ሲጠበቅ
የነበረው ተናፋቂው የኦሊምፒክ ጨዋታ በለንደን አስተናጋጅነት ከትናንትና በስቲያ (ሐምሌ 20፣ 2004) አሐዱ ብሏል፡፡ 17 ቀናት በሚዘልቀው 30ኛው
ኦሊምፒያድ 64 አባላት ያሉት የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ቡድን ተሳታፊ ነው፡፡ በርካታ ወጣት አትሌቶች በተካተቱበት፣ ለመጀመርያ
ጊዜም ሁለት ዋናተኞችን የያዘው ቡድን ቀደምት የኦሊምፒክ ድሉን ለመቀጠል አልሟል፡፡ በኢትዮጵያ ኦሊምፒክ የ56 ዓመት ታሪክ እንደ
ማሞ ወልዴ ሁሉ በአራት ኦሊምፒያዶች የተወዳደረው የሁለት ኦሊምፒክ አትላንታና ሲድኒ የ10ሺሕ ሜትር ባለወርቁ በኩሩ (ዘ ሌጀንድ) ኃይሌ ገብረ ሥላሴ፤ በአቴንስና ቤጂንግ ኦሊምፒክ
10ሺሕ ሩጫ 5ኛና 6ኛ የወጣው በኩሩ ኃይሌ፣ ዘንድሮ ለአምስተኛ ጊዜ ለመወዳደር ያለመው ሳይሆንለት ቀርቷል፡፡ በተለይ የአበበ
ቢቂላ፣ ማሞ ወልዴና ገዛኸኝ አበራ የማራቶን አራት ወርቆች ላይ ሌላ የወርቅ ታሪክ ለማምጣት ያሰበው ባይሆንለትም፣ ለንደን
ኦሊምፒክ ጎዳና ላይ እንዲሮጥ ያስቻለው ሌላ ዕድል ግን አላመለጠውም፡፡ የኦሊምፒክን ችቦ ይዞ በመሮጥ የቅብብሎሹ ባለታሪክ
ሆኗል፡፡ (በሔኖክ
ያሬድ)
No comments:
Post a Comment