- የቱሪዝም መለዮ በአማርኛ ‹‹ምድረ ቀደምት›› ተብሏል
- አቶ ሀብተ ሥላሴ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ሽልማት አግኝተዋል
17 መጋቢት, 2009
በቱሪዝም ትራንስፎርሜሽን ምክር ቤት አራተኛ መደበኛ ጉባኤ በፓርኮችና በሌሎች የአገሪቱ ቅርሶች ላይ ያንዣበቡ ችግሮች ሙሉ በሙሉ አለመቀረፋቸው ተጠቁሟል፡፡ በጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ የሚመራው ምክር ቤቱ አባላት የሆኑ የክልል ርዕሰ መስተዳደሮችና የባህልና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊዎች፣ የቱሪዝሙ መሠረት የሆኑ የአገሪቱ ቅርሶች ጥበቃ ትኩረት ሊቸረው እንደሚገባም ገልጸዋል፡፡ መጋቢት 13 ቀን 2009 ዓ.ም. በሸራተን አዲስ በተካሄደው ጉባኤ አስተያየታቸውን የሰጡ የምክር ቤቱ አባላት በየአካባቢያቸው ካሉ የቅርስ ጥበቃ ተግዳሮቶች በመነሳት፣ በአፋጣኝ መፍትሔ ካልተበጀ ችግሩን መቅረፍ አዳጋች ወደሚሆንበት ደረጃ መደረሱ እንደማይቀር አመልክተዋል፡፡
የቱሪዝም ዘርፉን ለማሻሻል የቱሪዝም ትራንስፎርሜሽን ምክር ቤት ከተቋቋመበት ጊዜ ጀምሮ በተካሄዱ ጉባኤዎች፤ ከዚያ በፊትም ለችግሮቹ የመፍትሔ ሐሳቦች ቢቀመጡም፣ በሚፈለገው መጠን መሬት ወርደው ስለማይተገበሩ ዛሬም ስለችግሮቹ ለማውራት መገደዳቸውን የምክር ቤቱ አባላት ተናግረዋል፡፡
የታሪካዊ ሥፍራዎችና የፓርኮች ጥበቃ ጉዳይ የአብዛኞቹ የምክር ቤቱ አባላት ጥያቄ የነበረ ሲሆን፣ በአሳሳቢ ደረጃ ስለሚገኙ ቅርሶቻቸውም በአጽንኦት ተናግረዋል፡፡ የደቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደሴ ዳልኬ እንደገለጹት፣ ነጭ ሳር ፓርክን ከተጋረጠበት አደጋ ለመታደግ በደቡብና ኦሮሚያ ክልሎች የጥምረት ሥራዎች እንዲከናወኑ ቢታቀድም ዕውን አልሆነም፡፡ ፓርኩ በሰዎች ሠፈራ ምክንያትም እየጠፋ ይገኛል፡፡ በተያያዥም የጥያ ትክል ድንጋዮች ይዘታቸውን የመቀየርና የመውደቅም አዝማሚያ እያሳዩ ነው፡፡ ‹‹ቅርሶችን ማስመዝገብ ብቻ ሳይሆን ጥበቃውም አብሮ መታየት አለበት፤›› በማለትም ተናግረዋል፡፡
ርዕሰ መስተዳድሩ እንደሚሉት፣ ኅብረተሰቡ የፓርኮች ባለቤት ሆኖ በቱሪዝም ከሚያስገኙት ገቢም ተጠቃሚ የሚሆንበት መንገድ ካልተፈጠረ ፓርኮች እስከወዲያኛው ሥጋት ያጠላባቸዋል፡፡ ማኅበረሰቡ የባለቤትነት ስሜት እንዲሰማው ካልተደረገ በስተቀር ዘላቂ ለውጥ እንደማይመጣም አክለዋል፡፡ ሐሳባቸውን የተጋሩት የአፋር ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ አቶ መሐመድ ያዩ፣ ‹‹የአካባቢው ማኅበረሰብ ባይተዋር ሆኖ ፓርኮችን እናለማለን ብሎ ማሰብ ይከብዳል፡፡ ኅብረተሰቡንና ፓርኮችን ማስታረቅ ይገባል፤›› ብለዋል፡፡
