የኦሊምፒክና
የዓለም ዋንጫ በ5,000 ሜትርና በ10,000 ሜትር ሻምፒዮን የነበረው የገናናው አትሌት ሻምበል ምሩፅ ይፍጠር
ሥርዓተ ቀብር ዛሬ እሑድ ታኅሣሥ 23 ቀን 2009 ዓ.ም. ከቀኑ ስምንት ሰዓት በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ
ካቴድራል ይፈጸማል፡፡
በመተንፈሻ አካል ችግር ምክንያት ሕክምናውን ሲከታተልበት በነበረው ካናዳ ታኅሣሥ 13 ቀን በቶሮንቶ ሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ 3 ሰዓት 05 ደቂቃ ያረፈው ሻምበል ምሩፅ፣ አስክሬን አዲስ አበባ የሚደርሰው፣ በዛሬው ዕለት ከጧቱ አንድ ሰዓት ከሩብ መሆኑን የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ አስታውቋል፡፡
የኮሚቴው ዋና ዳይሬክተር አቶ ታምራት በቀለ ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ በታላቅ ሀገራዊ ክብር በሀገር መከላከያ ሠራዊት የክብር ዘብ ታጅቦ ሥርዓተ ቀብሩ ይፈጸማል፡፡ በቤተሰቡና በከፍተኛ የመንግሥት ሹማምንት አቀባበል ከተደረገ በኋላ አስክሬኑ ቦሌ መድኃኔ ዓለም ቤተ ክርስቲያን አካባቢ በሚገኘው መኖሪያ ቤት ቆይታ ያደርጋል፡፡ ስንብትና በክብር መዝገብ ላይ አስተያየት የሚሰጥበት ሥነ ሥርዓት ከተከናወነም በኋላ በታላቅ ወታደራዊ አጀብ በቦሌ ዋናው መስመር፣ በዳግማዊ ምኒልክ ጎዳና ከመስቀል አደባባይ ሽኝት በኋላ ወደ ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ሲያመራ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አካባቢ እንደደረሰ በማርሽ ባንድ መሪነት በሐዘን ዜማ ታጅቦ ከማረፊያው ይደርሳል፡፡
በቤተ ክርስቲያኒቱ ከሚኖረው ሃይማኖታዊ ሥርዓት ባሻገር፣ የአገሪቱ ርእሰ መንግሥት፣ የወጣቶችና ስፖርት ሚኒስቴር፣ የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴና ብሔራዊ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን መልዕክቶች እንደሚተላለፉ ታውቋል፡፡
ለገድለኛው (ሌጀንድ) ኢትዮጵያዊ ሯጭ ምሩፅ ይፍጠር፣ ባረፈበት የካናዳዋ ቶሮንቶ ከተማ፣ ማክሰኞ ታኅሣሥ 18 ቀን 2009 ዓ.ም. በዚያው በምትገኘው ቅድስት ማርያም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ጸሎተ ፍትሐት መደረጉ ይታወሳል፡፡
‹‹ይፍጠር ዘሺፍተር›› (ማርሽ ቀያሪው ምሩፅ ይፍጠር)፣ ‹‹ይፍጠር ዘማስተር›› (የሩጫ ጌታው ምሩፅ ይፍጠር) በመባል የዐቢይ አድናቆት ባለቤት የነበረው ምሩፅ ይፍጠር በ1972 ዓ.ም. (እ.ኤ.አ. 1980) በሞስኮ ኦሊምፒክ ሁለት ወርቆችን በ10,000 ሜትርና በ5,000 ሜትር፣ በ1964 ዓ.ም. (እ.ኤ.አ. 1972) በሙኒክ ኦሊምፒክ በ10,000 ሜትር የነሐስ ሜዳሊያ ያሸነፈ ሲሆን፤ አህጉሮች በሚወዳደሩበትና በ1969 እና በ1971 ዓ.ም. በተከታታይ በተካሄዱት የዱዞልዶርፍና የሞንትሪያል የዓለም አትሌቲክስ ዋንጫ ምሩፅ ይፍጠር አራት ወርቆችን በ10,000 ሜትርና በ5,000 ሜትር ለአፍሪካ ማስገኘቱ ይታወቃል፡፡
ገድለኛው ምሩፅ በዐሥራ ስድስት ዓመታት የሩጫ ሕይወቱ፣ ከመካከለኛ ርቀት ማለትም ከ1,500 ሜትር እስከ ረዥም ርቀት (5,000 እና 10,000 ሜትር)፣ እንዲሁም ግማሽ ማራቶንን ጨምሮ ባሉት ርቀቶች በመወዳደርና ከ250 በላይ በመወዳደር በአንደኛነት ማጠናቀቁ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡
የኦሊምፒክ ሻምፒዮኑ ምሩፅ ሥርዓተ ቀብሩን በክብር ለማስፈጸም ከወጣቶችና ስፖርት ሚኒስቴር፣ ከኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ፣ ከብሔራዊ አትሌቲክስ ፌዴሬሽንና ከቤተሰቡ የተወጣጡ አባላት ያሉት ኮሚቴ እየሠራ መሆኑ ይታወሳል፡፡
ከአባቱ አቶ ይፍጠር ተክለሃይማኖትና ከእናቱ ወ/ሮ ለተገብርኤል ገብረአረጋዊ በ1937 ዓ.ም. በትግራይ፣ ዓዲግራት የተወለደውና በ72 ዓመቱ ያረፈው ምሩፅ ይፍጠር የሰባት ልጆች አባት ነበር፡፡

- ሔኖክ ያሬድ's blog
- 11 reads
No comments:
Post a Comment