21 Jan, 2017
በተለያዩ
አካባቢዎች ያሉ ወጣቶች ለጥምቀት መሰናዶ የጀመሩት በከተራ ዋዜማ ነበር፡፡ ሰንደቅ ዓላማና ልዩ ልዩ ሃይማኖታዊ
ምሥሎች በየሥፍራቸው ሰቅለዋል፡፡ ታቦት አጅበው ለሚሸኙና ለሚቀበሉ ምዕመናን ማረፊያ የፕላስቲክ ወንበሮችና የመጠለያ
ዳስ፣ ድፎ ዳቦና ውኃ ያዘጋጁም ነበሩ፡፡ ከነዚህ ወጣቶች አብዛኞቹ ተመሳሳይ የአገር ባህል ልብስ ለብሰው
ታይተዋል፡፡
በጥምቀት በዓል ጎልተው የታዩት በርካታ አዳዲስ የአገር ባህል ልብስ ዓይነቶችና አለባበሶች ትኩረት ሳቢ ናቸው፡፡ ፋብሪካ በተሠራ ካናቴራ ላይ ጥለት አሰፍተው የለበሱ፣ ካናቴራ ላይ ጥበብ ሰደሪያ የደረቡም ነበሩ፡፡ አምስትና ከዚያ በላይም ሴት ወጣቶችም በተመሳሳይ ጥበብ ቀሚስ ታይተዋል፡፡ የአንዳንዶቹ ጥለቱ ተመሳሳይ ሆኖ አሠራሩ መጠነኛ ልዩነት አለው፡፡
‹‹ለጥምቀት ያልሆነ ቀሚስ ይበጣጠስ›› የሚለው ዕድሜ ጠገብ ብሂል በዕውን ታይቷል ማለት ይቻላል፡፡ በዘንድሮው የጥምቀት በዓል እንዲሁም ባለፉት ጥቂት ዓመታትም በአሠራር ከተለመደው ወጣ ያሉ የአገር ባህል ልብሶች ማስተዋል ተጀምሯል፡፡ በዕውቅ ዲዛይነሮች ከተሠሩ ጥበብ ልብሶች፣ ፋብሪካ በተሠሩ ጨርቆች ላይ ጥበብ እስከተጠለፈባቸው ድረስ ይገኛሉ፡፡ በእርግጥ ጥምቀት ሁሉም በአቅሙ አምሮና ደምቆ የሚታይበት በዓል ነው፡፡ የተዘራ የሚታጨድበትና የሠርግ ወቅም እንደመሆኑ በዓሉ ይደምቃል፡፡
የበዓሉ ሃይማኖታዊ ይዘት እንዳለ ቢሆንም ከጊዜ ወደ ጊዜ የአክባሪዎቹ አለባበስና የምእመናኑ አከባበር ላይ ለውጦች አሉ፡፡ እስከ 1940ዎቹ ድረስ የአገር ባህል ልብስ የመደበኛ ቀን ልብስ እንደነበር ይነገራል፡፡ የወንዶች ተነፋነፍና እጀ ጠባብ እንዲሁም የሴቶች ጥልፍ የቤት፣ የሥራና የክት ልብስም ነበር፡፡ እንደየአካባቢው ባህል የተለያየ አሠራርና ስያሜ ያላቸው የአገር ባህል ልብሶች፣ ለበዓላት ወይም ለተለየ መርሐ ግብር ብቻ የሚለበሱ ከሆኑ በኋላ በአቀራረባቸውም ለውጥ ታይቷል፡፡