ተመሳሳይ ቅሬታዎች የተሰነዘሩት ከሁለቱ ክልሎች ብቻ ሳይሆን ከሌሎችም ሲሆን፣ የአማራ ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ ሒሩት ካሰው (ዶ/ር)፣ በክልሉ ቅርሶች አመዘጋገብና ጥገና በርካታ ችግሮች እንዳሉ ተናግረዋል፡፡ ለቅርሶች ጥገና ሲካሄድ የቀደመ ይዘታቸውን አለመቀየራቸው በዋነኛነት ሊተኮርበት ቢገባም፣ ቅርሶች የሚጠገኑት በዚህ መንገድ አለመሆኑን አመልክተዋል፡፡ ‹‹ቅርስን የሚጠግነው ማነው? የሚጠገነውስ እንዴት ነው? የሚለው ሊታሰብበት ይገባል፡፡ የጣና ቂርቆስ ገዳም ጣሪያው ተነስቶና ግርግዳው ፈርሶ ነው ያለው፡፡ ታሪክና ማንነትም እየጠፋ ነው፤›› ሲሉም አስረድተዋል፡፡
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ቅርሶች ነባርነታቸውን ሳይለቁ መታደስ እንዳለባቸው በአጽንኦት ተናግረው፣ በዚህ ረገድ ብቁ የሆኑ ባለሙያዎችን ማሰማራት መፍትሔ እንደሚሆን አመልክተዋል፡፡ በርካታ የብራና መጻሕፍት የሚቀመጡበት ሰፊ ቦታ ባለማግኘታቸው ታጭቀው እንደተቀመጡና ይህም ለብልሽት ዳርጓቸዋል ብለዋል፡፡ ፓትርያርኩ የጣና ቂርቆስ ገዳም ዕድሳትን እንደ ምሳሌ ጠቅሰው ስለ ዕድሳቱ መረጃ እንዳልደረሳቸውና የመረጃ ልውውጥ ቢኖር የተሻለ መሥራት እንደሚቻል ተናግረዋል፡፡
የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር ሒሩት ወልደማርያም (ዶ/ር) በጉባኤው ባቀረቡት ሪፖርት የፓርኮችን ይዘትና የቅርስ ጥበቃን በማሻሻል ረገድ የታዩ ለውጦች መኖራቸውን ቢገልጹም፣ አሁንም የተፈለገውን ያህል ውጤት አለመገኘቱን ተናግረዋል፡፡ ለምሳሌ በባቢሌና በነጭ ሳር ብሔራዊ ፓርኮች አካባቢ ያሉ ክልሎች በጋራ መፍትሔ እንዲፈልጉ ለማድረግ የተደረገው ጥረት ፍሬ አላፈራም፡፡ በማጎና በኦሞ ብሔራዊ ፓርኮች ሕገወጥ አደን ከመስፋፋቱም በላይ የስካውት አባላት ግድያ እየተባባሰ መጥቷል፡፡ የባቢሌ ዝሆኖች ግድያና በአብያታና ሻላ ሐይቆች ያለው የሕዝብ ሠፈራም በአሳሳቢ ደረጃ ይገኛል፡፡
በቅርስ ጥበቃ የላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስትያናት፣ የአክሱም መካነ ቅርስና የይሓ መካነ ቅርስ ጥገናና የመሠረተ ልማት ዝርጋታ ተጠቃሽ ቢሆኑም በአገሪቱ ካሉት ጥገና የሚሹ ቅርሶች አንፃር ብዙ ይቀራል፡፡ የገንዘብና የባለሙያ ውስንነት የሚፈለገውን ርቀት ያህል እንዳይጓዙ እንዳገዳቸው ገልጸዋል፡፡ ከቅርሶች ጥበቃ ጎን ለጎን የመዳረሻ ልማት ለቱሪዝም መበልፀግ የሚጫወተውን ከፍተኛ ሚና ሚኒስትሯ ገልጸው፣ በቱሪስት መዳረሻ አካባቢዎች ያለው የክፍያ ሥርዓት ወጥነት ማጣቱ ሌላው ፈተና ነው ብለዋል፡፡
በመዳረሻ አካባቢዎች የክፍያ መዘበራረቆች እንደሚታዩና በመስተንግዶ ተቋማትም ተገቢ ያልሆነ የዋጋ ጭማሪ እንደሚደረግ ገልጸዋል፡፡ በተያያዥም በመዳረሻ አካባቢዎች ያሉ አስጎብኚዎችና ከሌላ አካባቢ ወደ ቱሪስት መዳረሻዎች በሚጓዙ አስጎብኚዎች መካከል ግጭት እንደሚፈጠርና የዋጋ ጭማሪም ቱሪስቶችን እንደሚያውክም ተናግረዋል፡፡ ሚኒስትሯ ለዚህ መፍትሔ ይሆናል ያሉት የቱሪዝም ዘርፉን ተዋናዮች ባጠቃላይ የሚመራ ገዥ የሕግ ማዕቀፍ ማዘጋጀትን ነው፡፡
