Monday, January 23, 2017

በአገር ሰው የማይደፈረው የአገር ባህል ልብስ ዋጋ21 Jan, 2017
በተለያዩ አካባቢዎች ያሉ ወጣቶች ለጥምቀት መሰናዶ የጀመሩት በከተራ ዋዜማ ነበር፡፡ ሰንደቅ ዓላማና ልዩ ልዩ ሃይማኖታዊ ምሥሎች በየሥፍራቸው ሰቅለዋል፡፡ ታቦት አጅበው ለሚሸኙና ለሚቀበሉ ምዕመናን ማረፊያ የፕላስቲክ ወንበሮችና የመጠለያ ዳስ፣ ድፎ ዳቦና ውኃ ያዘጋጁም ነበሩ፡፡ ከነዚህ ወጣቶች አብዛኞቹ ተመሳሳይ የአገር ባህል ልብስ ለብሰው ታይተዋል፡፡
በጥምቀት በዓል ጎልተው የታዩት በርካታ አዳዲስ የአገር ባህል ልብስ ዓይነቶችና አለባበሶች ትኩረት ሳቢ ናቸው፡፡ ፋብሪካ በተሠራ ካናቴራ ላይ ጥለት አሰፍተው የለበሱ፣  ካናቴራ ላይ ጥበብ ሰደሪያ የደረቡም ነበሩ፡፡ አምስትና ከዚያ በላይም ሴት ወጣቶችም በተመሳሳይ ጥበብ ቀሚስ ታይተዋል፡፡ የአንዳንዶቹ ጥለቱ ተመሳሳይ ሆኖ አሠራሩ መጠነኛ ልዩነት አለው፡፡
‹‹ለጥምቀት ያልሆነ ቀሚስ ይበጣጠስ›› የሚለው ዕድሜ ጠገብ ብሂል በዕውን ታይቷል ማለት ይቻላል፡፡ በዘንድሮው የጥምቀት በዓል እንዲሁም ባለፉት ጥቂት ዓመታትም በአሠራር ከተለመደው ወጣ ያሉ የአገር ባህል ልብሶች ማስተዋል ተጀምሯል፡፡ በዕውቅ ዲዛይነሮች ከተሠሩ ጥበብ ልብሶች፣ ፋብሪካ በተሠሩ ጨርቆች ላይ ጥበብ እስከተጠለፈባቸው ድረስ ይገኛሉ፡፡ በእርግጥ ጥምቀት ሁሉም በአቅሙ አምሮና ደምቆ የሚታይበት በዓል ነው፡፡ የተዘራ የሚታጨድበትና የሠርግ ወቅም እንደመሆኑ በዓሉ ይደምቃል፡፡
የበዓሉ ሃይማኖታዊ ይዘት እንዳለ ቢሆንም ከጊዜ ወደ ጊዜ የአክባሪዎቹ አለባበስና የምእመናኑ አከባበር ላይ ለውጦች አሉ፡፡ እስከ 1940ዎቹ ድረስ የአገር ባህል ልብስ የመደበኛ ቀን ልብስ እንደነበር ይነገራል፡፡ የወንዶች ተነፋነፍና እጀ ጠባብ እንዲሁም የሴቶች ጥልፍ የቤት፣ የሥራና የክት ልብስም ነበር፡፡ እንደየአካባቢው ባህል የተለያየ አሠራርና ስያሜ ያላቸው የአገር ባህል ልብሶች፣ ለበዓላት ወይም ለተለየ መርሐ ግብር ብቻ የሚለበሱ ከሆኑ በኋላ በአቀራረባቸውም ለውጥ ታይቷል፡፡
የሴቶች ጥበብ በሱሪ ወይም በቦዲ መልክ ማግኘት ይቻላል፡፡ በእራት ልብስ ዲዛይን የሚሠሩ ቀሚሶች ገበያም የደራ ነው፡፡ ለወንዶችም ጥበብ በሸሚዝ፣ በከረባት በኮትና ስካርፍ ይቀርባል፡፡ የአገር ባህል ልብስ ከኢትዮጵያ አልፎ በዓለም አቀፍ መድረክም ተቀባይነት እያገኘ ነው፡፡ እዚህ ላይ እንደ ኒውዮርክ ፋሽን ዊክ ባሉ ዓለም አቀፍ የፋሽን መድረኮች በኢትዮጵያውያን ዲዛይነሮች የተሠሩ ጥበብ ልብሶች ለዕይታ መቅረባቸውን መጥቀስ ይቻላል፡፡ ጥበብ በአገሬው ዘንድ ከበዓል ባለፈ በሠርግ፣ መልስ፣ ምርቃትና ልደትም ይለበሳል፡፡ የኪነ ጥበብ ባለሙያዎች በሽልማት መድረኮችና ሥራዎቻቸውን ሲያስመርቁም በጥበብ ይዋባሉ፡፡
በአጠቃቀም ረገድ መልኩን እየለወጠ የመጣው የአገር ባህል ልብስን በተመለከተ ከሚሰነዘሩ ጥያቄዎች ቀዳሚው የዋጋ ጉዳይ ከሆነ ሰባብቷል፡፡ ጥበብ የሚሸጥበት ዋጋ እንደ አገር ባህል ልብስነቱ ብዙዎች ሊለብሱት የሚያስችል ነው የሚሉ በርካቶች ናቸው፡፡ ልብሶቹን ለማዘጋጀት ከሚወጣው ወጪና ከሚወስደው ጊዜ ጋር ተመጣጣኝ የሆነ ዋጋ እየተጠየቀባቸው ነው ወይ? የሚለውን ማንሳትም ይቻላል፡፡
የአገር ባህል ልብሶች በዘመነኛ መንገድ መምጣታቸው መልካም ሆኖ ሳለ ገበያ ላይ በሚቀርቡበት ዋጋ ስንቶች ያለ ቅሬታ ይገዛሉ? የሚለው አጠያያቂ ነው፡፡ ሰዎች በአቅማቸው መግዛት የሚችሉት ልብስ ከከፍተኛ ዋጋ እስከ ዝቅተኛው ገበያ ላይ ቀርቧል ቢባልም እንደ ሠርግና ማኅበር ባሉ ሁነቶች ተመሳሳይ ጥበብ ማሰፋት ግድ ይሆንና የአንዳንዶችን ኪስ ያስጨንቃል፡፡ የአገር ባህል ልብስ የሚል ስያሜ ተሰጥቶት ሳለ በአገሬው ነባራዊ ሁኔታ ለመግዛት ይቻላልን? የሚል ጥያቄ የሚነሳውም ለዚሁ ነው፡፡
ለምሳሌ በሴቶች ቀሚስ ረገድ ጥበብ እስከ 20,000 ብር ድረስ ይሸጣል፡፡ ዋጋውን ከልብሶቹ የአሠራር ዘዬና ጥራት አንፃር ተመልክተው ተገቢ ነው የሚሉ ቢኖሩም ተገቢ አይደለም የሚሉም አሉ፡፡ የጥበብ ዋጋ ልብሱ ከሚሸጥበት ቦታ አንፃር የሚለያይበት አጋጣሚም አለ፡፡ ቦሌና ሃያ ሁለት አካባቢ ባለውና በሽሮሜዳው የጥበብ ዋጋ ልዩነት አስተውለናል፡፡ ስማቸው በገነነ ዲዛይነሮችና ያልታወቁ ሰፊዎች መካከልም ልዩነቱ ይታያል፡፡
ወ/ሮ አስመረት ግርማይ የጥበብ ዋጋ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየናረ እንደመጣ ይናገራሉ፡፡ አንዳንዶቹ የአገር ባህል ልብሶች በጥራት ተሠርተው ብዙ ዋጋ የሚጠየቅባቸው ቢሆኑም የአብዛኞቹ ልብሶች ዋጋ ተገቢ እንዳልሆነ ይገልጻሉ፡፡ ‹‹በመነን ጨርቅ በሳባ ክር የተሠራ ቆንጆ ጥልፍ ቀሚስ ከ7,000 ብር በታች አይገኝም፡፡ ይህ ከአብዛኞቻችን የመግዛት አቅም በላይ ነው፤›› ይላሉ፡፡ በእሳቸው ገለጻ፣ ጥበብ ልብስ ከኢትዮጵያ ውጪ ያለው ገዥ ማለትም ቱሪስትና ዳያስፖራ ላይ ያነጣጠረ ይመስላል፡፡
ወ/ሮ አስመረት አምና ለልጃቸው ሠርግ በተመጣጣኝ ዋጋ ጥበብ ቀሚስ ለመፈለግ ብዙ መልፋታቸውን ያስታውሳሉ፡፡ ለልጃቸው ሠርግና መልስ ከእህቶቻቸውና የቅርብ ጓደኞቻቸው ጋር ተመሳሳይ ጥበብ ቀሚስ ፈልገው ዋጋ ለማጥናት ያልገቡበት ሠፈር እንደሌለም ይናገራሉ፡፡ የጥበብ ገበያ ተስፋፍቶ በየቦታው ሱቆች መኖራቸውና ከዲዛይን  አንፃርም አማራጭ መኖሩ ጥሩ ቢሆንም ዋጋው መስተካከል አለበት ይላሉ፡፡