የሴቶች ጥበብ በሱሪ ወይም በቦዲ መልክ ማግኘት ይቻላል፡፡ በእራት ልብስ ዲዛይን የሚሠሩ ቀሚሶች ገበያም የደራ ነው፡፡ ለወንዶችም ጥበብ በሸሚዝ፣ በከረባት በኮትና ስካርፍ ይቀርባል፡፡ የአገር ባህል ልብስ ከኢትዮጵያ አልፎ በዓለም አቀፍ መድረክም ተቀባይነት እያገኘ ነው፡፡ እዚህ ላይ እንደ ኒውዮርክ ፋሽን ዊክ ባሉ ዓለም አቀፍ የፋሽን መድረኮች በኢትዮጵያውያን ዲዛይነሮች የተሠሩ ጥበብ ልብሶች ለዕይታ መቅረባቸውን መጥቀስ ይቻላል፡፡ ጥበብ በአገሬው ዘንድ ከበዓል ባለፈ በሠርግ፣ መልስ፣ ምርቃትና ልደትም ይለበሳል፡፡ የኪነ ጥበብ ባለሙያዎች በሽልማት መድረኮችና ሥራዎቻቸውን ሲያስመርቁም በጥበብ ይዋባሉ፡፡
በአጠቃቀም ረገድ መልኩን እየለወጠ የመጣው የአገር ባህል ልብስን በተመለከተ ከሚሰነዘሩ ጥያቄዎች ቀዳሚው የዋጋ ጉዳይ ከሆነ ሰባብቷል፡፡ ጥበብ የሚሸጥበት ዋጋ እንደ አገር ባህል ልብስነቱ ብዙዎች ሊለብሱት የሚያስችል ነው የሚሉ በርካቶች ናቸው፡፡ ልብሶቹን ለማዘጋጀት ከሚወጣው ወጪና ከሚወስደው ጊዜ ጋር ተመጣጣኝ የሆነ ዋጋ እየተጠየቀባቸው ነው ወይ? የሚለውን ማንሳትም ይቻላል፡፡
የአገር ባህል ልብሶች በዘመነኛ መንገድ መምጣታቸው መልካም ሆኖ ሳለ ገበያ ላይ በሚቀርቡበት ዋጋ ስንቶች ያለ ቅሬታ ይገዛሉ? የሚለው አጠያያቂ ነው፡፡ ሰዎች በአቅማቸው መግዛት የሚችሉት ልብስ ከከፍተኛ ዋጋ እስከ ዝቅተኛው ገበያ ላይ ቀርቧል ቢባልም እንደ ሠርግና ማኅበር ባሉ ሁነቶች ተመሳሳይ ጥበብ ማሰፋት ግድ ይሆንና የአንዳንዶችን ኪስ ያስጨንቃል፡፡ የአገር ባህል ልብስ የሚል ስያሜ ተሰጥቶት ሳለ በአገሬው ነባራዊ ሁኔታ ለመግዛት ይቻላልን? የሚል ጥያቄ የሚነሳውም ለዚሁ ነው፡፡
ለምሳሌ በሴቶች ቀሚስ ረገድ ጥበብ እስከ 20,000 ብር ድረስ ይሸጣል፡፡ ዋጋውን ከልብሶቹ የአሠራር ዘዬና ጥራት አንፃር ተመልክተው ተገቢ ነው የሚሉ ቢኖሩም ተገቢ አይደለም የሚሉም አሉ፡፡ የጥበብ ዋጋ ልብሱ ከሚሸጥበት ቦታ አንፃር የሚለያይበት አጋጣሚም አለ፡፡ ቦሌና ሃያ ሁለት አካባቢ ባለውና በሽሮሜዳው የጥበብ ዋጋ ልዩነት አስተውለናል፡፡ ስማቸው በገነነ ዲዛይነሮችና ያልታወቁ ሰፊዎች መካከልም ልዩነቱ ይታያል፡፡
ወ/ሮ አስመረት ግርማይ የጥበብ ዋጋ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየናረ እንደመጣ ይናገራሉ፡፡ አንዳንዶቹ የአገር ባህል ልብሶች በጥራት ተሠርተው ብዙ ዋጋ የሚጠየቅባቸው ቢሆኑም የአብዛኞቹ ልብሶች ዋጋ ተገቢ እንዳልሆነ ይገልጻሉ፡፡ ‹‹በመነን ጨርቅ በሳባ ክር የተሠራ ቆንጆ ጥልፍ ቀሚስ ከ7,000 ብር በታች አይገኝም፡፡ ይህ ከአብዛኞቻችን የመግዛት አቅም በላይ ነው፤›› ይላሉ፡፡ በእሳቸው ገለጻ፣ ጥበብ ልብስ ከኢትዮጵያ ውጪ ያለው ገዥ ማለትም ቱሪስትና ዳያስፖራ ላይ ያነጣጠረ ይመስላል፡፡