በጉባኤው ከተነሱ ነጥቦች መካከል አገሪቱን በዓለም የማስተዋወቅ ጉዳይም ይገኝበታል፡፡ የኢትዮጵያ ቱሪዝም ድርጅት ዋና ዳይሬክተር አቶ ሰለሞን ታደሰ ባቀረቡት ሪፖርት በዓለም አቀፍ የንግድ ትርኢቶች በመሳተፍና የአገር ውስጥና የውጭ መገናኛ ብዙኃንን በመጋበዝ የተደረጉ እንቅስቃሴዎችን ገልጸው፣ ድርጅቱ በዌብሳይት፣ ፌስቡክ፣ ትዊተርና ሌሎችም ዲጂታል ማስታወቂያዎችን እየተጠቀመ መሆኑን አብራርተዋል፡፡
ሆኖም የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ጌታሁን መኩሪያ (ዶ/ር) ዓለም ከደረሰበት ቴክኖሎጂ አንፃር አገሪቱ እየተጠቀመችባቸው ያሉ ዲጂታል ማስታወቂያ መንገዶች ዘመን ያለፈባቸውና ውስን መሆናቸውን ተችተዋል፡፡ አገሪቱን እንዲጎበኙ ጥሪ የሚቀርብላቸው ሰዎች የሚጠቀሙበትን ቴክኖሎጂ የሚመጥን ሥርዓት መዘርጋት እንዳለበትም አሳስበዋል፡፡
ከጎረቤት አገሮች ውስጥ ኬንያ የዱር እንስሳትን እንቅስቃሴ ለመከታተልና መረጃ ለመያዝም የምትጠቀመውን ቴክኖሎጂ የጠቀሱት ሚኒስትሩ፣ በኢትዮጵያ ውስጥም መሰል አካሄድ እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል፡፡ የአገሪቱን ሀብቶች በመመዝገብ፣ በመጠበቅና በማስተዋወቅም ቴክኖሎጂ ከፍተኛ ሚና ስላለው ከጥቃቅን ሙከራዎች የላቀ ሥራ መሠራት አለበትም ብለዋል፡፡
ጉባኤውን የታደሙ ሌሎች ሚኒስትር መሥሪያ ቤቶችም በየዘርፋቸው ከቱሪዝም ጋር በተያያዘ መሠራት ያለበትን ገልጸዋል፡፡ ከምክር ቤቱ አባላቱ ከተነሱ አስተያየቶች መካከል የኢትዮጵያ ደራስያን ማኅበር ፕሬዚዳንት ሙሴ ያዕቆብ (ዶ/ር) ያቀረቡት ይጠቀሳል፡፡ ቱሪዝምና ጥበብ እጅና ጓንት ሆነው መጓዝ እንዳለባቸውና በዘርፉ ያሉ ችግሮችን ጠቁሞ መፍትሔ በማመላከት ረገድ ጥበብ የሚጫወተውን ሚና አስረድተዋል፡፡ እንደ ምሳሌ የወሰዱት የብዙኃኑ የጉባኤው ተሳታፊዎች ጥያቄ የነበረውን የፓርኮች ጉዳይ ሲሆን፣ ነጭ ሳር ፓርክና የባቢሌ ዝሆኖች ስላንዣበባቸው አደጋ የሚያሳውቁ ጥበባዊ ሥራዎች ቢሠሩ የኅብረተሰቡን ትኩረት በቀላሉ እንደሚያገኙ ተናግረዋል፡፡
ሌላው የብዙዎች አስተያየት የነበረው ጉዳይ በቱሪዝሙ ዘርፍ ኢንቨስት የሚያደርጉ ባለሀብቶች የሚያገኟቸው ማበረታቻዎች ነው፡፡ ልዩ ልዩ ቁሳቁሶች ከቀረጥ ነፃ ከውጪ እንዲገቡ መፍቀድና ሌሎች ማበረታቻዎችም ለባለሀብቶች ቢሰጡም፣ ማበረታቻዎቹ የሚበዘበዙባቸው አጋጣሚዎች መኖራቸው ተጠቁሟል፡፡ በተለይም በሆቴልና መስተንግዶ ዘርፍ የሚሰማሩ አንዳንድ ግለሰቦች ከቀረጥ ነፃ የሚያስገቧቸውን ዕቃዎች ያላግባብ ገበያ ላይ እንደሚያውሏቸው ተገልጿል፡፡ ከብዝበዛው ባሻገር ኢንቨስትመንትን ለማበረታታት በየክልሎቹ ያለው የመሬት አቅርቦት ተመሳሳይ አለመሆኑን አቶ ሰለሞን ተናግረዋል፡፡ አዳዲስ የቱሪዝም ፕሮጀክቶችን ተግባራዊ ለማድረግም ማበረታቻ እንደሌለ አክለዋል፡፡
