Friday, November 25, 2016

የግዕዝ ትምህርት በቶሮንቶ ዩንቨርሲቲ

 ቀን 22.11.2016

 ካናዳ የሚገጘዉ የቶሮንቶ ዩንቨርሲቲ የግዕዝ ቋንቋ ትምህርት መስጠት እንደሚጀምር ተገለጠ። በዩንቨርሲቲዉ በታሪክ ትምህርት ዘርፍ ዶክተር የሆኑት ፕሮፌሰር ማይክል ግሬቨርስ ለዶይቼ ቬለ እንደተናገሩት በቅርብና መካከለኛዉ የምስራቅ ስልጣኔ ትምህርት ክፍል ስር በጎርጎሮሳዊዉ ዘመን ቀምር ከጥር 2017 ጀምሮ  ቋንቋዉን ማስተማር ይጀምራል።
በግዕዝ ቋንቋ በርካታ ጥንታዊ የሥነ-ፅሁፍ ፣ የፍልስፍና ፤የሥነ-ክዋክብት እንዲሁም የሕክምና ጹሁፎች በመኖራቸዉ  ቋንቋዉን ማጥናት የመካከለኛዉ ዘመንን የሜዲተራንያን ስልጣኔና ታሪክ ላይ ለሚደረገዉ ምርምር ከፍተኛ አስተዋፅኦ አለዉ ተብሏል።                     
ከደቡብ ሴሜቲክ ቋንቋ የሚመደበዉ የግዕዝ ቋንቋ በአክሱም ዘመን ይነገር እንደነበር መዛግብት ይጠቁማሉ ።በጎዕዝ የተፃፉ አበዛኛወቹ መፃህፍት ሀይማኖታዊ ይዘት ያላቸዉ ቢሆኑም የመካከለኛዉ ዘመን ስልጣኔን የሚሳያሳዩ የተለያዩ የስነፅሁፍ፣ የፍልስፍና፤ የህክምናና የስነከዋክብት መፃህፍትም በዚሁ ቋንቋ እንደሚገኙ የዘርፉ ተመራማሪወች ይገልፃሉ። በመሆኑም የመካከለኛዉን ዘመን ታሪክ ለሚያጠኑ ተመራማሪወች አሁን አሁን ቀልብ እየሳበ የመጣ ይመስላል።
በቶሮንቶ ዩንቨርሲቲ በታሪክ ትምህር ዘርፍ ዶክተር የሆኑት ፕሮፌሰር ማይክል ግሬቨርስ እንደሚናገሩት በቶሮንቶ ዩንቨርሲቲ የቅርብና የመካከለኛዉ ዘመን ስልጣኔ ትምህርት ክፍል ስር በጎርጎሮሳዊዉ ዘመን ቀመር ከጥር 2017 ጀምሮ የግዕዝ ቋንቋ መስጠት ይጀምራል ።በትምህርት ክፍሉ ከአሁን ቀደም አረብኛና ዕብራይስጥን የመሳሰሉ የሴም ቋንቋወች እየተሰጡ መሆናቸዉን ፕሮፌሰር ማይክል ግሬቨርስ ተናግረዋል።
«ግዕዝ የኢትዮጵያ ጥንታዊ የቤተክርስቲያን ቋንቋ ብቻ አይደለም ። ከአረብኛና ከዕብራይስጥ ጋር  ዝምድና ያለዉ አስፈላጊ ቋንቋ ነዉ።
ይህንን ቋንቋ የሚያስተምሩ የቶሮንቶ ዩንቨርሲቲ የቅርብና የመካከለኛዉ  ምስራቅ  ስልጣኔ ትምህርt ክፍል ሰወች አረብኛና ዕብራይስጥም ያስተምራሉ።»
በኢትዮጵያ ታሪክ ላይ ምርምር ያካሄዱት ፕሮፌሰር ማይክል ግሬቨርስ፤ ላቲን በአዉሮፓ ባህልና ቋንቋ ላይ ያለዉን ተፅኖ ያህል ግዕዝም በምስራቅ  አፍሪካ ታሪክ ላይ ተፅዕኖ አለዉ ብለዋል። ምንም እንኳ ቋንቋዉ በአሁኑ ወቅት  ከቤተክርስቲያን ዉጭ ተግባቦት ላይ እየዋለ ባይሆንም ፣በቋንቋዉ የተፃፉ የመካከለኛዉ ዘመን የሜዲተራኒያንን ታሪክና ስልጣኔ የሚያሳዩ በርካታ ፅሁፎች እንደሚገኙ ገልፀዋል።
 « ግዕዝ ቋንቋ የተፃፉ በግዕዝ ብቻ የምናገኛቸዉ ፅሁፎች አሉ። በቀደመዉ ዘመን ወደ ግዕዝ የተተረጎሙ ነገር ግን መሰረታቸዉ የሜዲተራንያኑ አለም የሆኑ የጠፉና በጭራሽ ሊገጉ የማይችሉ ፅሁፎችም አሉ ። እነዚህን ፅሁፎች  ለማግኘት ከኢትዮጵያ በስተቀር ሌላ  አማራጭ  የለም።»
ይሁን እንጅ  ግዕዝን ማጥናት በቋንቋዉ የተፃፉ የ2000 አመት እድሜ ያላቸዉን በርካታ ፅሁፎች ላይ ምርምርና ጥናትን ለማድረግ እድል የሚሰጥና ለታሪክ ምርምር ዘርፍ ከፍተኛ አስተዋፅኦ እንደሚያበረክት  ፕሮፌሰሩ ተናግረዋል።ይሁን እንጅ ቋንቋዉ ያለዉን ጠቀሜታ ያህል ትኩረት አልተሰጠዉም ። በመሆኑም የቶሮንቶ ዩንቨርሲቲ ይህንን የጥናት ተቋም በሰሜን አሜሪካ የኢትዮጵያ ጥናት ማዕከል የማድረግ አላማ እንዳለዉ ጨምረዉ ገልፀዋል።
«በተለየ ሁኔታ ተስፋ የምናደርገዉ እዚህ ቶሮንቶ የከፈትነዉ። የጥናት ተቋም ወደፊት በሰሜን አሜሪካ የኢትዮጵያ ጥናት ማዕከል እንዲሆን ነዉ።  ያ ነዉ የእኛ አላማ።»                         
ለጥናት ተቋሙ በካናዳ የሚገኙ የኢትዮጵያ ማህበረሰብ አባላት የገንዘብ ድጋፍ ያደረጉ ሲሆን በተለይ ዘ ዊክ ኤንድ በሚባል ቅፅል ስሙ የሚታወቀዉ  ድምፃዊ  አቤል ተስፋየ በግሉ 50 ሺህ የካናዳ ዶላር ማበርከቱ ታዉቋል።
በጀርመን ሃገር ሃምቡርግ ዩንቨርሲቲ በኢትዮጵያ ጥናቶች ትምህርት ክፍል እየተሰጠ የሚገኘዉ የግዕዝ ቋንቋ፣ የቶሮንቶ ዩንቨርሲቲ ከኢትዮጵያ ዉጭ ያለ ሁለተኛዉ ግዕዝን የሚያስተምር ተቋም ይሆናል።

