የገና በዓል መገለጫ ከሆኑት አንዱ ዛፍ ነው፡፡ ቀደም ሲል ጥድ እየተቆረጠ በልዩ ልዩ ማሸብረቂያዎች ይዋብ ነበር፡፡ አሁን አሁን አርቲፊሻል ዛፎች በየቦታው ነግሰው ይታያሉ፡፡ በዘንድሮው ገናም በተለያዩ ከተሞች በየአደባባዩ በየመደብሩ ደጃፍ ተተክለው እየታዩ ነው፡፡ ከሕፃን እስከ አዋቂ ፎቶ ሲነሱበትም ነበር፡፡ በመቐለ ከተማ ጅብሩክ አካባቢ በሚገኘው ወዲ መሸሻ ሕንፃ የቆመው አንዱ ነው፡፡ በድረ ገጽ ውስጥ የተገኘው የገና ዛፍ ደግሞ በበለስ ዛፍና ፍሬው የተዋበ ነው፡፡ በሥነ ቃል የሚባለውን ‹‹ዕፀ በለስ በልቶ ሔዋን ከንፈርሽ፣ መድኃኔ ዓለም ልቤ ተሰቀለልሽ››ን ያስታውሳል፡፡