ከጉባኤው አባላት ለተነሱ ጥያቄዎችና ቅሬታዎች ምላሽ የሰጡት ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም፣ የምክር ቤቱ አባላት በየጉባኤው የሚነሱ የቱሪዝሙ ዘርፍ ችግሮች ተመሳሳይ እንደሆኑ መግለጻቸውን በተመለከተ፣ በየጉባኤው የሚቀመጡ የመፍትሔ ነጥቦች በሚመለከታቸው አካላት መተግበር እንዳለባቸው አስረግጠዋል፡፡ የመዳረሻ ልማትን በተመለከተ ባለሀብቶች ከፍተኛ አስተዋጽኦ ስላላቸው የባለሀብቶች ማበረታቻን የሚመራ የፖሊሲ አቅጣጫ ተጠንቶ እንዲቀርብ በሦስተኛው የምክር ቤቱ ጉባኤ ቢጠየቅም አልቀረበም፡፡ ጥናቱ በተባለው ጊዜ አለመቅረቡ አንድ ምሳሌ ቢሆንም ሌሎችም ዕቅዶችን እንዲተገብሩ ኃላፊነት የተሰጣቸው አካላት ለችግሮች መፍትሔ በመስጠት ፋንታ ደጋግመው ስለ ችግሮቹ ማማረር እንደሌለባቸው ተናግረዋል፡፡
በሌላ በኩል የመሠረተ ልማት ዝርጋታ ውስንነት ለቱሪዝሙ ማነቆ እየሆነ ነው የሚለውን ምክንያት እንደማይቀበሉ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገልጸው፣ ዋነኛ ተግዳሮት ለቱሪስቶች ምቹ ማረፊያ አለመኖሩ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ የኤርፖርቶች መስፋፋት በዋነኛነት የመሠረተ ልማት ዝርጋታ ጥያቄን ይመልሳል ብለው፣ የባለሀብቶች በዘርፉ የመሰማራት ጉዳይ የበለጠ ጥያቄ እንደሆነ አክለዋል፡፡
በእርግጥ ከቀረጥ ነፃ መሆንን የመሰሉ ማበረታቻዎች መበዝበዛቸውን እንደ ምክር ቤቱ አባላት እሳቸውም ሳይጠቅሱ አላለፉም፡፡ ‹‹አንዳንድ ወሮበሎች ከቀረጥ ነፃ የመጣውን ዕቃ ሸጠው በልተዋል፤›› በማለት ለሆቴል ሥራ ከሚያስፈልገው በላይ ዕቃ አስገብቶ በመሸጥ ዘርፉ እንዳያድግ ያደረጉ ባለሀብቶችን ኮንነዋል፡፡
በፓርኮችና ቅርስ ጥበቃ እንዲሁም ቱሪዝሙን ለማበልፀግ የቴክኖሎጂ ግብዓቶችን በመጠቀም ረገድ የቀረቡት አስተያየቶች ተቀባይነት ቢኖራቸውም፣ ጉዳዩ የሚመለከታቸው አካሎች ቅሬታ ከማቅረብ ባለፈ ምን ያህል ኃላፊነታቸውን ተወጥተዋል? የሚለው የበለጠ ሊታሰብበት እንደሚገባ አመልክተዋል፡፡
በጉባኤው ‹‹ላንድ ኦፍ ኦሪጂንስ›› የሚለው የቱሪዝም መለያ ‹‹ምድረ ቀደምት›› የሚል አማርኛ ፍቺ ተሰጥቶታል፡፡ በጉባኤው እንደተገለጸው፣ ለመለዮው አማርኛ ስያሜ በመፈለግ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ መምህራን የተሳተፉ ሲሆን፣ ‹‹ምድረ ቀደምት›› ከሚለው መጠሪያ በተጨማሪ ‹‹የቀደምት ምድር›› እና ‹‹መሠረተ ጥንት›› የሚሉ አማራጮች ቀርበው ምድረ ቀደምት፣ ገላጭ፣ ቀላልና በልቦና የሚቀር በመሆኑ ተመርጧል፡፡ በጉባኤው ‹‹የ13 ወር ፀጋ›› የሚለውንና ኢትዮጵያ ለዘመናት የተገለገለችበትን መለዮ በማመንጨትና በቱሪዝሙ የማስተዋወቅ ዕርምጃ ፈር ቀዳጅ በመሆንም ‹‹የቱሪዝም አባት›› በሚል የሚጠሩት አቶ ሀብተ ሥላሴ ታፈሰም ለአስተዋጽኦዋቸው ሽልማት ተበርክቶላቸዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለአቶ ሀብተ ሥላሴ የወርቅ ፒን ያደረጉላቸው ሲሆን፣ 50 ሺሕ ብርና የምስክር ወረቀትም ተሰጥቷቸዋል፡፡

No comments:
Post a Comment