ፀሐይ ጫኔ
አዜብ ታደሰ

Monday, November 21, 2016

ኢትዮጵያ ከአፍሪካና ከዓለም የስፖርት የአመራር መንበሮች ለምን ራቀች? ‹‹ዓለም አቀፍ የስፖርት ተቋማት [ከኢትዮጵያ] ቋሚ ሰው እንደማያገኙ ነው ድምዳሜ ላይ የደረሱት››አቶ ፍቅሩ ኪዳኔ፣ የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት አማካሪ

ፎቶ ካፕሽን

በቅደም ተከተል

  ወ/ሮ ዳግማዊት ግርማይ የኢንተርናሽናል ኦሊምፒክ ኮሚቴ አባል ሆነው ጳጉሜን 5 ቀን 2005 ዓ.ም. በቦነስ አይረስ፣ አርጀንቲና በተመረጡበት ዕለት ከወቅቱ ፕሬዚዳንት ዣክ ሩገ ጋር፤ የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን፣ የአፍሪካ ስፖርት ኮንፌዴሬሽኖች ማኅበር ፕሬዚዳንት፣ የኢንተርናሽናል ኦሊምፒክ ኮሚቴ የፊፋ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል የነበሩት አቶ ይድነቃቸው ተሰማ፤ የአፍሪካ ብሔራዊ ኦሊምፒክ ኮሚቴዎች ማኅበር ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዚዳንት፣ የአፍሪካ ስፖርት ከፍተኛ ምክር ቤት ምክትል ፕሬዚዳንት የነበሩት አቶ ፀጋው አየለና አዲሱ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ሻለቃ ኃይሌ ገብረሥላሴ፡፡
19 Nov, 2016 ከሦስት አሠርታት በፊት በወቅቱ የዓለም እግር ኳስ ፌዴሬሽኖች ማኅበር-ፊፋ ፕሬዚዳንት ለነበሩት ብራዚላዊው ጆኦዎ ሃቨላንጅ (1908-2008) ጋዜጠኞች ‹‹ከርስዎ በኋላ የፊፋ ፕሬዚዳንት ማን ይሆናል? እርስዎን የሚተካው ማነው?›› ብለው ለጠየቋቸው የሰጡት ምላሽ ባጭር ቋንቋ ‹‹ሚስተር ተሰማ ነዋ!›› ብለው በወቅቱ የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን (ካፍ) ፕሬዚዳንት፣ እንዲሁም የአፍሪካ ስፖርት ኮንፌዴሬሽኖች ማኅበር ፕሬዚዳንትና የኢንተርናሽናል ኦሊምፒክ ኮሚቴ አባል የነበሩት አቶ ይድነቃቸው ተሰማ (1914-1979) ለቦታው እንደሚመጥኑ ተናግረው ነበር፡፡
ሃቨላንጅ ያለምክንያት አልነበረም እኚህን ታላቅ ኢትዮጵያዊና አፍሪካዊ የስፖርትና የኦሊምፒክ ግንባር ቀደም መሪ ይድነቃቸው ተሰማን ያጩት፡፡ የኢትዮጵያን ዘመናዊ ስፖርት ያደራጁ ልዩ ልዩ ሕጎችንና መተዳደሪያ ደንቦችን በአማርኛ ያዘጋጁ ለአፍሪካም የተረፉ ናቸው፡፡ የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴን ትክክለኛ መስመር ያስያዙ፣ የአፍሪካ ብሔራዊ ኦሊምፒክ ኮሚቴዎች ማኅበር (አኖካ) ብቻ ሳይሆን፣ በዓለም አቀፍ ደረጃ ብሔራዊ ኢሊምፒክ ኮሚቴዎች ማኅበር (አኖክ) ህልውና የተጉ፣ የአፍሪካን የተለያዩ ስፖርት ኮንፌዴሬሽን ያስተሳሰረው የአፍሪካ ስፖርት ኮንፌዴሬሽኖች ማኅበር የቆረቆሩ በመሆናቸው ሥራዎቻቸው ‹‹ፕሮዤ ተሰማ›› ለመባል የበቁ ነበር፡፡
ሃቫላንጅ ያኔ ይድነቃቸውን ለፊፋ ፕሬዚዳንትነት ሲያስቧቸው ለጥቆማቸው አክብሮታቸውን የገለጹት አቶ ይድነቃቸው፣ በጤና ምክንያት እንደማያስቡት መናገራቸው ይታወሳል፡፡
ኢትዮጵያውያን በአህጉራዊ ስፖርት አመራር
በመጨረሻው የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት መንግሥት (1923-1967) ሆነ በኅብረተሰብአዊት ኢትዮጵያ ጊዜያዊ ወታደራዊ አስተዳደር ደርግ መንግሥት (1967-1979) ዘመኖች፣ ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ የስፖርት ፌዴሬሽኖች፣ በአፍሪካ የተለያዩ ኮንፌዴሬሽኖች፣ በኢንተርናሽናል ኦሊምፒክ ኮሚቴ (አይኦሲ) የአመራርነት እንዲሁም በተለያዩ ኮሚቴዎች በአባልነት ተሳትፎዋ ትታወቅ ነበር፡፡
በዘመነ ይድነቃቸው በአህጉሪቱ የተለያዩ ኮንፌዴሬሽኖች ኢትዮጵያውያን በአህጉራዊው አመራር ውስጥ ነበሩ፡፡ ለምሳሌ አቶ ታደለ መለሰ የአፍሪካ አትሌቲክስ ኮንፌዴሬሽን ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል፣ አቶ ሰሎሞን በቀለ የአፍሪካ ብስክሌት ኮንፌዴሬሽን ምክትል ፕሬዚዳንትና የምሥራቅና መካከለኛው አፍሪካ ብስክሌት ኮንፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ነበሩ፡፡ ከአቶ ይድነቃቸው ቀጥሎ የአካል ማሠልጠኛና ስፖርት ኮሚሽን ኮሚሽነር የነበሩት አቶ ፀጋው አየለ፣ የአፍሪካ ስፖርት ከፍተኛው ምክር ቤት ምክትል ሰብሳቢ፣ የአፍሪካ ብሔራዊ ኦሊምፒክ ኮሚቴዎች ማኅበር (አኖካ) ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዚዳንት ነበሩ፡፡
