው ሙከራ ምንድነው ተዋረዶችን
በመጠኑ በአግድሞሽ ለማምጣት መሞከር ነው፡፡ በቅዱስ መጽሐፍ ውስጥ ሁልጊዜ እንደዚህ ነው፡፡ ተዋረድ ስልም በጓደኞች መካከል
ያለው ተዋረድ ነው፡፡ እኩያነት ባላቸው ክሥተቶች ያለ ተዋረድ ነው፡፡ ሁልጊዜ ድርሰት ሲጻፍ አብስትራክት ለሆኑ ሰዎች ቦታ
ይሰጣል፡፡ ገፀ ባሕርያት በጣም ግዙፍ ይሆናሉ፡፡ ቁጭ ብዬ አንድ ዛፍ ማየትና ትልቅ ስብሰባ መሳተፍ እኩል ሕይወት ነው፡፡
ቅጠሉ
ሲንቀሳቀስ ማየት፣ ነፋሱ ሲመጣ መመልከት ለእኔ ሁሉም ዕውቀት ነው፡፡
(ሆ) ስለቀይ ቀለም አጠቃቀሙ
ቀይ
ቀለም የምጠቀመው በቅዱሳት መጻሕፍት እንዳለው አምላክንና ቅዱሳንን ለመግለጽ ሳይሆን ተርታና ተራ ነገሮች ላይ አጽንዖት
ለማሳየት ነው፡፡
ReplyDeleteGreat delivery. Sound arguments. Keep up the good spirit. hotmail sign in
Mortgage brokers and certain lenders can charge different mortgage interest levels depending for the province. mortgage payment calculator canada One of my favourite parts with this career is usually to be capable of provide that same satisfaction to others. mortgage payment calculator
ReplyDelete