ከጥቂት ዓመታት ወዲህ በየአካባቢው በሚገኝ መገበያያ ሕንፃ አንድና ሁለት የባህል ልበሶች መደብር ይገኛል፡፡ በመደብሮቹ የተመልካችን ቀብል የሚስቡ ጥበቦች ስለሚሰቀሉ አላፊ አግዳሚ መለስ ብሎ ያያል፡፡ እነዚህ ልብሶች በጥራት የሚሠሩና ረዘም ላለ ጊዜ የሚያገለግሉ በመሆናቸው ዋጋው ጥያቄ መሆን የለበትም የሚለው ታምራት ዘነበ ነው፡፡ ‹‹ዋጋቸው ውድ የሆኑት ልብሶች የሚሠሩት ደረጃውን በጠበቀ መንገድ ነው፡፡ ከፈትል ጀምሮ ዲዛይን እስከሚደረግ ያሉት ባለሙያዎች በጥራት ይሠሯቸዋል፤›› ይላል፡፡ ጥበብ በአንድ ዓመት ውስጥ እንኳ ጥቂት ቀናት ብቻ ስለሚለበስ ገዥዎች የረዥም ጊዜ አገልግሎት ያገኛሉ ሲልም ይገልጻል፡፡
ጥበብ ስካርፍ 500 ብርና ጥበብ ኮት 5,000 ብር የገዛበትን አጋጣሚ ያስታውሳል፡፡ ወደ ውጪ ለሚሄዱ ሰዎች ስጦታ የ6,000 ብር የአዋቂ ቀሚስና በ4,000 ብር የልጆች ልብስም ገዝቷል፡፡ በእሱ እምነት ልብሶቹ ማማራቸውና ለረዥም ጊዜ የሚቆዩ መሆናቸው የሚሸጡበትን ዋጋ አዋጭ ያደርገዋል፡፡ ሲታጠቡ የሚሳሱና የሚቀዳዱ ልብሶች አነስ ባለ ዋጋ ሊገኙ ይችላሉም ይላል፡፡
ከመደብሮች በተጨማሪ ለኦንላይን ግብይትም የቀረቡ ጥበብ ልብሶች አሉ፡፡ ነጠላ ከ350 እስከ 6,000 ብር ይገኛል፡፡ ጥበብ ቀሚስ ከ60 ዶላር እስከ 550 ዶላር ኢቤይ ላይ ይሸጣል፡፡ የተለያዩ ብሔር ብሔረሰቦች አልባሳት ዋጋ የተለያየ ሲሆን፣ በሸማኔ የተሠራ ጥበብና በፋብሪካ በተሠራ ጨርቅ ላይ የተለጠፈ ጥበብም ይለያያሉ፡፡
 ዛሬ ዛሬ እየተለመደ የመጣው በደማቅ ሳተን ጨርቅ የሚሠራ ቀሚስም ተጠቃሽ ነው፡፡ በሰማያዊ፣ ቢጫ፣ አረንጓዴ ወይም ሌላ ሳተን ጨርቅ ላይ ጥለት ይለጠፋል፡፡ የነጠላ ጫፍ ደግሞ ጥለት ሳይኖረው ከቀሚሱ ጨርቅ ጋር የተመሳሰለ ጨርቅ ይሰፋበታል፡፡ ሳተን ቀሚስ ላይ በክር ጥበብ ተጠልፎ የሚሸጥበትም ጊዜ አለ፡፡ ብዙዎች በሸማኔ የተሠራ የጥጥ ፈትል ጥበብ ልብስ ቢመርጡም ወደዚህኛው የሚያዘነብሉም አሉ፡፡ አንዳንዴ ጥበብ የመልበስ ፍላጎት ቢኖራቸውም ዋጋው አልቀመስ ያላቸው ሰዎች ጥበብን በማስመሰል ወደተሠራው ሳተን ሳይወዱ በግድ ፊታቸውን ሲያዞሩ ይታያል፡፡
ሮዛ ይርጋ በሳተን ጨርቅ የተሠራ ቀሚስ በ2,500 ብር የገዛችው በቅርብ ነው፡፡ ከዚያ በፊት ለተለያዩ በዓሎች የሸማ ጥበብ ቀሚስ ከ2,500 ብር እስከ 4,000 ብር ገዝታለች፡፡ ‹‹የጥበብ ገበያ ሁሉም ሰው በአቅሙ የሚገዛበት ነው፤›› ትላለች፡፡ ብዙ ጊዜ ጥበብ ከሽሮሜዳ እንደምትገዛ የምትገልጸው ሮዛ፣ በተመጣጣኝ ዋጋ የሸመተቻቸው ቀሚሶች ዕድሜ እንዳላቸውም ትናገራለች፡፡ በባለሙያዎች የተፈተለ ጥበብና በፋብሪካ የተሠራ ጨርቅ ላይ የተጠለፈ መካከል የዋጋ ልዩነት እንዳለና ሰው እንደ ምርጫው መግዛት እንደሚችልም ታስረዳለች፡፡ በእርግጥ የዋጋው ልዩነት ጠቦ ሰው ጥራት ያለው ልብስ ቢገዛ ይመረጣል፡፡ ከአገሪቱና ከሕዝቡ ነባራዊ ሁኔታ አንፃር ታስቦ ዋጋው ቢተመንም መልካም ነው፡፡
‹‹በቀለም የተነከረ ወይም በሳባ፣ በሱፍ ወይም በሹራብ ክር የሚሠራው ልብስ መካከል ሰፊ ልዩነት አለ፡፡ እንደየሥራቸው ዋጋቸውም ይለያያል፤›› ትላለች፡፡ ሮዛ ከሠርግና ከምርቃት በተጨማሪ ለበዓልና ከበዓል በኋላ ባሉ ቀናትም ሥራ ቦታዋ ላይ ጥበብ ለብሳ ትገኛለች፡፡ መካከለኛ ገቢ ያላት ሲሆን፣ ለጥበብ የምታወጣው ወጪ ከሌሎች ልብሶቿ ቢበልጥም፣ ኪሷን እንዳልጎዳው ትናገራለች፡፡ እሷ ጥሩ በምትለው ዋጋ ከምትገዛቸው ልብሶች ጋር የሚመሳሰሉ ልብሶች በውድ ዋጋ የሚሸጡባቸው አካባቢዎች እንዳሉም ታክላለች፡፡ ‹‹በጥራታቸው መካከል ልዩነት የለውም፡፡ አንዳንዴ የሞል ኪራይ ለመክፈል ልብሶቹ ላይ ዋጋ የሚጨምሩ ነጋዴዎች አሉ፤›› ትላለች፡፡
ከዓመታት በፊት ጥበብ በ200 እና 300 ብርም ይሸጥባቸው የነበሩ እንደ ሸማ ተራ ባሉ አካባቢዎች ዛሬ 1,000 ብርና ከዚያም በላይ ይጠራባቸዋል፡፡ ከጊዜ ወደ ጊዜ ምርቶች ላይ የሚደረገው የዋጋ ጭማሪ ጤናማ ቢሆንም፣ የጥበብ ልብሶች ዋጋ ጉዳይ አሳሳቢ እንደሆነ የሚገልጹ አሉ፡፡ የልብሶቹ ዋጋ የጨመረው ጥራት ስላላቸውና ዘመነኛ ገጽታ ስለተላበሱ ነው በሚለው የሚስማሙና የማይስማሙም አሉ፡፡
አንድ ያነጋገርነው አባት፣ ‹‹ሁለት ልጆቼ የብሔር ብሔረሰቦችን በዓል ትምህርት ቤት ሲያከብሩ የጉራጌና የራያ ልብስ ለመግዛት ከ800 ብር በላይ አውጥቻለሁ፤›› ይላል፡፡ አንዲት እናት ለልጇ ልደት ቤተሰባቸው ተመሳሳይ ጥለት ያለው ልብስ እንዲለብስ አስባ ለሷ፣ ለልጇና ለባለቤቷ ወደ 4,000 ብር ማውጣቷን ትገልጻለች፡፡ ሁለቱም አስተያየት ሰጪዎች ‹‹አማራጭ የለም›› ነበር ያሉት፡፡
የእንቁ ዲዛይን መሥራች ዲዛይነሯ እንቁጣጣሽ ክብረት፣ የጥበብ ዋጋ እንደየዲዛይኑ ቢለያይም ሁሉም የገዥ አቅም ያገናዘበ እንደሆነ ትገልጻለች፡፡ ‹‹ሸማኔ፣ ጠላፊ፣ ዲዛይነርና ሰፊ እንደሚወስድባቸው ጊዜና እንደ ልብሱ አሠራር ረቂቅነት ዋጋው ይተመናል፤›› ትላለች፡፡ እስከ ሁለት ወር የሚወስዱና ዲዛይናቸው ከባድ የሆኑ ልብሶች እስከ 20 ሺሕ ብር ይሸጣሉ፡፡ ዲዛይነሯ እንደምትለው፣ ከባለሙያዎች ድካም አንፃር ከተማው ላይ ያለው የአገር ባህል ልብስ ዋጋ ተገቢ ነው፡፡ በተለይም ለሠርግና ለበዓላት ጥበብ የሚያሠሩ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ እንደሆነም ትናገራለች፡፡