አቶ ፀጋው በስፖርትና በኦሊምፒክ መድረኮች ላበረከቱት የላቀ አስተዋጽዖ፣ በኢንተርናሽናል ኦሊምፒክ ኮሚቴ ይሁንታ አግኝተው በወቅቱ ፕሬዚዳንት ጁዋን ኦቶንዮ ሳማራንሽ አማካይነት፣ የአገሪቱ ርእሰ ብሔር ኮሎኔል መንግሥቱ ኃይለማርያም በተገኙበት የኦሊምፒክ ኦርደር ሜዳይ መሸለማቸው ይታወቃል፡፡ አቶ ፀጋው በአህጉር ደረጃ የአመራር ቦታ መያዝና የአይኦሲ ቀልብም እሳቸው ላይ ማረፍ ሲጀምር፣ እንደ አቶ ይድነቃቸው፣ የኢንተርናሽናል ኦሊምፒክ ኮሚቴ አባል ሆነው ለመታጨት በሩ የሚከፈትላቸው ጊዜ ሩቅ እንደማይሆን ተስፋ ያደረጉ ጥቂት አልነበሩም፡፡
ይሁን እንጂ ደርግ፣ የኢትዮጵያ ሕዝባዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክን (ኢሕዲሪ) በ1980 ዓ.ም. ሲመሠርት፣ ቀደም ብሎ በአደረጃጀት ራሱን ችሎ የነበረው ስፖርት ኮሚሽን ፈርሶ ከባህል ጋር ሲቀላቀልና ባህልና ስፖርት ጉዳይ ሚኒስቴር ሲባል፣ ኮሚሽነር ፀጋው አየለ ከቦታው ተነስተው የአካባቢ ጉዳዮች ሚኒስትርነት በመሾማቸው ከስፖርቱና ከኦሊምፒኩ ተፋቱ፡፡
በአህጉር ደረጃ በስፖርቱም ሆነ በኦሊምፒክ አመራርነት ለመመረጥ በቀላሉ የማይገኘውን ክብር ያገኘችው ኢትዮጵያ መንበሩን አጣች፡፡ ሌሎች ያሰፈሰፉት ጨበጡት፡፡
በስፖርት ተወልዶ በስፖርት ውስጥ ያለፈን፣ በወወክማ ኢትዮጵያ በልዩ ልዩ ተግባሮች የተሳተፈና እስከ ዋና ጸሐፊነት የደረሰ፣ የኢትዮጵያ ቅርጫት ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት፣ የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ዋና ጸሐፊ፣ በስፖርት ኮሚሽን የውድድር ስፖርቶች መምሪያ ኃላፊ የነበረ፣ በኋላም ኮሚሽነርና ብሔራዊ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ፕሬዚዳንትነት ደረጃ የደረሰን ኢትዮጵያዊ፣ ለአህጉር አመራርነት ብሎም ለዓለም በሚንደረደርበት ጊዜ ማቆም ለምን? አሰኝቶ ነበር፡፡
ከሩብ ምታመት በፊት የተደረገውን የመንግሥት ለውጥ ተከትሎ፣ የስፖርት ፌዴሬሽኖችን የሚመሩት አባላት የሚመርጡበት ሒደት፣ ስፖርቱን በተለይም ክለቦችን ማዕከል ያደረገ ባለመሆኑና ባመዛኙ ከስፖርቱ ጋር ትውውቅ የሌላቸው መሆኑ፣ ባለፉት ዓመታት የታዩት ውጣ ውረዶች፣ በተለይ በእግር ኳስ ፌዴሬሽን ውስጥ ተፈጥሮ የነበረው ቀውስ በፊፋ እስከ መታገድ የተደረሰበት ገጽታ ይነሳል፡፡
በእግር ኳስና በአትሌቲክስ በምሥራቅና መካከለኛ አፍሪካ ደረጃ ለአመራርነት በቅተው የነበሩት ዶ/ር አሸብር ወልደጊዮርጊስና ወ/ሮ ብስራት ጋሻውጠና ይጠቀሳሉ፡፡ ዶ/ር አሸብር የካፍ ምክትል ፕሬዚዳንትነት ሊበቁ የሚችሉባቸው አጋጣሚዎች ቢፈጠርላቸውም በአገር ቤት የተፈጠረው ውዝግብ እንዲያመልጣቸው ማድረጉ ይነገራል፡፡
ብሔራዊ አትሌቲክስ ፌዴሬሽንን ለስምንት ዓመታት በመምራት ልምድ ያካበቱትና ለክፍለ አህጉራዊው ኮንፌዴሬሽን መሪነት በቅተው የነበሩት ወ/ሮ ብሥራት ጋሻው ጠና፣ በአህጉራዊው ኮንፌዴሬሽን በተለይም ዓለም አቀፍ አትሌቲክስ ፌዴሬሽኖች ማኅበር ምክር ቤት አባልነት ታጭተው፣ የውድድር ጊዜውን እየጠበቁ ሳለ ከብሔራዊው ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንትነት እንዲነሱ መደረጉ ዋጋ አስከፍሏል፡፡
ከርሳቸው ጋር ተፎካካሪ የነበሩት የሌሎች አገሮች ዕጩዎች በቀላሉ ለመመረጥ አስችሏቸዋል፡፡ ኢትዮጵያ በአትሌቲክስ በተለይም በረዥም ርቀትና በማራቶን ገናና ስም ያላት መሆኑ ሥጋት ፈጥሮባቸው ነበር፡፡ ‹‹ባለቤቱ ያቀለለውን…›› እንዲሉ የኢትዮጵያ ዕድል አምልጧል፡፡
በኢንተርናሽናል ኦሊምፒክ ኮሚቴና በአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን፣ እንዲሁም በተለያዩ ተቋማት በልዩ ልዩ ቦታዎች ያገለገሉትና እያለገሉ ያሉት የቀድሞው የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ዋና ጸሐፊ አቶ ፍቅሩ ኪዳኔ፣ ሃቻምና (2007 ዓ.ም.) ከሪፖርተር ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ በወ/ሮ ብሥራት ላይ የተፈጸመውን ድርጊት ተችተው ነበር፡፡ እንዲህ ሲሉ፡-
