የኢትዮጵያ
ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በልሳነ ግእዝ እና በአፋን ኦሮሞ (ግእዚፊ አፋን ኦሮሞቲን- Giiiziifi Afaan
Oromootiin) ያዘጋጀችውና 14ቱን መጽሐፈ ቅዳሴ የያዘው ‹‹መጽሐፈ ቅዳሴ -ክታበ ቅዳሴ- Kitaaba Qiddaasee››
መጋቢት 10 ቀን 2008 ዓ.ም. በኢሊሌ ሆቴል ተመረቀ፡፡
ባለ
ሦስት ዓምዱ (ኮለም) መጽሐፈ ቅዳሴ፡- የመጀመርያው ረድፍ በግእዝ ቋንቋ፣ ሁለተኛው ረድፍ በኦሮምኛ ሆኖ በሳባ (ግእዝ) ፊደል፣
ሦስተኛው ረድፍ በኦሮምኛ ሆኖ በቁቤ ፊደል ተጽፏል፡፡ ‹‹የኦሮሞ ብሔረሰብ ምእመናን ልጆቻችን በአሁኑ ወቅት በአፍ መፍቻ ቋንቋቸው
አምልኮአቸውን መፈጸም እንዲችሉ፣ በቋንቋቸውም እንዲያስቀድሱና እግዚአብሔርን
እንዲያመሰግኑ ተተርጕሟል፤›› ያሉት መጽሐፉን የመረቁት ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ፣ ‹‹የኦሮሞ ክልል ምእመናን ልጆቻችን እንኳን
ደስ አላችሁ እንላለን፤›› ብለዋል፡፡ በሥነሥርዓቱ ላይ የቀድሞው ፕሬዚዳንት ግርማ ወልደ ጊዮርጊስ ተገኝተዋል፡፡
No comments:
Post a Comment