ወ/ሮ አስመረት አምና ለልጃቸው ሠርግ በተመጣጣኝ ዋጋ ጥበብ ቀሚስ ለመፈለግ ብዙ መልፋታቸውን ያስታውሳሉ፡፡ ለልጃቸው ሠርግና መልስ ከእህቶቻቸውና የቅርብ ጓደኞቻቸው ጋር ተመሳሳይ ጥበብ ቀሚስ ፈልገው ዋጋ ለማጥናት ያልገቡበት ሠፈር እንደሌለም ይናገራሉ፡፡ የጥበብ ገበያ ተስፋፍቶ በየቦታው ሱቆች መኖራቸውና ከዲዛይን አንፃርም አማራጭ መኖሩ ጥሩ ቢሆንም ዋጋው መስተካከል አለበት ይላሉ፡፡
ከጥቂት ዓመታት ወዲህ በየአካባቢው በሚገኝ መገበያያ ሕንፃ አንድና ሁለት የባህል ልበሶች መደብር ይገኛል፡፡ በመደብሮቹ የተመልካችን ቀብል የሚስቡ ጥበቦች ስለሚሰቀሉ አላፊ አግዳሚ መለስ ብሎ ያያል፡፡ እነዚህ ልብሶች በጥራት የሚሠሩና ረዘም ላለ ጊዜ የሚያገለግሉ በመሆናቸው ዋጋው ጥያቄ መሆን የለበትም የሚለው ታምራት ዘነበ ነው፡፡ ‹‹ዋጋቸው ውድ የሆኑት ልብሶች የሚሠሩት ደረጃውን በጠበቀ መንገድ ነው፡፡ ከፈትል ጀምሮ ዲዛይን እስከሚደረግ ያሉት ባለሙያዎች በጥራት ይሠሯቸዋል፤›› ይላል፡፡ ጥበብ በአንድ ዓመት ውስጥ እንኳ ጥቂት ቀናት ብቻ ስለሚለበስ ገዥዎች የረዥም ጊዜ አገልግሎት ያገኛሉ ሲልም ይገልጻል፡፡
ጥበብ ስካርፍ 500 ብርና ጥበብ ኮት 5,000 ብር የገዛበትን አጋጣሚ ያስታውሳል፡፡ ወደ ውጪ ለሚሄዱ ሰዎች ስጦታ የ6,000 ብር የአዋቂ ቀሚስና በ4,000 ብር የልጆች ልብስም ገዝቷል፡፡ በእሱ እምነት ልብሶቹ ማማራቸውና ለረዥም ጊዜ የሚቆዩ መሆናቸው የሚሸጡበትን ዋጋ አዋጭ ያደርገዋል፡፡ ሲታጠቡ የሚሳሱና የሚቀዳዱ ልብሶች አነስ ባለ ዋጋ ሊገኙ ይችላሉም ይላል፡፡
ከመደብሮች በተጨማሪ ለኦንላይን ግብይትም የቀረቡ ጥበብ ልብሶች አሉ፡፡ ነጠላ ከ350 እስከ 6,000 ብር ይገኛል፡፡ ጥበብ ቀሚስ ከ60 ዶላር እስከ 550 ዶላር ኢቤይ ላይ ይሸጣል፡፡ የተለያዩ ብሔር ብሔረሰቦች አልባሳት ዋጋ የተለያየ ሲሆን፣ በሸማኔ የተሠራ ጥበብና በፋብሪካ በተሠራ ጨርቅ ላይ የተለጠፈ ጥበብም ይለያያሉ፡፡