‹‹በኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የተደረገውን ብንመለከት፣ ወ/ሮ ብሥራት ለትልልቅ ዓለም አቀፍ ተቋማት አመራርነት የሚያበቃቸውን መንገድ ሲጀምሩ ነው እንዲነሱ የተደረገው፡፡ ከአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን ጀምሮ በየደረጃው በሚገኙ ዓለም አቀፍ የስፖርት ተቋማት ውስጥ፣ ኢትዮጵያውያን የሚገቡበትን ሁኔታ ተነስቶ ውይይት ሲደረግ፣ ቋሚ ሰው እንደማያገኙ ነው ድምዳሜ ላይ የሚደርሱት፤ ለኔም ተደጋግሞ የሚነገረኝ ይኸው ነው፡፡ ይኼ ችግር ሥር የሰደደ ነው፡፡›› ይሄ ሥር የሰደደው ችግር አቶ ፀጋው አየለ ከተነሱበት ከ1980 ዓ.ም. የጀመረ ነው፡፡ ወ/ሮ ብሥራት በምን ምክንያት እንደተነሱ እንኳ አልተነገረም፡፡ ‹‹ክልሉ ውክልናዬን አንስቻለሁ፤›› ማለቱ ብቻ ነበር የተሰማው፡፡
‹‹ብቸኛዋ ኢትዮጵያዊት››
ኢትዮጵያ በአሁን ወቅት በዓለም አቀፍና በአህጉር፣ እንዲሁም በኢንተርናሽናል ኦሊምፒክ ኮሚቴ በአመራርነትና በአባልነት ያላት ወ/ሮ ዳግማዊት ግርማይ ናቸው፡፡ የኢትዮጵያ ባድሚንተን ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንቷ ወ/ሮ ዳግማዊት፣ የአፍሪካ ባድሚንተን ኮንፌዴሬሽን ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል፣ የብሔራዊ ኦሊምፒክ ኮሚቴዎች ማኅበር (አኖክ) ሥራ አስፈጻሚ ቦርድ አባል ናቸው፡፡ ከጳጉሜን 5 ቀን 2005 ዓ.ም. ወዲህ ደግሞ የኢንተርናሽናል ኦሊምፒክ ኮሚቴ በግል አባል ሆነዋል፡፡ (ጳጉሜን 5 ቀን በኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ታሪክ ልዩ ቦታ አላት፤ አበበ ቢቂላ በሮም ኦሊምፒክ ማራቶን ድል ያደረገው ጳጉሜን 5 ቀን 1952 ዓ.ም. ነበር)፡፡ ቀደም ሲልም በኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ዋና ጸሐፊነታቸው በኢንተርናሽናል ኦሊምፒክ ኮሚቴ አባልነት ሲሠሩ ነበር፡፡ እንዲሁም የኢትዮጵያን ኦሊምፒክ ኮሚቴ ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዚዳንት፣ ፕሬዚዳንትና ዋና ጸሐፊነት ከማገልገላቸው በተጨማሪ፣ አቶ ፀጋው አየለ በተቀዳሚ ምክትል ፕሬዚዳንትነት መርተውት በነበረው የአፍሪካ ብሔራዊ ኦሊምፒክ ኮሚቴዎች ማኅበር (አኖካ)፣ የሥራ አስፈጻሚ ቦርድ አባል ሆነው አገልግለዋል፡፡
የነ ኃይሌ ገብረሥላሴ አብዮት ይቀጥል ይሆን?
በብሔራዊ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ለዘመናት የአመራርነት ቦታን ያጡት አትሌቶች ዘንድሮ ባስነሱት ‹‹አብዮት›› መንበሩን ጨብጠውታል፡፡ ፌዴሬሽኖች የክለቦች መሆኑን ያሳየው 20ኛ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ጉባኤ፣ ሻለቃ ኃይሌ ገብረሥላሴን ፕሬዚዳንት፣ ገብረእግዚአብሔር ገብረማርያምን ምክትል ፕሬዚዳንት አድርጎ መርጧል፡፡ ሁለቱም በአትሌቲክሱ ውስጥ ያለፉና የላቀ ደረጃ ላይ የደረሱ መሆናቸው ይታወቃል፡፡
ለበርካታ ዓመታት በብሔራዊ ፌዴሬሽን አመራር ውስጥ የአዲስ አበባ አትሌቲክስ ክለቦች ሳይኖራቸው ቆይቶ ለመጀመሪያ ጊዜ ሁለት ባለሙያዎችን ሻለቃ ኃይሌና ዶ/ር በዛብህ ወልዴን በዘንድሮው ምርጫ አስገብተዋል፡፡ ዶ/ር በዛብህ የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ የቀድሞ ዋና ጸሐፊ የነበሩ ሲሆን፣ በተሰናባቹ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ በአባልነት የተሰየሙት ምክትል ፕሬዚዳንት የነበሩት ዘብጥያ በመውረዳቸው ነበር፡፡
እነ ሻለቃ ኃይሌ ወደ አመራርነት መምጣት ባላቸው ገናና ስም አማካይነት ወደ አህጉራዊና ዓለማቀፋዊ የስፖርትና ኦሊምፒክ ተቋማት የመግባት የመመረጥ ዕድላቸው እንደሚሰፋ ይታመናል፡፡
የብሔራዊ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የምርጫ ሒደት ፋና ወጊ ሆኖ በሌሎችም ብሔራዊ ፌዴሬሽኖች እንዲንፀባረቅ የሚፈልጉ ለየስፖርቱ ልዕልና ብቻ ሳይሆን ኢትዮጵያ በተለየ ታዋቂ በሆነችባቸውና በአህጉር ደረጃ ኮንፌዴሬሽንን በመመሥረት ከታወቀችባቸው የአህጉርና የዓለም አመራርነት ለመመለስ በር እንደሚከፍትላት ነው፡፡      