እንቁጣጣሽ የባህል ልብሶችን ለገበያ የምታቀርበው በተለያየ ፓኬጅ ሲሆን፣ እናትና ልጅ ኮሌክሽን እንዲሁም ቤተሰብ ኮሌክሽን የሚሉ አማራጮች አሏት፡፡ እንደ ቤተሰቦች ብዛት ከ6,000 ብር ጀምሮ እስከ 15,000 ብር ይሸጣል፡፡ የሙሽራ ልብስ ከ5,000 እስከ 20,000፣ የሚዜና ሌሎች ተጠሪዎች ልብስ ከ3,500 ብር ጀምሮ ይገኛል፡፡
ዲዛይነሯ ዘርፉን ከጥበብ ዋጋ በተጨማሪ ከተደራሽነት አንፃርም ታየዋለች፡፡ የባህል ልብስን ከበዓላት ውጪ የሚለብሱ ሰዎች ቁጥር ባይጨምርም፣ የኢትዮጵያውያን ዲዛይነሮች ልብሶች ዓለም አቀፍ ዕውቅና ማደጉን ትገልጻለች፡፡ በተቃራኒው የፋሽን ዝግጅት የሚያሰናዳው ሰለሞን ጌታቸው (ሶሎቢ) የጥበብ ዋጋ የገዥዎችን አቅም ያገናዘበ አይደለም ከሚሉት ወገን ነው፡፡ የጥበብ ዋጋ አሁን ባለበት አካሄድ ከቀጠለ ለወደፊት የገዥዎች ቁጥር እንደሚቀንስ ይናገራል፡፡
በከፍተኛ ዋጋ እየተሸጡ ካሉት ልብሶች አብዛኞቹ ከባህላዊ የጥበብ አሠራር መንገድ ያፈነገጡ መሆናቸውንም አይቀበለውም፡፡ ከሱ ጋር ተመሳሳይ አስተያየት ያላቸው ሰዎች በዋነኛነት በሳተን ጨርቅ የሚሠሩ ልብሶችና የትኛውንም የኢትዮጵያ አካባቢ የማይወክሉ ልብሶችን የአገር ባህል ልብስ ብሎ ለመጥራት አይቻልም ይላሉ፡፡ ሰለሞን እንደሚለው፣ ደረጃውን የጠበቀ ሥራ የሚያቀርቡ ብዙ ዲዛይነሮች ገበያውን ቢቀላቀሉም፣ የልብሶቹ መወደድ ዘርፉ እንዳያድግ አግዶታል፡፡ አንዳንድ ጥበብ ልብሶች የሚጠየቅባቸው ዋጋ ከአንድ ኢትዮጵያዊ አማካይ ገቢ አንፃር ለወራት አስቤዛ ሊያሸምቱም ይችላሉ፡፡
የባህል ልብስ በየትኛውም የኢኮኖሚ ደረጃ ያለውን ማኅበረሰብ ታሳቢ ያደረገ መሆን እንዳለበት ያምናል፡፡ የአገር የሚል መጠሪያ ያለው ልብስ ጥቂቶች ብቻ መምሰሉን አያይዞ ያነሳል፡፡ ጥሩ ስም ያላቸው ዲዛይነሮች እስከ 15,000 ብር ሲያስከፍሉ ሽሮ ሜዳ ወደ 3,000 ብር ገደማ ዋጋ የሚጠራው እንደቀላል ነው፡፡ ጥበብ ጠቀም ያለ ገቢ ካላቸው ሰዎች ውጪ የማይቀመስ መሆኑንም በአጽንኦት ይገልጻል፡፡
ብዙዎች ለሠርግ ወይም ለሌላ መርሐ ግብር ሲባል ግዴታ ካልሆነባቸው በስተቀር ጥበብ ለመግዛት እንደማይደፍሩም ያክላል፡፡ በባህላዊ ልብሶች አሠራርና በሚሸጡት ዋጋ ረገድ ቁጥጥር ቢደረግ ለውጥ እንደሚመጣ ያምናል፡፡
የአገር ባህል ልብስ በስፋት መቅረቡ፣ በብዙዎች ይመረጥና ይለበስ ዘንድ በተለያየ ዲዛይን መቅረቡ እሰየው የሚያስብል ቢሆንም ይህ በአቅርቦት፣ በጥራትና በተሻለ ዲዛይን እየቀረበ ያለ የአገር ባህል ልብስ ዋጋ ሰማይ እየነካ መሄድ የአገር ባህል ልብስ ሆኖ መቀጠል መቻሉን ጥያቄ ውስጥ ይከታል፡፡ ልብሱን ማድረግ የሚችለው ሰፊው ሕዝብ አገሬው መሆኑ ቀርቶ የውጭ አገር ዜጎችና ዳያስፖራው ከሆነ፤ ሰፊው ሕዝብ ከዲዛይንና ከጥበብ አንፃርም፣ በእውነተኛው ጥበብ ፋንታ የሚጠለፈውን፣ ከውጭ የሚገባውን ጥለት መሰል ጨርቅና ሸማ ሳይሆን ሳተንን ወደ መምረጥ (ተገዶም ቢሆን) መሄድ የብዙዎች ጭንቀት ሆኗል፡፡


በዓለ ጥምቀት በዝዋይ ሐይቅ

21 Jan, 2017
ዓመታዊው የጥምቀት በዓል ከተከበረባቸው ቦታዎች መካከል በዝዋይ ሐይቅ ውስጥ የሚገኙት ገዳማት ይጠቀሳሉ፡፡ ከአዲስ አበባ 161 ኪሎ ሜትር ርቀት በምትገኘው ዝዋይ (ባቱ) ከተማ ዳርቻ፣ ባለው ሐይቅ የሚገኙት አቡነ ተክለሃይማኖት፣ ቅዱስ ሚካኤል፣ ደብረ ጽዮን ቅድስት ማርያም፣ አርባዕቱ እንስሳትና ፀዴቻ አቡነ አብርሃም ገዳማት ጥር 10 እና 11፣ 2009 ዓ.ም. በዓሉን አክብረዋል፡፡ ከአምስቱ ገዳማት አቡነ ተክለሃይማኖትና ደብረ ጽዮን ከደሴታቸው በመውጣት ሦስት ኪሎ ሜትር የሚሆነውን የሐይቁን ክፍል አቋርጠው ምድር ላይ በማክበር ብቸኛ ያደርጋቸዋል፡፡ የተቀሩት ሦስቱ ደግሞ ከሐይቁ ዳር በጣም የራቁ በመሆናቸው ከቤተ መቅደሳቸው በመውጣት በግቢያቸው የሐይቁ ጠርዝ ላይ ድንኳን በመጣል እዚያው አክብረዋል፡፡ (ፎቶ በታምራት ጌታቸው)

ከተራ በቦሌ

የጥምቀት በዓልን በዩኔስኮ የማስመዝገብ ማመልከቻ - በሁለት ወር ውስጥ ከቀረበ በኅዳር 2011 ዓ.ም. ውሳኔ ይሰጥበታል-- ካልቀረበ ኅዳር 2012ን ይሻገራል
በባሕር ማዶ ‹‹የአፍሪካው ኤጲፋኒያ›› (African Epiphany) በመባል በልዩ ልዩ ድርሳኖች የሚታወቀው የጥምቀት በዓልን በዩኔስኮ (የተባበሩት መንግሥታት የትምህርት፣ የሳይንስና የባህል ድርጅት) በሰው ልጅ ወካይ የማይዳሰስ ባህላዊ ቅርስነት ለማስመዝገብ ባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር በይፋ እንቅስቃሴ መጀመሩን አብስሯል፡፡
