ባህላዊ አለባበስ አንድን ግለሰብ ወይም ማኅበረሰብ በቀላሉ ከወዴት እንደሆነ ለማወቅ ያስችላል ለሚለው አገላለጹም ማሳያ ያቀረበው የጎጃም ማኅበረሰብን ነው
19 Apr, 2017
በሪፖርተር አንደከተብነው
የሐበሻ
ቀሚስ ብሂል ከባህል ያጣቀሰ ነው፡፡ ኢትዮጵያውያቱ በየአካባቢያቸው፣ በየአጥቢያቸው ከትውፊታቸው ከሚቀዳው አለባበስ
አንዱ ሀገርኛው ቀሚሳቸው ነው፡፡ ቀሚስ በመዝገበ ቃላዊ ፍችው በሦስት ወገን የተስፋ የሴት ልብስ፤ ልኩ 6 ዘንግ፣
24 ክንድ ነው፡፡
ከአምስት አሠርታት በፊት የኅትመት ብርሃን ያየው የአለቃ ደስታ ተክለ ወልድ ‹‹ዐዲስ ያማርኛ መዝገበ ቃላት›› ቀሚስን በየፈርጁ ይበይነዋል፡፡ በሐር የተጠለፈ፣ የተዘመዘመውን ጥልፍ ቀሚስ ሲለው፤ ጥበብ ያለበትን ደግሞ ጥበብ ቀሚስ ይለዋል፡፡
ቀሚስ ለሴቶች ብቻ የሚውል ቃል አይደለም፡፡ እጀ ሰፊ የቄስ፣ የመነኩሴ ልብስ፣ ረዥም ጥብቆ የሸማ የሐር፣ የዳባ ልብስም ቀሚስ ይባላል፡፡ የበቅሎ፣ የፈረስ ኮርቻ ልብስ፣ የመሶብ ልብስም ቀሚስ ይባላል፡፡
የቀሚስ ገላጭነት
የቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለሥልጣን በጎጃምና በሰሜን ሸዋ የሚገኙ የማይዳሰሱ ባህላዊ ቅርሶችን አስመልክቶ በአንትሮፖሎጂና በፎክሎር ባለሙያዎቹ አስጠንቶ ዓምና ባዘጋጀው ድርሳኑ ውስጥ አንደኛው ትኩረቱ አለባበስ ላይ ነው፡፡
ባህላዊ አለባበስ አንድን ግለሰብ ወይም ማኅበረሰብ በቀላሉ ከወዴት እንደሆነ ለማወቅ ያስችላል ለሚለው አገላለጹም፣ ማሳያ ያቀረበው የጎጃም ማኅበረሰብን ነው፡፡ ለአብነት ያህልም የልጃገረዶችና የሴቶች አለባበስን ከአጊያጌጥ ጋር እንደሚከተለው ገልጾታል፡፡
ቀደም ባሉት ጊዜያት የጎጃም ልጃገረዶች ባህላዊ አለባበስ በተለይም በዓል ሲሆን፣ ለብሰውት የሚወጡት ልብስ ሙሉ በሙሉ የሐበሻ ቀሚስ ነበር፡፡ የሐበሻ ቀሚስ ጉንፍ፣ ሸብሸቦና ጥልፍ ቀሚስ እንዲሁም ፍቅር ቁርጥ የተባለ ነበር፡፡ ፀጉራቸውን ደግሞ ቃሬና ቁንጮ ተላጭተው፣ ጥቁራት ተጠቁረው፣ አልቦና አምባር አጥልቀው፣ ምሪያቸውን ወገባቸው ላይ አስረው፣ ነጠላ ከላይ ጣል አድርገው ነው የሚወጡት፡፡
አሁን ላይ ግን ይህን አለባበስ ሳይሸራረፍ ለብሳ የምትወጣ ልጃገረድ ማግኘት ባይቻልም በተለይ በገጠር አካባቢ የሚኖሩ ልጃገረዶች ባህላዊ ልብሳቸውን ያዘወትራሉ፡፡ በዕለት ተዕለት እንቅስቃሴዎቻቸው የሐበሻ ቀሚሱ ቀስ በቀስ ዘመን አመጣሽ በሆኑ ከብትን ጨርቆች በሚዘጋጁ ልብሶች ቢተካም በበዓላት፣ ቤተ እምነት ሲሄዱና በሌሎች ማኅበራዊ መሰባሰቦች (ሠርግ፣ ዘመድ ጥየቃ፣ ሕዝባዊ ስብሰባዎች….) ላይ አሁንም የሐበሻ ቀሚስ መልበስ የተለመደ ነው፡፡ ለእንግጫ ቆረጣ ካልሆነ ምሪ የምታሰር ልጃገረድ ማግኘት ከባድ ነው፡፡
ሸብሸቦ ቀሚስ
ሸብሸቦ ቀሚስ የተለያዩ ቀለም ካላቸው ጥለቶች ከክርና ከማግ ከዝሃም የሚዘጋጅ፣ ባላገቡ ወጣት ሴቶችና በእናቶች ሊለበስ የሚችል የልብስ ዓይነት ነው፡፡ ይህ ልብስ ልጃገረዶች በሠርጋቸው ላይ ከሚለብሷቸው አንዱ ነው፡፡ ሸብሸቦ የተባለበትም ምክንያት፣ እንደጉንፍ ቀሚስ ልቅ ባለመሆኑና ወገቡ ላይ ገመድ በማስገባት የሚሰፋ ስለሆነ፣ ቀሚሱ ከወገቡ ጀምሮ እስከታች እስከጥለቱ ድረስ የሚሸበሸብ በመሆኑ ነው፡፡