Monday, November 14, 2016

ለ25 ታላላቅ አርበኞች የመታሰቢያ ቴምብሮች ታተሙ


ኢትዮጵያን ከ1928 እስከ 1933 ዓ.ም. ድረስ ወርሮ የነበረው የኢጣሊያ ፋሺስት ሠራዊት፣ ድል የተመታበትን 75ኛ ዓመት የአልማዝ ኢዮቤልዩ የድል በዓል ምክንያት በማድረግ ሦስት የውጭ አገር ዜጎችን ጨምሮ ለ25 ታላላቅ አርበኞች የመታሰቢያ ቴምብር ታተመላቸው፡፡
የኢትዮጵያ ፖስታ አገልግሎት ድርጅት ‹‹የኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞች 75ኛ ዓመት መታሰቢያ የድል በዓል›› በሚል ርእስ ያሳተመው ስድስት ዓይነት ቴምብሮችን ኅዳር 1 ቀን 2009 ዓ.ም. በመላ አገሪቱ አሠራጭቷል፡፡
አምና በሚያዝያ 2008 ዓ.ም. የጥንታዊት ኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞች ማኅበር የድሉን አልማዛዊ ኢዮቤልዩ በብሔራዊ ደረጃ በልዩ ልዩ ዝግጅቶች ሲያከብር አንዱ እቅዱ የአርበኞች መታሰቢያ ቴምብር ማሳተም ነበር፡፡
እንደ ማኅበሩ መግለጫ፣ በቴምብሮቹ ላይ እነማን ይካተቱ በሚለው ጉዳይ ዙሪያ የማኅበሩ የሥራ አመራር ምክር ቤት መክሮና ዘክሮበት በስማቸው ቴምብር እንዲታተምላቸው ከብዙዎቹ መካከል የመረጣቸው 25 ናቸው፡፡ በአንድ ቴምብር ላይ ከአራት እስከ ስድስት አርበኞችን የሚወክሉ ምስሎችን ወጥተዋል፡፡
በመስፈርቶቹ መሠረት ከተመረጡት አርበኞች መካከል ከሃይማኖታዊ ታላቅ ተልዕኮአቸው በተጨማሪ የአርበኝነት ግዳጅን በመወጣት በጀግንነት የሕይወት መስዋዕትነት የከፈሉት የምዕራብ ኢትዮጵያ ጎሬ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ሚካኤልና የምሥራቅ ኢትዮጵያ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ በመታሰቢያው ቴምብር ተካትተዋል፡፡
እንዲሁም ጠላትን ፊት ለፊት ተጋፍጠው የሕይወትና የአካል መስዋዕትነት እየከፈሉ ካርበደበዱት መካከል ራስ ደስታ ዳምጠው፣ ደጃዝማች ኃይሉ ከበደ፣ ልዕልት ከበደች ሥዩም መንገሻ (እመቤት ሆይ)፣ ደጃዝማች በላይ ዘለቀ፣ ደጃዝማች ኃይለማርያም ማሞ፣ ደጃዝማች ገረሡ ዱኪ፣ ደጃዝማች ባልቻ አባ ነፍሶ፣ ደጃዝማች አፈወርቅ ወልደሰማያት፣ ፊታውራሪ ዓለማየሁ ጎሹ፣ ሼህ ሆጄሌ አልሃሰን፣ ደጃዝማች ፍቅረማርያም አባተጫንና ኮሎኔል በላይ ኃይለአብ ይገኙበታል፡፡
በጥንታዊት ኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞች ማኅበር ፕሬዚዳንትነት ካገለገሉት መካከል፣ ሁለቱ ቀዳሚዎች ራስ አበበ አረጋይና ራስ መስፍን ስለሺ፤ በፋሺስቱ ሩዶልፍ ግራዚያኒ ላይ የካቲት 12 ቀን 1929 ዓ.ም. አደጋ የጣሉት አብርሃ ደቦጭ፣ ሞገስ አስገዶምና ስምዖን አደፍርስ፣ የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ በፋሺስቶች ሲዋረድ፣ መቀበል አቅቷቸው በሮም አደባባይና በኢጣሊያ በረሃዎች ታላቅ ገድል የፈጸሙት ደጃዝማች ዘርዓይ ድረስና ኮሎኔል አብዲሳ አጋ በየቴምብሮቹ ምስላቸው ታትሟል፡፡
የፋሺስቶች ወረራ አስቆጥቷቸው በአርበኝነት ተጋድሎ ከኢትዮጵያ ጐን ለቆሙ የውጭ ዜጐች እንግሊዛውያኑ ሲልቪያ ፓንክረስት፣ ሜጀር ጀነራል አርዲ ቻርለስ ዊንጌትና አሜሪካዊው ኮሎኔል ሲ ሮቢንሰንም የመታሰቢያ ቴምብሮቹ አካሎች ናቸው፡፡
በወቅቱ በነበረው የመንግሥታቱ ማኅበር (ሊግ ኦፍ ኔሽንስ) መቀመጫ ጄኔቭ በመገኘት፣ ለዓለም መንግሥታት አቤቱታቸውን ያሰሙት ንጉሠ ነገሥት ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ (1923-1967) ዲስኩር ሲያሰሙ የተነሱት ፎቶም የኅትመቱ አካል ነው፡፡ ከ80 ዓመታት በፊት፣ ሰኔ 23 ቀን 1928 ዓ.ም. ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ በሸንጎው ላይ ካደረጉት ዲስኩር የሚከተለው ኃይለ ቃል ይገኝበታል፡፡
