‹‹ዮሐንስን ጥሩ እሱ ይያዘኝ
እስኪ ካሳን ጥሩ በል አንተ ያዘኝ
ቴዎድሮስን ወስዶ ካሳ አንተ ሰጠኝ
እስኪ ካሳን ጥሩ በል አንተ ያዘኝ
ቴዎድሮስን ወስዶ ካሳ አንተ ሰጠኝ
እጅግ ደስ ይለኛል ያንተ ስም ሲነሣ
የቁና ዐፈር ንፉግ አንተ ነህ ወይ ካሳ››
ከ80 ዓመታት በፊት ታዋቂው ሠዓሊ አገኘሁ እንግዳ ከ127 ዓመታት በፊት በኢትዮጵያና ሱዳን ድንበር መተማ ላይ ሰማዕት ለሆኑት አፄ ዮሐንስ ራብዓዊ (አራተኛ) የተቀኙት ቅኔ ነው፡፡
‹‹የኢትዮጵያ ድምፅ›› በሚል በ1928 ዓ.ም. በሠዓሊው የተጻፈው ተራኪ ግጥም ከአፄ ቴዎድሮስ እስከ አፄ ምኒልክ ድረስ ይዘልቃል፡፡ ለዘመናዊት ኢትዮጵያ፣ ለ19ኛው ምእት ዓመቷ ኢትዮጵያ በር ከፋች የነበሩት በዱሮ ስማቸው ካሳ ኃይሉ፣ በንግሥና ስማቸው አፄ ቴዎድሮስ ዳግማዊ (ሁለተኛ)፣ ለአሐዳዊት ኢትዮጵያ መነሣት በቀዳሚነት ሲጠቀሱ፤ ማዕከላዊው መንግሥት ተጠናክሮ ፌዴራላዊ በሚመስል መልኩ ለአካባቢያዊ ገዢዎች ሥልጣን በመስጠት አሐዳዊቷን ኢትዮጵያ አጠናክረው ብቅ ያሉት ደግሞ በዱሮ ስማቸው ካሳ ምርጫ በንግሥና ስማቸው አፄ ዮሐንስ ራብዓዊ (አራተኛ) እስከ መጠርያቸው ‹‹ንጉሠ ጽዮን ንጉሠ ነገሥት ዘ ኢትዮጵያ›› ናቸው፡፡
አገኘሁ ከመጀመርያው ካሳ (ቴዎድሮስ) በኋላ ከተክለ ጊዮርጊስን ቀጥሎ የመጡትን ካሳ (ዮሐንስ) መተማ ላይ የፈጸሙት ጀብዱና የከፈሉትን ሰማዕትነት በ17 ዓመት የሥልጣን ዘመናቸው ሉዓላዊት ኢትዮጵያን በማጠናከራቸው፣ በኢትዮጵያ ድምፅነት ‹‹ዮሐንስን ጥሩ እሱ ይያዘኝ
እስኪ ካሳን ጥሩ በል አንተ ያዘኝ
ቴዎድሮስን ወስዶ ካሳ አንተ ሰጠኝ›› ብለው ስንኞችን አሰሩ፡፡ ከ127 ዓመት በፊት በመጋቢት መባቻ ዕለት መተማ ላይ ሰማዕት መሆናቸውንም ተከትሎም አገኘሁ ተራኪ ግጥማቸውን
‹‹ዮሐንስ ካሳህን ማን ሊችለው ነው፣
ከዘውድ ይልቅ ሞትክን አንተ የመረጥኸው
እንዳንተ ለድርጎ ዐፈር ንፉግ ሰው የለም፣
በደምበር ላይ ብትሞት አይደነቅም፤›› ብለው ዘለቁበት፡፡
እንደ አገኘሁ እንግዳ ምሥጠራ የአገሬን አፈር ባዕድ ይዞት አይሄድም ብለው እግር ያሳጠቡት አፄ ዮሐንስ በደምበር ላይ መሞታቸው መደነቅ ሳይሆን ለድርጎ አፈር ንፉግ ሆነው መገኘታቸውና ‹‹እምቢ ለአፈሬ›› ማለታቸውንና ታላቅነታቸውን ያጎሉበት ስንኝ ነው፡፡
(ሔኖክ መደብር )

No comments:
Post a Comment