ዓመታዊው ክብረ በዓል በአገሪቱና የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን በምትገኝበት የዓለም ክፍሎች ጥር 11 ቀን 2009 ዓ.ም. ተከብሯል፡፡ በተለይ በአዲስ አበባ በጃንሜዳ ሲከበር በሥነ በዓሉ ላይ የተገኙት አዲሷ የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር ዶ/ር ሒሩት ወልደማርያም እንዳበሰሩት፣ የጥምቀት በዓልን በዩኔስኮ ለማስመዝገብ ቅድመ ዝግጅት እየተደረገ ነው፡፡ ሚኒስትሯ አያይዘውም የጥምቀት በዓል ‹‹ከጥንት ጀምሮ የሰላምና የፍቅር ተምሳሌት በመሆን የሚከበር፣ የኩራታችንና የማንነታችን መገለጫ ሃይማኖታዊ በዓል ከመሆኑ ባሻገር የበርካታ ባህላዊ እሴቶች ማሳደጊያ ነው፤›› ሲሉ፣ ቡራኬ የሰጡት ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ወፓትርያርክ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊም፣ ‹‹በዓለ ጥምቀቱ የኢትዮጵያ ሕዝቦች አንድነት መጠበቂያ ጠንካራ ዘዴ በመሆኑ ኢትዮጵያውያኑ ሊጠብቁትና ለዓለም ሊያስተዋውቁት ይገባል፤›› ብለዋል፡፡
ዋዜማውን ከተራ (ጥር 10) እና ማግስቱን (ጥር 12) ቃና ዘገሊላን ይዞ በዓለ ጥምቀት በልዩ ድምቀት ከሚከበርባቸው አካባቢዎች አንዱ በሆነውና ጎንደር ከተመሠረተችበት ከ17ኛው ምታመት ጀምሮ በልዩ አገባብ እየተከበረ ያለውን ሒደት ለመሰነድ የቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለሥልጣን ባለሙያዎች ቡድን ሥራውን እያከናወነ ይገኛል፡፡ የጥናት ቡድኑ አስተባባሪና የባህል አንትሮፖሊጂስቱ አቶ ገዛኸኝ ግርማ ለሪፖርተር እንደገለጹት ቡድኑ ከጥር 1 ቀን 2009 ዓ.ም. ጀምሮ በሥራ ላይ ነው፡፡
እንደ አቶ ገዛኸኝ አገላለጽ፣ በጎንደር ከሚሰነደው አከባበር በተጨማሪ በቤተክህነት አማካይነት በተለያዩ አካባቢዎች በየባሕረ ጥምቀቱ የሚኖረውን ሥርዓት ስነዳ ይከናወናል፡፡ የማስመረጫ ሰነዱ ለዩኔስኮ የሚላክ ሲሆን፣ እ.ኤ.አ. ለ2018 በዕጩነት ለማቅረብ እስከ መጋቢት 22 ቀን 2009 ዓ.ም.¸ሰነዱን አሟልቶ መላክ ይጠበቃል፡፡
በዓለ ጥምቀቱ ሲገለጽ
በኦርቶዶክሳዊቷ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን የሚከበረው የጥምቀት በዓል፣ እግዚእ ኢየሱስ ክርስቶስ በ30 ዓመቱ በመጥምቁ ዮሐንስ እጅ በዮርዳኖስ ባሕር የተጠመቀበትን ዕለት የሚያስታውስ ነው፡፡ ‹‹ኤጲፋንያ›› በመባልም ይታወቃል፡፡ ጥር 10 ቀን በከተራ፣ በገጠርም ሆነ በከተማ ታቦታት ከየአብያተ ክርስቲያናቱ ወደየባሕረ ጥምቀቱ የሚያደርጉት ጉዞና መንፈሳዊ አዳር በማግስቱ የጥምቀት ዕለት ‹‹ተጠምቀ ሰማያዊ በእደ መሬታዊ፤›› ሰማያዊው በመሬታዊው እጅ ተጠመቀን ይዞ የሚኖረው ያሬዳዊ ዝማሬ የበዓሉ ገጽታ ነው፡፡
ሥዕላዊ ከሆነው ከሃይማኖታዊና መንፈሳዊ አከባበሩ በተጓዳኝም ባህላዊ ገጽታው ይታያል፡፡ ወጣቶች የሚተጫጩበት የትዳር አጋራቸውን የሚመርጡበት አጋጣሚዎችን ከመፍጠሩም ባለፈ በከተማም ሆነ በገጠር ሰውን የሚያገናኝ ድልድይ ነው፡፡
በየዓመቱ በመላ ኢትዮጵያ የሚከበረው የጥምቀት በዓል፣ ታቦታት ከመንበራቸው ወጥተው፣ በየባሕረ ጥምቀቱ የሚከበሩ በመሆናቸው፣ አገሬውን ብቻ ሳይሆን ዓለም አቀፋዊ መስህብነትን በመጎናጸፉ፣ ቱሪስቶችን እንደሳበ ነው፡፡ ከአዲስ አበባ እስከ ላሊበላ፣ ከአክሱም እስከ ጎንደር፣ ከሐዋሳ እስከ ጂማ፣ ከአሶሳ እስከ ጋምቤላ በሁሉም ሥፍራዎች በዚሁ ዓይነት ደምቆ ይከበራል። የምእመናኑም ሆነ የካህናትና ዲያቆናት አለባበስ ፍፁም በሚማርክ ባህላዊ አልባሳት የተዋበ በመሆኑ ከውጭም ሆነ ከአገር ውስጥ ለሚመጡ ጎብኚዎች ሁልጊዜ አዲስ ነው።
ከሃይማኖታዊው ሥነ ሥርዓት በኋላ ካህኑ በሃሌታ፣ ወንዱ በሆታ፣ ሴቱ በእልልታ ታቦተ ሕጉን አጅበው፣ እንደያመጣጣቸው ወደየአጥቢያቸው ይመለሳሉ።
‹‹እዩት ወሮ ሲመለስ
መድኃኔ ዓለም በፈረስ
ወሮ ሲመለስ
የሚካኤል አንበሳ
ሎሌው ሲያገሳ።
ማር ይፈሳል ጠጅ
በእመቤቴ ደጅ፤» እያሉ ምእመናኑ ታቦታቱን በዝማሬቸው ያጅቡታል።
ታቦተ ሕጉም ቅጽር ግቢው ሲደርስ ሁሉም ምኞታቸውን በፍሡሕ ገጽ እንዲህ እያሉ ይገልጻሉ።
«በሕይወት ግባ በዕልልታ
የዚህ ሁሉ አለኝታ
በሕይወት ግቢ እምዬ
እንድበላ ፈትዬ››
ሊቃውንቱ እንደሚናገሩት፣ ዘመነ አስተርእዮ የሚባለው፣ ከጥር 11 ቀን ጀምሮ እስከ ጾመ ነነዌ (ለዘንድሮ እስከ ጥር 28 ቀን 2009 ዓ.ም.) ያለው ጊዜ ነው። በዚህ ጊዜ ውስጥ አምላክ ሰው ሆኖ በሥጋ መገለጡ፣ በዮርዳኖስ በተጠመቀ ጊዜ የአንድነትና የሦስትነት ምሥጢር መታወቁ፣ በቃና ዘገሊላ በተደረገው ሠርግ ላይ የመጀመሪያው ተዐምር በመፈጸሙ፣ አምላካዊ ኃይሉ መገለጡ፣ እየታሰበ ምስጋና ይቀርባል። ይህ ኩነት ኢትዮጵያ ብሂልን ከባህል ጋር አዛምዳ ከሌላው የክርስቲያን ዓለም በተለየ አከባበር በዓሉን ማክበሯ፣ አያሌ ቱሪስቶችን ለመሳብ አስችሏታል።
ያኔ የሎሚ ውርወራው፣ የከተራው ሽልምልም ዱላ አሁን አሁን በከፊል ሎሚው ወደ ፕሪም፣ ሽልምልሙ ዱላ ወደ ረዥም ቄጠማ (ጨፌ ላይ የሚበቅል) ተለውጦ መታየቱ፣ ከባህላዊ ጭፈራው በተጓዳኝ ወጣቱ በአመዛኙ ከመንፈሳዊ ማኅበራት (ሰንበት ትምህርት ቤቶች) መዘምራን ጋር ወደ ዝማሬ አዘንብሏል፡፡