‹‹… ከእግዚአብሔር መንግሥት በቀር የፍጡር መንግሥት ሁሉ አንዱ ከአንዱ የማይበልጥ ሥራ የለውም፡፡ ነገር ግን በምድር ላይ ኃይለኛ የሆነው መንግሥት ምንም በደል የሌለበትን የሌላውን መንግሥት ሕዝብ ለማጥፋት የሚገባው መስሎት በተነሳበት ጊዜ ተጠቂው ወገን ለመንግሥታት ማኅበር የተበደለውን የሚያቀርብበት ሰዓት ነው፡፡ እግዚአብሔር ታሪክ ለምትሰጡት ፍርድ ለመንግሥት ማኅበርም ምስክር ሆነው ይመለከታሉ…››
የጥንታዊት ኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞች ማኅበር ‹‹እኔ ለሀገሬ›› በሚል ርእስ ባዘጋጀው፣ የ75ኛ ዓመት የአልማዝ ኢዮቤልዩ የድል በዓል መታሰቢያ ቴምብሮች መግለጫው ላይ እንደተወሳው፣ በመታሰቢያ ቴምብሩ ላይ ምስሎቻቸው እንዲወጣ የተደረጉት አርበኞች አመራረጥ፣ ‹‹በተቻለ መጠን ሚዛናዊ የሆነ ኅብረ ብሔራዊና የጾታ ስብጥርን ከግንዛቤ ውስጥ ያስገባ ነው፡፡››
ይሁን እንጂ ከ25ቱ አርበኞች መካከል ሴት አርበኛ አንድ ብቻ መሆናቸው ለምን? ያሉ አልታጡም፡፡ በአምስቱ ዘመን በተለያዩ ግንባሮች በውጊያው አውድማ ውስጥ ከዘመቱት በሺዎች ከሚቆጠሩት ሴቶች መካከል አንዲት አርበኛ ልዕልት ከበደች ሥዩም ብቻ ለቴምብሩ በቅተዋል፡፡
ሌላው ቢቀር ማኅበሩ ለአልማዝ ኢዮቤልዩ መታሰቢያ ባሳተመው ‹‹እኔ ለሀገሬ›› መጽሔት ጀግንንታቸው የተዘረዘረላቸው ፊታውራሪ በላይነሽ ገብረ አምላክ ሁለተኛዋ ለመሆን ለምን አልታደሉም?
በ1928 ዓ.ም. በምሥራቅ ግንባር ሰርጎ የገባው የፋሺስት ወራሪን ፊታውራሪ በላይነሽ ገብረ አምላክ ሱሪ ታጥቀው፣ ዝናር ታጥቀው ብረት አንግተው ተፋልመዋል፡፡ ከፊታውራሪ በላይነሽ ጋር ከ15 ዓመታት በፊት ቃለምልልስ ባደረገው ‹‹እኔ ለሀገሬ›› መጽሔት አገላለጽ፣ ከወረራው 10 ዓመት በፊት ያረፉትን የአባታቸውን ፊታውራሪ ገብረአምላክ ውብነህ ማዕረግን የያዙት ፊታውራሪ በላይነሽ፣ ከድል በኋላ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ዘንድ በቀረቡበት ጊዜ፣ ጃንሆይ ‹‹ጄኔቭ በነበርንበት ጊዜ፣ በላይነሽ የምትባለው ሴት ትዋጋለች እየተባለ የምንሰማው እሷን ነው?› ብለው ጠየቁ፡፡ ደጃዝማች ይገዙም ‹አዎ› ብለው አቀረቡኝ፡፡ ጃንሆይም በፈገግታ ተቀበሉኝ፡፡ ‹አለሽ እንዴ! ማን ትባያለሽ?› አሉኝ፡፡ እኔም፣ ‹ፊታውራሪ በላይነሽ ነኝ› አልኳቸው፡፡ ‹በስምሽ ተጠሪበት› ብለው ሹመቱን አፀደቁልኝ፡፡››
ፋሺስት ኢጣሊያ ኢትዮጵያን ሲወር ባለቤታቸው በጅጅጋ በኩል ወደ ጂቡቲ ለስደት እንዲሄዱ ቢገፋፏቸው አገራቸውን ትተው እንደማይሄዱና ተጋድሏቸውን እንደሚቀጥሉ ነግረዋቸው የተለዩዋቸውን እኚህን እርመኛ አርበኛ የቴምብሩ ገበታ ሊረሳቸው ባልተገባ ነበር፡፡
አደራ ተረካቢ ወካይ የሆኑ ወጣቶችን ጨምሮ በስድስት ዓይነት የታተሙት 600 ሺሕ ቴምብሮች ሲሆኑ፣ የያንዳንዱ ዋጋም ከ1 ብር እስከ 1.50 ብር መሆኑ ታውቋል፡፡   
በዳግማዊ ምኒልክ ዘመን (1888 ዓ.ም.) ዓድዋ ላይ ድል የተመታው የኢጣሊያ ወራሪ ሠራዊት፣ ከ40 ዓመት ቆይታ በኋላ በፋሺስቱ ቤኔቶ ሙሶሎኒ አማካይነት ኢትዮጵያን መውረሩና በተለይ በዓለም የተከለከለው የመርዝ ጋዝ በመጠቀም የኢትዮጵያን ሠራዊት በ1928 ዓ.ም. መፈታቱ ይታወሳል፡፡
እርመኛ አርበኞች የአገሪቱን ነፃነት ለማስከበር የሕዝቡን ልዕልና ለማስጠበቅ መራር ተጋድሎ ማድረጋቸውም ባይዘነጋም የፋሺስት ወንጀለኞች በታኅሣሥ 1928 ዓ.ም. የኢትዮጵያን ሠራዊት የፈቱበት፣ በተምቤንና በሐሸንጌ በመርዝ ጋዝ ያደረሱት እልቂት ይጠቀሳል፡፡
ከሰባ አምስት ዓመታት በፊት የድሉን ብሥራት አስመልክተው ባለቅኔው የእንጦጦ ራጉኤሉ ብርሃኑ ድንቄ (ከስድስት አሠርታት በፊት በአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር የነበሩ) ግእዝ ከአማርኛ አጣቅሰው እንዲህ ተቀኝተው ነበር፡-
‹‹ኢትዮጵያ ከማር ለሚጣፍጥ ለስምሽ አጠራር ሰላም ይገባል፡፡
ባምላክ እጅ ለተሠራ ለራስ ፀጉርሽም ሰላምታ ይገባል፡፡
ምሳሌ የሌለሽ መቅደስ ኢትዮጵያ፤
ጠላት ኢጣሊያ ስላረከሰሽና መሠዊያሽን ስላጠፋ ፈንታ፣
ከእንግዲህ ወዲህ ተቀደሽ፣ ኃይልንም ገንዘብ አድርጊ፡፡››
እኚሁ ሊቀ ሊቃውንት ብርሃኑ ድንቄ እንዲህ እያሉም ዘመሩላት፡፡
‹‹እናታችን ኢትዮጵያ ሆይ
ለታረዙ ልብስ ነሽና
በባንዲራሽ ጥላ ሰብስቢ ልጆችሽን!››