ዛሬ ዛሬ እየተለመደ የመጣው በደማቅ ሳተን ጨርቅ የሚሠራ ቀሚስም ተጠቃሽ ነው፡፡ በሰማያዊ፣ ቢጫ፣ አረንጓዴ ወይም ሌላ ሳተን ጨርቅ ላይ ጥለት ይለጠፋል፡፡ የነጠላ ጫፍ ደግሞ ጥለት ሳይኖረው ከቀሚሱ ጨርቅ ጋር የተመሳሰለ ጨርቅ ይሰፋበታል፡፡ ሳተን ቀሚስ ላይ በክር ጥበብ ተጠልፎ የሚሸጥበትም ጊዜ አለ፡፡ ብዙዎች በሸማኔ የተሠራ የጥጥ ፈትል ጥበብ ልብስ ቢመርጡም ወደዚህኛው የሚያዘነብሉም አሉ፡፡ አንዳንዴ ጥበብ የመልበስ ፍላጎት ቢኖራቸውም ዋጋው አልቀመስ ያላቸው ሰዎች ጥበብን በማስመሰል ወደተሠራው ሳተን ሳይወዱ በግድ ፊታቸውን ሲያዞሩ ይታያል፡፡
ሮዛ ይርጋ በሳተን ጨርቅ የተሠራ ቀሚስ በ2,500 ብር የገዛችው በቅርብ ነው፡፡ ከዚያ በፊት ለተለያዩ በዓሎች የሸማ ጥበብ ቀሚስ ከ2,500 ብር እስከ 4,000 ብር ገዝታለች፡፡ ‹‹የጥበብ ገበያ ሁሉም ሰው በአቅሙ የሚገዛበት ነው፤›› ትላለች፡፡ ብዙ ጊዜ ጥበብ ከሽሮሜዳ እንደምትገዛ የምትገልጸው ሮዛ፣ በተመጣጣኝ ዋጋ የሸመተቻቸው ቀሚሶች ዕድሜ እንዳላቸውም ትናገራለች፡፡ በባለሙያዎች የተፈተለ ጥበብና በፋብሪካ የተሠራ ጨርቅ ላይ የተጠለፈ መካከል የዋጋ ልዩነት እንዳለና ሰው እንደ ምርጫው መግዛት እንደሚችልም ታስረዳለች፡፡ በእርግጥ የዋጋው ልዩነት ጠቦ ሰው ጥራት ያለው ልብስ ቢገዛ ይመረጣል፡፡ ከአገሪቱና ከሕዝቡ ነባራዊ ሁኔታ አንፃር ታስቦ ዋጋው ቢተመንም መልካም ነው፡፡
‹‹በቀለም የተነከረ ወይም በሳባ፣ በሱፍ ወይም በሹራብ ክር የሚሠራው ልብስ መካከል ሰፊ ልዩነት አለ፡፡ እንደየሥራቸው ዋጋቸውም ይለያያል፤›› ትላለች፡፡ ሮዛ ከሠርግና ከምርቃት በተጨማሪ ለበዓልና ከበዓል በኋላ ባሉ ቀናትም ሥራ ቦታዋ ላይ ጥበብ ለብሳ ትገኛለች፡፡ መካከለኛ ገቢ ያላት ሲሆን፣ ለጥበብ የምታወጣው ወጪ ከሌሎች ልብሶቿ ቢበልጥም፣ ኪሷን እንዳልጎዳው ትናገራለች፡፡ እሷ ጥሩ በምትለው ዋጋ ከምትገዛቸው ልብሶች ጋር የሚመሳሰሉ ልብሶች በውድ ዋጋ የሚሸጡባቸው አካባቢዎች እንዳሉም ታክላለች፡፡ ‹‹በጥራታቸው መካከል ልዩነት የለውም፡፡ አንዳንዴ የሞል ኪራይ ለመክፈል ልብሶቹ ላይ ዋጋ የሚጨምሩ ነጋዴዎች አሉ፤›› ትላለች፡፡
