አየለ ሰይፉ፣ ከአዲስ አበባ
የሎንዶኗ ልዕልት ሙጫዮ ዲባባ
ሲያዩዋት ትንሽ ነገር ሆድ የምታባባ
ረጃጅሞቹን ቀድማቸው ስትገባ
ስትከተል ኋላ ለድል ስታደባ፤
ኧረ ኧረ ቀረች ብለን ትዕግስት ስናጣ
ድንገት ፈትለክ ብላ ቀድማ ስትወጣ
በአስገራሚ ርቀት ድንቅ ተፈትልካ
ተመልካችንና ወገን ስታረካ
ምን ይባላል ይኼ ቃልና ተግባር
ታይቶ ሲተገበር በነጮች አገር
ይፍረደን ያለችው ሜዳው ይመስክር፤
‹‹ፈረዳንስ ኩን ለፋንስ ኩን›› ብላ
ሕያው ቃሏ ሕያው ፎካሪ አስከትላ
ታየች ያች ኮከብ አብርታና ደምቃ
ልብ አስፈነደቀች ዓለም አስደንቃ፡፡
ሐምሌ ሃያ ሰባት ያየሁት ሩጫ
ምክንያቱን ሳላውቀው በዲባባ ሙጫ
ልቤ ተነካና ስሜቴ ፈንድቶ
ዕንባዬ ወረደ ሳላውቀው አቁቶ፤
እሰይ ተመንደጊ በበረከት ትሪ
ጥሩነሽ ዲባባ ይገባል ልትኮሪ፡፡
No comments:
Post a Comment