Saturday, November 12, 2016

Ethiopian athletics great, Gebrselassie, receives lifetime achievement award

Haile Gebrselassie, Ethiopia’s athletics great, has been given the Lifetime Achievement Award from the Association of International Marathons and Distance Races (AIMS).
Haile – who is the new President of the Athletics Federation – received his award at an event organized on Friday in the Greek capital, Athens.
“What an honor to receive the AIMS Lifetime Achievement Award in Athens tonight, thank you!” Haile tweeted after the award.
We are honoured to be able to recognise the achievements of Haile Gebrselassie and his unrivaled contribution to the Marathon Movement and world sport.
AIMS President Paco Borao is quoted to have said “We are honoured to be able to recognise the achievements of Haile Gebrselassie and his unrivaled contribution to the Marathon Movement and world sport. Haile’s success has been an inspiration to so many throughout Africa and around the world and his dedication is an example we can all follow.”
AIMS has previously presented Haile with the AIMS World Athlete of the Year Award for three consecutive years between 2006 and 2008.
Gebrselassie, has brought the country a lot of glory in long-distance events had a stellar career which spanned over two decades, since 1992 when he won the 5000m and 10,000m titles at the World Junior Championships.
Over the duration of his active days, he set 27 world records and 61 Ethiopian records, as well as win two Olympic gold medals and eight world titles both indoors and out.
In addition to his athletics career, Haile is also a businessman and employs more than 2000 people in several businesses back home. Local media reports that he is involved in real estate projects, owns four hotels, a coffee plantation and is the distributor for Hyundai in Ethiopia.
He is also a goodwill ambassador for the United Nations and is involved in tree planting and road projects. He has built several schools in his residential area.
 http://www.africanews.com/2016/11/12/ethiopian-athletics-great-gebrselassie-receives-lifetime-achievement-award/

Haile Gebrselassie to receive more honours

Tuesday, November 8, 2016

Gebrselassie elected new President of Ethiopian AthleticsBy sportsnewsarena correspondent
Nov 06, 2016
  • Haile Gebrselassie in an interview with Sports News Arena at his home in Addis Ababa in 2014.(Photo SNA File)
Long distance legend Haile Gebrselassie was on Saturday elected the new President of the Ethiopian Athletics Federation in Addis Ababa.
The double Olympic champion in the 5000 and 10000m secured 9 of the 15 votes and immediately promised to work on a great future for Ethiopian Athletics.
“I feel so honoured to be elected president of the Ethiopian Athletics Federation. I will work on a great future for Ethiopian athletics,” said the 43-year old after his election.
He will be deputised by Dr Bezabih Wolde. The former world marathon record holder takes over from long-serving president Bisrat Gashawtena. Her deputy Nega Gebre-Egziabher also failed to recapture his seat.
“I am very honoured that they trust me in this position. I am looking forward to working together with all people involved in the EAF to work on a great future for Ethiopian athletics,” he said after his election.
Double Olympic silver medallist Sileshi Sihine was elected the Ethiopian athletes’ leader and will be assisted by Meseret Defar, Olympic gold winner in London and Athens.
Other members of the Ethiopian Athletics Federation include Dr Gatlok who will represent Gambella Region, athlete Gebreegzabher Gebremariam who will represent the Tigray region, Ato Farid Mohamed who will sit as the delegate from the Harari region.
Ato Belayneh Kinde was voted as the area representative from Amhara region, Ato Admassu Sajin was voted as the member from South region.
Gebrselassie’s march to the Ethiopian presidency gained momentum in July when he led a protest by local runners to the Federation office, incensed by the Rio marathon selection process.
The runners argued the selection fro Rio was biased, with the legendary runner particularly concerned with the exclusion of the 2016 Berlin marathon champion Kenenisa Bekele.
Since announcing his retirement earlier in the year the gold medal winner from Atlanta and Sydney has focussed on growing his businesses across the horn African nation.
The long distance track and road runner is considered one of the richest men in Ethiopia, a one party state, which has recently been experiencing a new round of unrest with thousands of campaigners including leading athletes, calling for a regime change.
Gebrselassie, who won nine marathon has interests in real estate, gold mining, car dealership, coffee farming among others.
He also organises the largest annual 5 and 10km runs in his country dubbed the Great Ethiopian run.