ከዓመታት በፊት ጥበብ በ200 እና 300 ብርም ይሸጥባቸው የነበሩ እንደ ሸማ ተራ ባሉ አካባቢዎች ዛሬ 1,000 ብርና ከዚያም በላይ ይጠራባቸዋል፡፡ ከጊዜ ወደ ጊዜ ምርቶች ላይ የሚደረገው የዋጋ ጭማሪ ጤናማ ቢሆንም፣ የጥበብ ልብሶች ዋጋ ጉዳይ አሳሳቢ እንደሆነ የሚገልጹ አሉ፡፡ የልብሶቹ ዋጋ የጨመረው ጥራት ስላላቸውና ዘመነኛ ገጽታ ስለተላበሱ ነው በሚለው የሚስማሙና የማይስማሙም አሉ፡፡
አንድ ያነጋገርነው አባት፣ ‹‹ሁለት ልጆቼ የብሔር ብሔረሰቦችን በዓል ትምህርት ቤት ሲያከብሩ የጉራጌና የራያ ልብስ ለመግዛት ከ800 ብር በላይ አውጥቻለሁ፤›› ይላል፡፡ አንዲት እናት ለልጇ ልደት ቤተሰባቸው ተመሳሳይ ጥለት ያለው ልብስ እንዲለብስ አስባ ለሷ፣ ለልጇና ለባለቤቷ ወደ 4,000 ብር ማውጣቷን ትገልጻለች፡፡ ሁለቱም አስተያየት ሰጪዎች ‹‹አማራጭ የለም›› ነበር ያሉት፡፡
የእንቁ ዲዛይን መሥራች ዲዛይነሯ እንቁጣጣሽ ክብረት፣ የጥበብ ዋጋ እንደየዲዛይኑ ቢለያይም ሁሉም የገዥ አቅም ያገናዘበ እንደሆነ ትገልጻለች፡፡ ‹‹ሸማኔ፣ ጠላፊ፣ ዲዛይነርና ሰፊ እንደሚወስድባቸው ጊዜና እንደ ልብሱ አሠራር ረቂቅነት ዋጋው ይተመናል፤›› ትላለች፡፡ እስከ ሁለት ወር የሚወስዱና ዲዛይናቸው ከባድ የሆኑ ልብሶች እስከ 20 ሺሕ ብር ይሸጣሉ፡፡ ዲዛይነሯ እንደምትለው፣ ከባለሙያዎች ድካም አንፃር ከተማው ላይ ያለው የአገር ባህል ልብስ ዋጋ ተገቢ ነው፡፡ በተለይም ለሠርግና ለበዓላት ጥበብ የሚያሠሩ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ እንደሆነም ትናገራለች፡፡
እንቁጣጣሽ የባህል ልብሶችን ለገበያ የምታቀርበው በተለያየ ፓኬጅ ሲሆን፣ እናትና ልጅ ኮሌክሽን እንዲሁም ቤተሰብ ኮሌክሽን የሚሉ አማራጮች አሏት፡፡ እንደ ቤተሰቦች ብዛት ከ6,000 ብር ጀምሮ እስከ 15,000 ብር ይሸጣል፡፡ የሙሽራ ልብስ ከ5,000 እስከ 20,000፣ የሚዜና ሌሎች ተጠሪዎች ልብስ ከ3,500 ብር ጀምሮ ይገኛል፡፡
ዲዛይነሯ ዘርፉን ከጥበብ ዋጋ በተጨማሪ ከተደራሽነት አንፃርም ታየዋለች፡፡ የባህል ልብስን ከበዓላት ውጪ የሚለብሱ ሰዎች ቁጥር ባይጨምርም፣ የኢትዮጵያውያን ዲዛይነሮች ልብሶች ዓለም አቀፍ ዕውቅና ማደጉን ትገልጻለች፡፡ በተቃራኒው የፋሽን ዝግጅት የሚያሰናዳው ሰለሞን ጌታቸው (ሶሎቢ) የጥበብ ዋጋ የገዥዎችን አቅም ያገናዘበ አይደለም ከሚሉት ወገን ነው፡፡ የጥበብ ዋጋ አሁን ባለበት አካሄድ ከቀጠለ ለወደፊት የገዥዎች ቁጥር እንደሚቀንስ ይናገራል፡፡