በዓለም አቀፍ የፌስቲቫሎች መድበል የአፍሪካ ኤጲፋኒያ/ጥምቀት (The African Epiphany) እየተባለ የጎንደሩ፣ የላሊበላው፣ የአዲስ አበባው… የጥምቀት አከባበር በዓለም የክብረ በዓላት (Festivals) ድርሳን ላይ በየጊዜው የሚተዋወቀው፣ ቱሪስቶችም እየመጡ የሚያደንቁት አንዳንዶችም ‹‹ጥምቀትን ለምን በቅርስነት አላስመዘገባችሁም?›› እያሉ ሠርክ እየጠየቁ ባሉበት፣ የቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለሥልጣን ለከተራ ጥምቀት አከባበር ምዝገባ ለዓመታት ትኩረት ሳይሰጥ መክረሙ ይነገራል፡፡
በ2006 ዓ.ም. የጥምቀት በዓል በአዲስ አበባም ሆነ በጎንደር ሲከበር የቤተክህነትም ሆነ የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ከፍተኛ ሹማምንት ክብረ በዓሉን በዓለም ቅርስነት ለማስመዝገብ እየሠራን ሲሉ ቢደመጡም፣ በተግባር ግን የሚታይ እንቅስቃሴ እንዳልነበረ ገሐድ ነበር፡፡ ዘንድሮ ግን ተግባራዊ እንቅስቃሴ መጀመሩ ይበል አሰኝቷል፡፡
የጥምቀት በዓል በዩኔስኮ በግዙፍ ቅርስነት ከተመዘገቡት ከአክሱም፣ ላሊበላ የጎንደሩ ፋሲል ግቢ ጋር በጥብቅ ተሳስሮ የሚከበር የማይዳሰስ ባህላዊ ቅርስ መሆኑ፣ እንዲሁም በዓሉ ከ1,500 ዓመታት በላይ በተከታታይ የአገሪቱ ትውልዶችና ሥልጣኔዎች እየተከበረ ያለ ሕያው ቅርስ መሆኑ ይታወቃል፡፡
በዓሉ መቼ ይመዘገብ ይሆን?
ኢትዮጵያ እስካሁን ሦስት የማይዳሰሱ ቅርሶቿን (የመስቀል በዓል፣ ፊቼ ጫምባላላና የገዳ ሥርዓት) በዩኔስኮ አስመዝግባለች፡፡ የገዳ ሥርዓት ባለፈው ኅዳር አዲስ አበባ በተደረገው ጉባኤ መመዝገቡ ይታወሳል፡፡
ኢትዮጵያ ለዘንድሮው 2017 ለዩኔስኮ ያቀረበችው አንድም የማይዳሰስ ባህላዊ ቅርስ የለም፡፡ ስምንት የአፍሪካ አገሮች አልጀሪያ፣ ማላዊ፣ ቦትስዋና፣ አይቮሪኮስት፣ ግብፅ፣ ሞሮኮ፣ ናይጄሪያና ሞሪሸስ እንዲመረጡላቸው የተለያዩ ባህላዊ ቅርሶችን ማቅረባቸው ዩኔስኮ ይፋ አድርጓል፡፡ ከነዚህም መካከል ቦትስዋና ዶኮፔሎ የሚሰኘውን ባህላዊ ሙዚቃ፣ ግብፅ የላዕላይ ግብፅን የታሊ ዕደ ጥበብና ሥነ ጥበብ፣ ማላዊ ባህላዊ ምግቧን፣ ናይጄሪያ የዮሩባን ቃል ግጥም ይገኙባቸዋል፡፡
በመጪው ኅዳር 2010 ዓ.ም. በሚደረገው የዩኔስኮ የዘርፉ ኮሚቴ ጉባኤ ለውሳኔ እንዲታይላቸው ማመልከቻቸውን ያስገቡት በሕገ ደንቡ መሠረት ማርች 31 ቀን 2016 (መጋቢት 22 ቀን 2008 ዓ.ም.) ነበር፡፡
ኢትዮጵያ ለመወዳደር ያለፋትን ዘንድሮ (2017)፣ በ2018 (2011 ዓ.ም.) ለማግኘት ዕድል የሚኖራት የጥምቀት በዓልን እንዲመዘገብ የሚያስችለውን የኖሚኔሽን ሰነዷን አዘጋጅታ እስከ መጋቢት 22 ቀን 2009 ዓ.ም. (ማርች 31 ቀን 2017) በፓሪስ ሰዓት አቆጣጠር እስከ እኩለ ሌሊት ስትልክ ብቻ ነው፡፡
በሁለት ወር ውስጥ የመጀመሪያውን ተግባር ካላከናወነች ማመልከቻው የሚገባው ባመቱ መጋቢት 22 ቀን 2010 ዓ.ም. (ማርች 31 ቀን 2018) ሲሆን፣ ውሳኔውም በሦስተኛው ዓመት ኅዳር 2012 ዓ.ም. ይከናወናል፡፡


Tuesday, January 17, 2017

ዕፀ በለስ እንደ ገና ዛፍ

13 Jan, 2017 
የገና በዓል መገለጫ ከሆኑት አንዱ ዛፍ ነው፡፡ ቀደም ሲል ጥድ እየተቆረጠ በልዩ ልዩ ማሸብረቂያዎች ይዋብ ነበር፡፡ አሁን አሁን አርቲፊሻል ዛፎች በየቦታው ነግሰው ይታያሉ፡፡ በዘንድሮው ገናም በተለያዩ ከተሞች በየአደባባዩ በየመደብሩ ደጃፍ ተተክለው እየታዩ ነው፡፡ ከሕፃን እስከ አዋቂ ፎቶ ሲነሱበትም ነበር፡፡ በመቐለ ከተማ ጅብሩክ አካባቢ በሚገኘው ወዲ መሸሻ ሕንፃ የቆመው አንዱ ነው፡፡ በድረ ገጽ ውስጥ የተገኘው የገና ዛፍ ደግሞ በበለስ ዛፍና ፍሬው የተዋበ ነው፡፡ በሥነ ቃል የሚባለውን ‹‹ዕፀ በለስ በልቶ ሔዋን ከንፈርሽ፣ መድኃኔ ዓለም ልቤ ተሰቀለልሽ››ን ያስታውሳል፡፡

አዲሱ የትግራይ ቋንቋዎች አካዴሚ20 Jul, 2016 By ሔኖክ ያሬድ  Comments
በትግራይ ብሔራዊ ክልል በሚገኙ ሦስት ቋንቋዎች ሳሆ (ኢሮብ) ኩናምኛና ትግርኛ ዙርያ በተለያዩ የቋንቋና ባህል ዘርፎች ሳይንሳዊ ጥናቶች የሚያከናውን፣ ቋንቋዎቹም የሳይንስና ቴክኖሎጂ ጽንሰ ሐሳብ የመግለጽ አቅም እንዲኖራቸው የሚያስችል የትግራይ ቋንቋዎች አካዴሚ ሥራውን ባለፈው ኅዳር ወር ጀምሯል፡፡ አካዴሚው በክልሉ ምክር ቤት በአዋጅ ቁጥር 249/06 መሠረት ያቋቋመው 2006 .. ነበር፡፡ አካዴሚው ሐቻምና ከመቋቋሙ በፊት 1988 .. ያለ አዋጅ ተቋቁሞ በሥራ ላይ ከአንድ ዓመት ከመንፈቅ በላይ ማለፍ አልቻለም፡፡ ዘንድሮ እንደ አንድ መንግሥታዊ አካል በተለይም ለክልሉ ርእሰ መስተዳደር ተጠሪ ሆኖ፣ ዳግም የተቋቋመው የትግራይ ቋንቋዎች አካዴሚን በዋና ዳይሬክተርነት የሚመሩት / ዳንኤል ተኽሉ ናቸው፡፡ በተግባራዊ ሥነ ልሳንና ግንኙነት (አፕላይድ ሊንጉስቲክስና ኮሙዩኒኬሽንስ) የዶክትሬት ዲግሪ ያላቸው / ዳንኤል፣ ከትግርኛ ቋንቋና ባህል እንዲሁም ሥነ ጽሑፍ ጋር የተያያዙ 19 መጻሕፍት አሳትመዋል፡፡ ከነዚህም መካከል የትግርኛ እንግሊዝኛ፣ የእንግሊዝኛ ትግርኛ መዛግብተ ቃላት፣ የሰዋስው (ግራመር) የሥነ ጽሑፍና የሥነ ግጥም፡፡ የሥነ ቃልና የሕፃናት መጻሕፍት ይገኙባቸዋል፡፡ 1,300 በላይ ገጾች ያሉት የትግርኛ በትግርኛ መዝገበ ቃላትም አዘጋጅተዋል፡፡ የሕትመቱን ብርሃን እየጠበቀ ነው፡፡ በአካዴሚው እንቅስቃሴ ዙሪያ ዋና ዳይሬክተሩን / ዳንኤልን ሔኖክ ያሬድ አነጋግሯቸዋል፡፡
ሪፖርተር፡- የአካዴሚው ምሰሶዎች ምንድን ናቸው?