‹‹ኢትዮጵያ ንቂ…››

‹‹ኢትዮጵያ ንቂ…››
ኢትዮጵያውያን በተለያዩ ጉዳዮች በራሳቸው ይመካሉ፡፡ ከነሱም ሌላ በኢትዮጵያ የሚመኩ አሉ ብዙ ጥቁር ሕዝቦች፡፡ ከነዚህ ውስጥ ከሰሜን አሜሪካ በስተደቡብ በሚገኙ ደሴቶች ውስጥ የሚኖሩት የዌስት ኢንዲያን ጥቁሮች ናቸው፡፡ በተለይም ደግሞ ጃማይካውያን፡፡ እነዚህ በራስ ተፈሪ ስም ራስ ተፈሪያን የሚባል ቡድን አቋቁመው ኢትዮጵያ መመኪያ ሀገራቸው እንደሆነች ይከራከራሉ፡፡ አብርሃም በእግዚአብሔር ጥሪ ከከሃዲዎቹ ሀገር ከካራን ወጥቶ ወደ ተስፋይቱ ወደ እግዚአብሔር ሀገር ወደ ከነዓን እንደሄደ የነሱም የተስፋ ምድራቸው ሀገር እግዚአብሔር ኢትዮጵያ እንደሆነች ይናገራሉ፡፡ ለዚህም ነው በሕይወታቸውና የሕይወታቸው መግለጫ በሆነው በሥነ ጽሑፋቸው ውስጥ ኢትዮጵያ ገንና የምትገኘው፡፡
ዌስት ኢንዲያንስ ምንጫቸው አፍሪካ እንደሆነች ያምናሉ፡፡ የማንነታቸው መገኛ እንደምትሆንም ይገምታሉ፡፡ በአ.አርዳቶርኔ መጽሐፍ ‹‹The scholar Man›› ውስጥ ያለው የዩኒቨርሲቲ አስተማሪ አዳም ኩየስተስ የማንነቱን ጉዳይ አንስቶ ሲናገር ‹‹የራሴ ታሪክ ኖሮኝ  እንዳደገ ሰው ስለራሴ ምንም ነገር አላውቅም፡፡ የማውቀው ያልሆንኩትን ብቻ ነው፡፡ እንግሊዛዊ አይደለሁም እንደምገምተው እንዲያውም ዌስት ኢንዲያንም አይደለሁም›› ይላል፡፡ ትግሉ ማን እንደሆነ ለማወቅ ነው፡፡
በዚህ የማንነት ፍለጋ ውስጥ ነው አፍሪካ በተለይ ደግሞ ኢትዮጵያ የማንነታቸው ተምሳሌት ሆና በየድርሰቶቻቸው ውስጥ የምትገለፀው፡፡ በሲልቪያ ዋይንተር በተጻፈው ‹‹The Hills of Hebron›› በሚለው ድርሰት ውስጥ ፀጉሩ የተንዠረገገውና ፂማሙ ራስታ ሲታሠር በፖሊስ መኪና ፊት ተንበርክኮ በጥልቅ ስሜት፤
ኢትዮጵያ ንቂ የልጆችሽንም ጩኸት አድምጪ
ኢትዮጵያ ዛሬ ነፃ ናት፤ የኛም ለቅሶ በምድሪቱ ያስተጋባል
ኢትዮጵያ ንቂ፣ ንጋታችን በእጃችን ናትና፡፡ እያለ ይዘምራል፡፡ ‹‹The children of sisyphus›› በሚለው በኦርላንዶ ፓተርሰን ድርሰት ውጥ ያለው የራስ ተፈሪያውያን መሪ ወንድም ሰሎሞን ደግሞ የኃይለሥላሴ መንፈስ እንዳደረበት ጥቁር ሙሴ ይቆጠራል፡፡ የራስ ተፈሪያውያን ተከታይ ሴቶች ስለኒህ የኢትዮጵያ ንጉሥ እንደሚከተለው ይናገራሉ፡፡
‹‹በነሱ እኩይ መንገድ እኛን ሴቶችን ያረከሱንን ነጫጮቹን ውሾችና ቡናማዎቹን ከሃዲዎች የእኛ ጥቁር አምላክ፣ እውነተኛ የእስራኤል ልጆች፣ የጥቁር ንጉሥ ሰለሞንና የጥቁሯ ንግሥት ሳባ ዘሮች ያቃጥሉልናል፡፡
ይኸው ወንድም ሰለሞን ስለጥቁሮች በደል ‹‹አዎ ወንድሞቼ! ነገር ግን አሁንም ከኛ የደበቁት ከሁሉም በላይ በጣም ጠቃሚ የሆነ ሌላ ነገር አለ፡፡ ይህም ያ ሰው አምላክ ነው፡፡ የራስ ተፈሪ መንፈስ ስለምንፈልገው በሁላችን ላይ አርፏል፡፡ ይህ ይህ ነው ወንድሞቼ ነጮቹ ሰዎች በእሱና በኛ ላይ የፈፀሙት የከፋ ሀጢአት፡፡ ይህንንም ቡናማዎቹ አጋሮቻቸው አሁንም ያስተጋባሉ፡፡ በማለት ብቸኛው መፍትሔያቸው ወደ ኢትዮጵያ መመለስ መሆኑን ይሰብካል፡፡ በዚሁ ገጽ ላይም ኢምፔሪያሊዝም ነጮችንም ጥቁሮችንም ባርያ እንዳደረጋቸውና እንግሊዝን ያገነናትና ለዚህ ያበቃትም የጥቁሮች ላብ መሆኑን ይዘረዝራል፡፡
-    ገዛኸኝ ጌታቸው ‹‹ኢትዮጵያ በዌስት ኢንዲስ ሥነ ጽሑፍ›› (1992)