በከፍተኛ ዋጋ እየተሸጡ ካሉት ልብሶች አብዛኞቹ ከባህላዊ የጥበብ አሠራር መንገድ ያፈነገጡ መሆናቸውንም አይቀበለውም፡፡ ከሱ ጋር ተመሳሳይ አስተያየት ያላቸው ሰዎች በዋነኛነት በሳተን ጨርቅ የሚሠሩ ልብሶችና የትኛውንም የኢትዮጵያ አካባቢ የማይወክሉ ልብሶችን የአገር ባህል ልብስ ብሎ ለመጥራት አይቻልም ይላሉ፡፡ ሰለሞን እንደሚለው፣ ደረጃውን የጠበቀ ሥራ የሚያቀርቡ ብዙ ዲዛይነሮች ገበያውን ቢቀላቀሉም፣ የልብሶቹ መወደድ ዘርፉ እንዳያድግ አግዶታል፡፡ አንዳንድ ጥበብ ልብሶች የሚጠየቅባቸው ዋጋ ከአንድ ኢትዮጵያዊ አማካይ ገቢ አንፃር ለወራት አስቤዛ ሊያሸምቱም ይችላሉ፡፡
የባህል ልብስ በየትኛውም የኢኮኖሚ ደረጃ ያለውን ማኅበረሰብ ታሳቢ ያደረገ መሆን እንዳለበት ያምናል፡፡ የአገር የሚል መጠሪያ ያለው ልብስ ጥቂቶች ብቻ መምሰሉን አያይዞ ያነሳል፡፡ ጥሩ ስም ያላቸው ዲዛይነሮች እስከ 15,000 ብር ሲያስከፍሉ ሽሮ ሜዳ ወደ 3,000 ብር ገደማ ዋጋ የሚጠራው እንደቀላል ነው፡፡ ጥበብ ጠቀም ያለ ገቢ ካላቸው ሰዎች ውጪ የማይቀመስ መሆኑንም በአጽንኦት ይገልጻል፡፡
ብዙዎች ለሠርግ ወይም ለሌላ መርሐ ግብር ሲባል ግዴታ ካልሆነባቸው በስተቀር ጥበብ ለመግዛት እንደማይደፍሩም ያክላል፡፡ በባህላዊ ልብሶች አሠራርና በሚሸጡት ዋጋ ረገድ ቁጥጥር ቢደረግ ለውጥ እንደሚመጣ ያምናል፡፡
የአገር ባህል ልብስ በስፋት መቅረቡ፣ በብዙዎች ይመረጥና ይለበስ ዘንድ በተለያየ ዲዛይን መቅረቡ እሰየው የሚያስብል ቢሆንም ይህ በአቅርቦት፣ በጥራትና በተሻለ ዲዛይን እየቀረበ ያለ የአገር ባህል ልብስ ዋጋ ሰማይ እየነካ መሄድ የአገር ባህል ልብስ ሆኖ መቀጠል መቻሉን ጥያቄ ውስጥ ይከታል፡፡ ልብሱን ማድረግ የሚችለው ሰፊው ሕዝብ አገሬው መሆኑ ቀርቶ የውጭ አገር ዜጎችና ዳያስፖራው ከሆነ፤ ሰፊው ሕዝብ ከዲዛይንና ከጥበብ አንፃርም፣ በእውነተኛው ጥበብ ፋንታ የሚጠለፈውን፣ ከውጭ የሚገባውን ጥለት መሰል ጨርቅና ሸማ ሳይሆን ሳተንን ወደ መምረጥ (ተገዶም ቢሆን) መሄድ የብዙዎች ጭንቀት ሆኗል፡፡

- ምሕረተሥላሴ መኰንን's blog
- 449 reads
No comments:
Post a Comment