በሔኖክ ያሬድ
ነፃ ፕሬስ ነፃ ሐሳብ ነፃ መንፈስ www.ethiopianreporter.com FREE PRESS FREE SPEECH FREE SPIRIT
ነሐሴ 2 ቀን 2004
ነፃ ፕሬስ ነፃ ሐሳብ ነፃ መንፈስ www.ethiopianreporter.com FREE PRESS FREE SPEECH FREE SPIRIT
ነሐሴ 2 ቀን 2004
“የኦሊምፒክ
ማራቶንን ማሸነፍ ለእኔ በጣም ልዩ ነው፤ ማራቶን ሕይወቴ ነው፤እኛ ኢትዮጵያውያን ማራቶንን እንደ ብሔራዊ ስፖርት እናየዋለን፡፡
በመሆኑም ወርቁ ለኢትዮጵያ ትልቅ ዋጋ አለው፤” በማለት የተናገረችው አዲሷ የማራቶን ጀግና ቲኪ ገላና ናት፡፡
ለንደን
ላይ እየተካሔደ ባለው 30ኛው ኦሊምፒያድ የሴቶች ማራቶንና ኢትዮጵያ ከተለያዩ ከ16 ዓመታት በኋላ ዳግም እንዲገናኙ ያደረገችው
ቲኪ ገላና ድሏን ያጣጣመችው የኦሊምፒክን ክብረ ወሰን በመስበር ጭምር ነው፡፡ ውድድሩን በ2 ሰዓት ከ23 ደቂቃ ከ7 ሰከንድ በመፈጸም
በሲዲኒ ኦሊምፒክ ጃፓናዊቷ ናኦኮ ታካሺ በ2 ሰዓት 23 ደቂቃ 14 ሰከንድ የያዘችውን ክብረወሰን በሰባት ሰከንድ አሻሽላዋለች፡፡
ቲኪ ፋጡማ ሮባ በ1988 ዓ.ም. አትላንታ ላይ ያስገኘችውን የመጀመርያውን የማራቶን ወርቅ ዳግመኛ ወደ አገሯ በማምጣቷ ልዩ ስሜት
እንደፈጠረባት ከውድድሩ በኋላ ለዜና ሰዎች ተናግራለች፡፡
“ፋጡማ
የእኔ ምልክት፣ የእኔ አርዓያ ናት፡፡ ከልጅነቴ ጀምሮ ታሪኳና ድሏን ስከታተል ነበር፤” ብላለች፡፡
በአርሲ
በቆጂ ጥቅምት 12 ቀን 1980 ዓ.ም. የተወለደችው ቲኪ ሩጫን እዚያው ትውልድ ቦታዋ በምትማርበት ትምህርት ቤት የጀመረች ሲሆን፣
በ1997 ዓ.ም በታላቁ ሩጫ ተካፍላ 4ኛ ሆና ፈጽማለች፡፡
በተከታታይ
ዓመታትም በትራክ በ3000 ሜትር፣ በ5000 ሜትርና በ10000 ሜትር፣ በጎዳና ላይ ከ10 ኪ.ሜ እስከ 30 ኪ.ሜ ባሉ የተለያዩ
ርቀቶች፣ ግማሽ ማራቶንና ሙሉ ማራቶን ሮጣለች፡፡
እ.ኤ.አ.
በ2009 በደብሊን ማራቶን 3ኛ፣ በ2010 በሎስ አንጀለስና ደብሊን በተካሄዱትም የማራቶን ውድድሮች 4ኛ ሆና አጠናቃለች፡፡ በጊዜውም
ምርጥ ሰዓቷ 2 ሰዓት ከ29 ደቂቃ 53 ሰከንድ ነበር፡፡ የማራቶንን ድል መጨበጥ የጀመረችው እ.ኤ.አ. በ2011 የአምስተርዳም
ማራቶን ሲሆን፣ 2 ሰዓት 22 ደቂቃ 08 ሰኮንድ በመፈጸም ቀድሞ ከነበራት ሪከርድ 8 ደቂቃ ያህል አሻሽላለች፡፡ ይህም ጌጤ ዋሚ
ለዘጠኝ ዓመት ይዛው የነበረውን ብሔራዊ ክብረወሰን ያሻሻለችበት አጋጣሚ ነው፡፡ ከስኬት ጫፍ የደረሰችበት ደግሞ ዘንድሮ በተካሔደው
የሮተርዳም ማራቶን 2 ሰዓት 18 ደቂቃ 58 ሰከንድ በሆነ ጊዜ በመፈጸም በራሷ የተያዘው ክብረወሰንን መስበሯ ነው፡፡ ይህም በማራቶን
አራተኛው የዓለም ምርጥ ጊዜዋ ሆኖ ተመዝግቦላታል፡፡
የሐምሌ
29 ቀን 2004 ዓ.ም. የለንደን ኦሊምፒክ ማራቶን ፍፃሜውን ያደረገው እንደሌሎች ኦሊምፒያዶች ስታዲየሙ ውስጥ አልነበረም፡፡ አዲሷ
ጀግና ቲኪ ገላና “የማራቶን ንግሥት የሆነችውና ወርቅ ያጠለቀችው ከእንግሊዟ ንግሥት ቤተ መንግሥት አካባቢ ነው፡፡ የሮም ኦሊምፒክ
የአበበ ቢቂላ የማራቶን ድልም ተጀምሮ ፍፃሜውን ያገኘው በኮንስታንቲን ቅስት አካባቢ ጎዳናው ላይ ነበር፡፡
የሴቶች
ማራቶን ለመጀመርያ ጊዜ የኦሊምፒክ ውድድር የሆነው ከ28 ዓመት በፊት በሎስ አንጀለስ ኦሊምፒክ ሲሆን፣ የመጀመርያዋ አሸናፊ አሜሪካዊቷ
ጆአን ቤኖይት ነበረች፡፡ እስከ ዘንድሮ የለንደን ኦሊምፒክ ስምንት ጊዜ ተካሒዶ ሁለት ሁለት ጊዜ ያሸነፉት ኢትዮጵያና ጃፓን ናቸው፡፡
የሯጮች
መፍለቂያና የአትሌቶች መናኸርያ የሆነችው በቆጂ አሁንም ከዋክብትን ማፍራቷን ቀጥላለች፡፡ ደራርቱ ቱሉ፣ ፋጡማ ሮባ፣ ገዛኸኝ አበራ፣
ቀነኒሳ በቀለ፣ ጥሩነሽ ዲባባና እህቶቿን ለሻምፒዮናነት፣ ለኦሊምፒክ ባለወርቅነት እንዳበቃች ሁሉ ወጣቷን አዲሷን ጀግና ቲኪ ገላናን
እነሆ ብላለች፡፡
No comments:
Post a Comment