/ ዳንኤል፡- አካዴሚው የተቋቋመበት መሠረታዊ ነገሮች አሉት፡፡ አንደኛው መነሻ ሦስቱ ቋንቋዎች የሳይንስና የቴክኖሎጂ ቋንቋዎች እንዲሆኑ ስለተፈለገ ነው፡፡ ዘመኑ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ቋንቋ ነውና ለኅብረተሰቡ በሌሎች ቋንቋዎች ጽንሰ ሐሳቡን አምጥተህ ሊረዳ አይችልም፡፡ ጽንሰ ሐሳቦቹን ተረድቶ ተግባራዊ ሊያደርግ፣ ሕይወቱንም የሚያሻሽልበት ሁኔታ ለማመቻቸት አይችልም፡፡ ስለዚህ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ጽንሰ ሐሳቦች በራሱ ቋንቋ ከቀረበለት ይበልጥ ተጠቃሚ ሊሆን ይችላል፡፡ ሌላው በተለያዩ ምክንያቶች እነዚህ ቋንቋዎች የተጎዱ ነበር ማለት ይችላል፡፡ በመማር ማስተማር ላይ አልነበሩም፡፡ በተለይ ሳሆኛና ኩናምኛ ስንወስድ፡፡ ትግርኛም ቢሆን የቅርብ ጊዜ ታሪክ ነው ያለው፡፡ አንዳንድ ጊዜ ገባ ወጣ ያለበት ሁኔታ ቢኖርም ኅብረተሰቡን ሙሉ በሙሉ ለማገልገል ብቃት እያለው ሳይሆን የቀረበት ነው፡፡ ቋንቋዎቹ ሳይንሳዊ በሆነ መንገድ በሰዋስውም ሆነ በሌሎች ዘርፎች ተጠንተው አገልግሎት በሚሰጡባቸው አካባቢዎች ያሉ ክፍተቶች ለመሙላት ታስቦ አካዴሚው ተቋቁሟል፡፡
ሌላው ከዚሁ ጋር በተያያዘ መልኩ የተወሰኑ ጥረቶች ቢኖሩም በቋንቋዎቹ ዙርያ የተለያዩ መዛግብተ ቃላት የሉም፡፡ ስለዚህ ይሄ አካዴሚ በዋናነት እነዚህ ነገሮች ይዞ ለመሥራት ተነስቷል፡፡ ቋንቋዎቹ በፍትሕ፣ በትምህርት፣ በሚዲያ እንዲሁም በጽሕፈት ቤት እየተገለገልንባቸው ቢሆንም ክፍተቶች ስላሉ ችግሮቹ በጥናት ተለይተው ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ሆነን መፍትሔ የምንሻበት አጋጣሚው ይፈጠራል ብለን እናስባለን፡፡
ሪፖርተር፡- ብዙ ጊዜ በቋንቋዎቻችን ላይ እንደ ክፍተት የሚነሳው ጥያቄ ሰዋስውን (ግራመር) የተመለከተ ነው፡፡ ተጠቃሚዎች በአግባቡ አይጠቀሙም ይባላል፡፡ በክልሉ ያሉት ሦስት ቋንቋዎች ከሰዋስው ጥናት ጋር ያላቸው ቁርኝት እንዴት ይገለጻል?
/ ዳንኤል፡- ከሦስቱ ቋንቋዎች ሰዋስውን በተመለከተ በደንብ ተጠንቷል ብለን የምናስበው ትግርኛ ላይ የተሠሩትን ነው፡፡ ፈረንጆችም የተወሰነ ሒደውበታል፡፡ ርሱ በቂ ላይሆን ይችላል፡፡ ሳሆ አካባቢ የተወሰኑ ጥረቶች አሉ፡፡ ኩናምኛ ግን ብዙ ነገር ይቀረናል፡፡ አካዴሚው ሲቋቋም ዓላማዬ ካላቸው አንዱ የሦስቱ ቋንቋዎች ሰዋስው በስፋት በሳይንሳዊ መንገድ እንዲጠና ማስቻል ነው፡፡ አጠቃቀም ላይ ስንመጣ ጽሑፍና ንግግር ብለን ብንለየው የተሻለ የሚሆን ይመስለኛል፡፡ በርግጥ አንዳንድ ጊዜ የምንናገረውን ስለምንጽፈው ችግር አለ፡፡ የምንናገረው ደግሞ በቃላቱ፣ በሰዋስው፣ በዕርባታው በሌሎች ቋንቋዎች የተበረዘ ነው፡፡ ለምሳሌ በመዋቅሩ ትግርኛ በአማርኛ የሚዘነበልበት (ዶሚኔት የሚደረግበት) ሁኔታ አለ፡፡ የተጻፉ መጻሕፍት፣ የተሠሩ ጥናቶች ቢኖሩም በመማር ማስተማር ሒደት፣ በሚዲያና በመሥሪያ ቤቶች አካባቢ ውጥንቅጥ አካሄድ ነው ያለው፡፡ ስለዚህ የግንዛቤ ችግር የፈጠረው መሆኑን ተረድተን በሒደት የምናስተካክለው ይሆናል፡፡ ችግሩና ክፍተቱ በሰዋስው ብቻ አይደለም፡፡ ትግርኛ የመግለፅ ብቃቱ የለኝም ሳይል የትግርኛ ቃላትን እየተውን ቃላትን እየቀላቀልንና በሌሎች እየተካን ነው፡፡ በሳሆና በኩናምኛም ተመሳሳይ ነገር አለ፡፡ ስለዚህ እነዚህን መሠረታዊ ችግሮች ለመፍታት አካዴሚው የራሱ የሆነ ሚና ይኖረዋል፡፡
ሪፖርተር፡- አደረጃጀቱ እንዴት ነው?
/ ዳንኤል፡- አካዴሚው ተጠሪነቱ ለክልሉ ፕሬዚዳንት ነው፡፡ አደረጃጀቱም በውስጡ ሦስት ክንፎች አሉት፡፡ አንደኛው ክንፍ የሰዋስውና የመዛግብተ ቃላት ጥናት ነው፡፡ ሁለተኛው ሥነ ቃል፣ ሥነ ጽሑፍና ትርጉም የሚል ሲሆን ሦስተኛው የፋይናንስ ዘርፍ ሆኖ ተዋቅሯል፡፡ እያንዳንዱ ዘርፍ በተለይ በሥነ ጽሑፍና በሥነ ልሳን አካባቢ የሦስቱም ቋንቋዎች ክፍሎች ይኖራሉ፡፡ በሥነ ቃልና በትርጉምም እንዲሁ፡፡ አደረጃጀቱ ለጊዜው እንጂ ቋሚ ላይሆን ይችላል፡፡ ምክንያቱም የሰው ኃይሉ ታይቶም በቢፒአር ጥናት መሠረት ሊሰፋ ይችላል፡፡
ሪፖርተር፡- በባህልና ቱሪዝም ቢሮ ተመሳሳይ ሥራ እየተሠራ ነው፡፡ ተደራራቢነት አይኖርም? መተሳሰርስ ይኖራል?
