‹‹ክኣትዋ ደሞ ሸገይ ወሊዐየ
ክኣትዋ ደሞ መስቀላይ ሒዘየ››
ልግባ ወይ ችቦዬን ለኩሼ
ልግባ ወይ መስቀሌን ይዤ፤ እያሉ
አንድም በዜማ፣ አንድም እንደወግ እያሰማመሩ የሚጫወቱት ዓዲግራቶች ናቸው፡፡ ዘንድሮም እንደሁሌው የመስቀል በዓል በመጣ ቁጥር የሚያቀነቅኑት በተድላና ደስታ ነው፡፡
የምሥራቅ ትግራይ ዞን (በቀድሞው አጠራር የዓጋመ አውራጃ መዲናዋ ዓዲግራት በዓለ መስቀል በድምቀት ከሚከበሩባቸው አካባቢዎች አንዷ ናት፡፡ ሁሌም እንደሚደረገው በዓዲግራት ከተማና በገጠር የመስከረም ወር ከባተበት ጀምሮ ለመስቀል በዓል የሚደረገው ዝግጅት ደመቅ ያለ ነው፡፡ ከሕፃን እስከ አዋቂ፣ ከደቂቅ እስከ ልሂቅ ወንድም ሴቱም እንደየድርሻው ይሳተፋል፡፡
የዓዲግራት የመስቀል አከባበር እንደ አንዳንዶች ለየት የሚያደርገው በዋዜማው መስከረም 16 ቀን አመሻሽ ላይ ከከተማው ምዕራብ ጥግ ቀንዳዕሮ ከሚባለው ተራራ ላይ የተለኮሰውን ችቦ ኅብረተሰቡ እያበራ መውረዱ ነው፡፡ በተለይ ወጣቶች የችቦ ብርሃን ይዘው ‹‹ሆያየ ሆየ! ሆየ…›› እያሉ መውረዳቸው ልዩ ድባብ ይሰጠዋል፡፡ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ አነስተኛ መስቀል ተተክሎበት የነበረው የቀንዳሮ ጫፍ ዘንድሮ 22 ሜትር ርዝመት 8 ሜትር ጎን ያለው አዲስ መስቀል ተተክሎበታል፡፡ ለባለሰባት ቶን ክብደት ግንባታ የወሰደው ወጪ 1.4 ሚሊዮን ብር መሆኑን የከተማው የሕዝብ ግንኙነት ጽሕፈት ቤት አስታውቋል፡፡ በሰሜን ኢትዮጵያ አካባቢዎች ባለው ትውፊት መሠረት የመስቀል ደመራ በሃይማኖታዊ ሥነ ሥርዓት የሚለኮሰው መስከረም 17 ቀን በመሆኑ ዓዲግራቶችም በወልዋሎ ስታዲየም ማክሰኞ መስከረም 17 ቀን 2009 ዓ.ም. በተመሳሳይ ሥርዓቱን ፈጽመዋል፡፡ (ሔኖክ ያሬድ ከዓዲግራት)

- ሔኖክ ያሬድ's blog
- 111 reads
No comments:
Post a Comment