ጉርድ ቀሚስ
ጉርድ ቀሚስ ከጊዜ በኋላ ነባሩን የማኅበረሰቡን ባህል በማሻሻል የተገኘ እንደሆነ ይገመታል፡፡ የተለያዩ ቀለም ካላቸው ጥለቶች፣ ከክርና ከማግ ከዝሃም የሚዘጋጅ ሲሆን፣ ጉርድ የተባለበትም ምክንያት እስከ ወገቡ ድረስ ጉርድ ሆኖ ከወገቡ በታች ልቅ ስለሆነ ነው፡፡ ቀሚሱ ከወገብ ጀምሮ እስከ ታች ጥለቱ ድረስ የሚሸበሸብ በመሆኑ ከሸብሸቦ ቀሚስ ጋር ተመሳሳይነት አለው፡፡ ይህ ልብስ ባላገቡ ወጣት ሴቶችና በእናቶች ደረጃ ሊለበስ የሚችልና ልጃገረዶች በሠርጋቸው ላይ ከሚለብሷቸው የልብስ ዓይነቶች አንዱ ነው፡፡ ጉርድ ቀሚስ ሕፃናትም ይለብሱታል፡፡
ጉንፍ ቀሚስ
የጎጃም ማኅበረሰብን ከሚወክሉና ባህሉን ከሚያንፀባረቁ ሀገረሰባዊ አልባሳት መካከል አንዱ ጉንፍ በመባል የሚታወቀው የቀሚስ ዓይነት ነው፡፡ ጉንፍ ከጥጥ የሚዘጋጅና በአካባቢው ሸማኔዎች የሚሠራ የሴቶች ልብስ ሲሆን፣ በአብዛኛው በተለያዩ በዓላትና ክብረ በዓላት ላይ ይለበሳል፡፡ በተለይ በታቦት ንግሥ፣ በዘመን መለወጫ (ቅዱስ ዮሐንስ)፣ እንዲሁም ጥምቀትን በመሳሰሉ ሃይማኖታዊ ክብረ በዓላት ጊዜ ሴቶች የሚለብሱት ነው፡፡
ጉንፍ ቀሚስ ፍታል እየተባለ መጠራቱ፣ በእጅ የተሠራና የተፈተለ መሆኑን ለማመላከት ነው፡፡ ይህ የልብስ ዓይነት የጎጃም ማኅበረሰብ ከቀደምቱ የወረሰውና የማኅበረሰቡን ባህል፣ ወግ፣ ልማድና አኗኗር መሠረት በማድረግ በአካባቢው ከሚገኝ ጥሬ ዕቃና የመሥሪያ ቁስ በመጠቀም የሚመረት ነው፡፡ ዘመናዊ የልብስ ማምረቻ ከመግባቱ በፊት ተፈጥሮ ጥቅም ላይ የዋለና በማገልገልም ላይ የሚገኝ የልብስ ዓይነት ነው፡፡
ጉንፍ ቀሚስ ባለ ሁለት ዓይነት ሲሆን፣ አንደኛው እጅጌው ጉርድ የሆነ ወይም እጅጌ የሌለው ሲሆን፤ ሁለተኛው ደግሞ በተለምዶ በማኅበረሰቡ አጠራር ባለ ክናድ ወይም ቅጥል በመባል የሚጠራና እጅጌ ያለው ነው፡፡
መቀነት
የጎጃም ማኅበረሰብን ባህል ከሚወክሉና ከሚገልጹ አልባሳት መካከል መቀነት ይገኝበታል፡፡ መቀነት ያገቡ ሴቶች በወገባቸው ላይ የሚታጠቁት ከጥጥ የሚሠራ የልብስ ዓይነት ነው፡፡ ያገቡ ሴቶችን ካላገቡ ሴቶች ለመለየትም ይረዳል፡፡ መቀነት ተቀናቾችን አድምቆና አሳምሮ ለማሳየት፣ የለበሱት ቀሚስ እንዳይዝረከረክ ለመሰብሰብ ልክ እንደ ቦርሳ በመሆን ያገለግላል፡፡ መቀነት የሚባለው የልብስ ዓይነት የመጣው ‹‹የማርያም መቀነት›› ከሚባለው ከቀስተ ደመና ምስል እንደሆነ ይነገራል፡፡ በአካባቢው ማኅበረሰብ መቀነትን ትፍትፍ፣ ጃኖና ንቅሳት በማለት መድበው ይገለገሉበታል፡፡
ሻሽ
የጎጃምን ማኅበረሰብ ባህል ከሚወክሉ ሀገረሰባዊ አልባሳት መካከል ሻሽ አንዱ ነው፡፡ ሻሽ ከጥጥ የሚሠራና በሴቶች ራስ ላይ የሚጠመጠም ሲሆን፣ ራስን ከፀሐይና ከብርድ ለመከላከል፣ እንዲሁም ተውቦና ደምቆ ለመታየት ያገለግላል፡፡

No comments:
Post a Comment