/ ዳንኤል፡- በባህልና ቱሪዝም ቢሮ በቋንቋ ጉዳይ፣ በሥነ ቃልና በመዛግብተ ቃላት ላይ የሚሠሩ ባለሙያዎች አሉ፡፡ ይኸ ማለት ያለ መናበብ ችግር ይፈጥራል ወደሚል የሚወስድ አይመስለኝም፡፡ ከዚያም በተጨማሪ በአዲስ አበባ፣ በመGለና በዓዲግራት ዩኒቨርሲቲዎች፣ በዓድዋና በዓቢይ ዓዲ የመምሀራን ትምህርት ኮሌጆች የትግርኛ ትምህርት ክፍል አለ፡፡ የትግራይ ባህል ማኅበርም በጠቀስናቸው ዘርፎችም ይሠራል፡፡ መንግሥት እነዚህን እንቅስቃሴዎች አድንቋል፡፡ ግን አካሄዳቸው የተበተነ በመሆኑ አካዴሚው እንዲመሠረት ትልቅ መነሻ የሆነው እነዚህ በተለያዩ ቦታዎችና ባለሙያዎች የሚደረጉ ጥረቶች በማማከል እየተናበቡ እንዲሄዱ ለማመቻቸት ነው፡፡ አብረን ነው የምንሠራው፡፡ አካዴሚው በማስተባበርና በመምራት ሙሉ ድርሻ ይኖረዋል ብለን እናስባለን፡፡
ሪፖርተር፡- ትግራይ የጥንት የኢትዮጵያ ሥልጣኔ መገኛ ነች፡፡ በዘመነ አክሱም ሆነ ቅድመ አክሱም፣ በደኣማት ቅርስና ውርሶችን የሚያሳዩ የድንጋይ ላይ ጽሑፎች በግእዝ፣ በሳባ፣ በግሪክ ይገኙበታል፡፡ እንዲሁም ሄይሮግራፊክስም መገኘቱም የሚያወሳ ጥናትም አይቻለሁ፡፡ በተለይ አካባቢው የግእዝ ሥነ ጽሑፍ 1,500 ዓመታት ታሪክም ዐቢይ አካል ነው፡፡ ከአክሱም እስክ ናዝሬን/ናዝሬት (ደቡብ ትግራይ) ጉንዳጉንዶን ጨምሮ በርካታ የግእዝ ሥነ ጽሑፍ ሀብት አለ፡፡ አካዴሚው ከዚህ አንፃር ምን ሥራ ይኖረዋል? በአካዴሚው አዋጅ ላይ ስለ ግእዝና ስለ ሌሎች ጥንታዊ ቋንቋዎች የሚያነሳው ነጥብ የለም፡፡ አካዴሚው ይኼን እንዴት ያየዋል?
/ ዳንኤል፡- ለጊዜው በክልሉ ሕገ መንግሥታዊ ዕውቅና ያገኙት ሦስቱ ቋንቋዎች ናቸው፡፡ ይኸ ማለት ግን በግእዝ ላይ የምንሠራው ሥራ አይኖርም ማለት አይደለም፡፡ ምክንያቱም ቀደም ብዬ እንደጠቀስኩት ሦስቱ ቋንቋዎች የሳይንስና ቴክኖሎጂ ቋንቋዎች እንዲሆኑ ይፈለጋሉ፡፡ ወደ ትርጉም ስንመጣ ግን የግድ ወደ ግእዝ እንሄዳለን፡፡ ወደ ሌሎችም የአገራችን ቋንቋዎችም እንዲሁ እንመለከታለን፡፡ በቋንቋዎቻችን የመዋዋስ ነገር አለ፡፡ ከግእዝ የሚወስዱት ብዙ ነገር ይኖራል፡፡ የግእዝ ህልውና ያስፈልጋል፡፡ አካዴሚው ጥናቱን ሲያጠቃልል የዶክመንቴሽን ማዕከል ይኖረዋል፡፡ ሦስቱ ቋንቋዎች ከምን ተነስተው እምን ደረሱና ምን ላይ ይገኛሉ? በሚል የዶክመንተሽን (ስነዳ) ማዕከል ይኖረዋል፡፡ ጎን ለጎን የግእዝ ስነዳ ማዕከል ይኖራል ብለን እናስባለን፡፡ ከግእዝ እንዋሳለን ስንል ሰነዶች ያስፈልጉናል፡፡ ማዕከሉ የሚያስፈልገን ሰነዶቹን የምናሰባስብበት ስለሚሆን ነው፡፡ ለትግርኛ፣ ኩናምኛና ሳሆኛ የምንጠቀምበት ይሆናል፡፡ የኅብረተሰቡ ባህል፣ ቋንቋ፣ ሥነ ልቦናዊ የሆኑ ሀብቶች፣ እንዲሁም ታሪክ ለማጥናትም ግእዝ የራሱ የሆነ አስተዋጽኦ ይኖረዋል፡፡ በትርጉም ዙሪያ ደግሞ በስፋት እየሄድን እናጠናዋለን ብለን እናስባለን፡፡
ሪፖርተር፡- ከሌሎች ተመሳሳይ ተቋማት ጋር ያላችሁ ወይም የሚኖራችሁ ግንኙነትስ እንዴት ይገለጻል?
/ ዳንኤል፡- አካዴሚያችን ገና በጅምር ላይ ነው ያለው፤ ተሞክሮ እናገኝበታለን ብለን ከምናስበው ተቋም ጋር አብረን መሥራት እንፈልጋለን፡፡ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የኢትዮጵያ ቋንቋዎችና ባህሎች አካዴሚ፣ ከብሔራዊ ቤተ መዛግብትና ቤተ መጻሕፍት ኤጀንሲ (ወመዘክር) ከኦሮሚኛ ቋንቋና ባህል ማዕከል፣ ከባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የአማርኛ ማበልፀጊያ ማዕከል፣ ወደ ደቡብ ሲኬድ የሀዲያን ተሞክሮ በስፋት እንዳስሳለን፡፡ አብረንም እንሠራለን፡፡ በተመሳሳይ መልኩ ውጭ ካሉት ከሩሲያ የቋንቋዎች አካዴሚ፣ ከጀርመን ሐምቡርግ ዩኒቨርሲቲ፣ ከስዊድን ጋርም ግንኙነት ጀምረናል፡፡ ምክንያቱም ትግርኛ የተጠናበትና እየተጠናበት ነው፡፡ ለአካዴሚው ግብአት ይኖረዋል እስካልን ድረስ ከተቋማት ሌላ ከግለሰቦች ጋርም አብረን ለመሠራት ዝግጁ ነን፡፡
ሪፖርተር፡- ትግርኛ በኤርትራም የሚነገር ቋንቋ እንደመሆኑ ትስስር አለ፡፡ በዚህስ ረገድ ምን ታስባላችሁ?
/ ዳንኤል፡- ኤርትራ አካባቢ የሚነገረውና እዚህ የሚነገረው ቋንቋ አንድ ነው፡፡ አሜሪካና እንግሊዝ የተለያዩ አገሮች ናቸው፡፡ በሁለቱም እንግሊዝኛ ይነገራል፡፡ በመካከላቸው የቋንቋ ድንበር አናበጅም፡፡ እንግሊዝኛ ነው ብለን ነው የምንቀበለው፡፡ በሁለቱም ያለው ትግርኛ ነው፡፡ ስለዚህ በሁለቱ መካከል የፖለቲካ ልዩነት ሊኖር ይችላል፡፡ ቋንቋው ግን እዚያም ሆነ እዚህ ሲነገርም ሆነ ሲጻፍ ተደጋግፈው ቢሄዱ ቋንቋውን ይበልጥ ያበለፅጉታል፡፡ በኤርትራ የሚጻፉ ለምሳሌ መዛግብተ ቃላት ያስፈልጉናል፤ እንጠቀምባቸዋለን፡፡ እዚህ የሚጻፉ እነሱም ይጠቀሙባቸዋል፡፡ በኤርትራ የተሠሩ የተለያዩ ጥናቶችም እያየን ነው፡፡ በትግራይ ተወላጆች የተጻፉ የትግርኛ ጽሑፍን አጣቅሰው (ሪፈር አድረገው) ጥናቶችን የሚያቀርቡበት ሁኔታ አለ፡፡ ስለዚህ የምናወራው ስለ ትግርኛ ነው፡፡ ፖለቲካው ሌላ ነገር ነው፤ ለትግርኛ ቋንቋ ዕድገት የሚጠቅም እስከሆነ ድረስ እንጠቀምበታለን፡፡
ሪፖርተር፡- የፊደል አጠቃቀምን በተመለከተ በመGለና በአስመራ በተለይ ሁለቱ ‹‹›› እና ‹‹›› ላይ ልዩነት አለ፡፡ አስመራዎች ‹‹›› ሲጠቀሙ Gለዎች ‹‹›› ይጠቀማሉ፡፡ አንዳቸው አንዱን ጥለዋል፡፡ ትርጉም ላይ ልዩነት ያሳያል፡፡ ለምሳሌ በአስመራ ‹‹ጸሓይ›› በመG ‹‹ፀሓይ›› ተብሎ ይጻፋል፡፡ የመGለው ታዳጊ የአስመራውን ሲያነብ ‹‹›› ስለማያውቃት ‹‹›› ብሎ ሲያነባት፣ የአስመራው በበኩሉ ‹‹›› ስለማያውቃት ‹‹›› ብሎ ስለሚያነባት አለመግባባት ይፈጥራል፡፡ በዚህ ረገድ ምን ማለት ይቻላል?
/ ዳንኤል፡- ሁለት ነገሮችን እናንሳ፡፡ አንደኛው በትግርኛ ፊደላት ሞክሼነት የለም፡፡ ሁሉም ራሳቸውን ችለው በየድምፃቸው የቆሙና አገልግሎት የሚሰጡት፡፡ ምናልባት ‹‹›› ጸሐዩና፣ ‹‹›› ጸሎቱ፣ ‹‹›› ንጉሡና ‹‹›› እሳቱ አካባቢ ችግር ሊኖር ይችል ይሆናል፡፡ እንደ ችግርም ላይነሳ ይችላል፡፡ ትልቁ ችግር እየተፈጠረ ያለው ተማሪዎች ሕፃኖቻችን ሲማሩ የአማርኛ ፊደል ገበታን መጠቀማቸው ነው፡፡ ለምሳሌ አፀደ ሕፃናት (ኬጂ) ብትሄድ አማርኛ ለማስተማር በተቀረፁ የፊደል ገበታ ትግርኛን ይማራሉ፡፡ በትግርኛና በአማርኛ መካከል በአጠቃቀም ሰፊ ልዩነት አለ፡፡ ለምሳሌ ‹‹በርሀየመጀመርያው [] ነው፡፡ ‹‹አብርሃ›› አራተኛው ( ራብዕ) ነው፡፡ የአማርኛ ተጽዕኖ ነው ወደ ትግርኛ መጥቶ ችግር የፈጠረው፡፡ ያነሳኸው ልዩነት በኤርትራና በትግራይ ያለው የሁለቱ ፊደላት አጠቃቀም ሥነ ዘዴያዊ (ሜቶዶሎጂካል) ዕይታ አለው፡፡ እኛ ‹‹›› ፀሓዩን ለመጠቀም የወሰንነው በጥናት ነው፡፡ ምናልባት ሌላ ተጨማሪ ጥናት ያስፈልጋል ቢባል ያስኬዳል፡፡ ግን አንዳንዱ የፊደል አወሳሰዱ ጥናት ላይ የተመሠረተ አይደለም የሚለውን አስተሳሰብ አልደግፈውም፡፡ ለግእዝ ሁለቱም ‹‹›› እና ‹‹›› የተለያዩ ናቸው፡፡ በትርጉም ደረጃ የሚያስተላልፉት መልዕክት አለ፡፡ እንደ ‹‹ሠረቀ›› እና ‹‹ሰረቀ››፡፡ በትግርኛ ግን አንድ ‹‹›› ብቻ እንጠቀማለን፡፡ እሳቱ ‹‹›› የሆነበት ምክንያት ፊደል ስናስተምር ‹‹›› ብለን እንጀምራለን፡፡ አናቱ ላይ ጭረት አድርግ ካልነው አንድ ፊደልን በቀላሉ ተማረ ማለት ነው፡፡ ሌላ ‹‹›› ከሆነ ግን እናበዛበታለን፡፡ ሸክም ነው፡፡ ‹‹›› ተምሮ ‹‹›› ከዚያ ‹‹›› ላይ አግድም ሲያደርግበት ‹‹›› ይሆናል፡፡ ስለዚህ አንድ ልጅ ፊደልን ለማጥናት ስለሚያቀላጥፍለት፣ ለትምህርት ዕድገት በጎ አስተዋጽኦ ስላለው በዚህ ተመረጠ፡፡ ‹‹›› እና ‹‹›› ላይ ስንሄድም ተመሳሳይ ነው፡፡ በትግርኛ ‹‹›› አስተምረን ስንጨርስ መሀል ላይ ሠረዝ አድርግና ‹‹›› አድርገው፡፡ በቀላሉ እንዲገነዘበው ለማድረግ ነው፡፡ ጸሎቱ ‹‹›› ግን ‹‹›› ጋር ይምታታል፡፡
ስለዚህ አካሄዳችን ከትምህርት ሥነ ዘዴ አኳያ ተቀባይነት ያለውና በጥናት ላይም የተመሠረተ ነው፡፡ ከቅርስ ጋር ተያይዞ የሚነሳ አስተያየት አለ፡፡ የቅርስ ጉዳይ እኛንም ያገባናል፡፡ ሥርዓተ ጽሕፈታችን ይዞ ያመጣቸው ሁለቱ ‹‹ ›› መጥፋት የለባቸውም የሚለውን እንደግፋለን፡፡ በቅርስነታቸው ለመቀበል ሁለት ዓይነት አማራጭ አለ ብዬ አስባለሁ፡፡ አንዱ አማራጭ ግእዝ ቋንቋን ማዳን ነው፡፡ እርሱን ማዳን ካልተቻለ ቢያንስ ቢያንስ ድሮ የተጻፉ በመጻሕፍት መልክ ያሉትን ሰነዶች ሰንዶ ለትውልድ ማቆየትና ማስተላለፍ ነው፡፡
ሪፖርተር፡- በአካዴሚው ማቋቋሚያ አዋጅ አማካሪ ቦርድ አባላት ብሎ ከዘረዘራቸው ውስጥ ከትግርኛም ሆነ ከሳሆ እና ኩናማ ቋንቋዎች ጋር በተያያዘ በርካታ ሥራ የሠሩ የሃይማት ተቋማት ለምን እንዲካተቱ አልተደረገም? ለምሳሌ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሥር የሚገኘው የኢትዮጵያ ቋንቋዎችና ባህሎች አካዴሚ ከኦርቶዶክስ፣ ካቶሊክና እስልምና ተቋማት የተወከሉ ሊቃውንትን በቦርድ አባልነት አቅፏል፡፡ ከነርሱ ልምድ መቅሰም አይቻልም? ለአካዴሚያችሁስ አይበጅም?
/ ዳንኤል፡- በሁለት መልኩ እንየው፡፡ አማካሪው ቦርድ አቅጣጫ የሚሰጥ ነው፡፡ አካዴሚው የራሱን ዕቅድ እየነደፈ አቅጣጫ እያስቀመጠ ለቦርዱ ያቀርባል፡፡ አማካሪው ቦርድ በሚቀርብለት ጉዳይ ሐሳብ ይሰጣል፡፡ ሁለተኛው የጠቀስካቸው የሃይማኖት ተቋማት በጣም ጠቃሚ ናቸው፡፡ የሃይማኖት ተቋማቱን ብቻ ሳይሆን ግለሰቦች ጭምር ከአካዴሚው ጋር እንዲሠሩ የሚደረግበትም አሠራር ይኖረናል፡፡ ስለዚህ የሃይማኖት ተቋማት፣ ከቋንቋና ባህል ጋር የተያያዙ ባለሙያዎች፣ ምሁራን ይኖሩበታል፡፡ ሙያዊ ሥራ የሚሠራ አካልም ከሁሉም የሚውጣጣ ስለሚኖር ተቋማቱ የሚተው አይደሉም፡፡