የጥር
ወር መገባደጃ ላይ ያገኘኋት ዕለተ ሰንበት ልዩ ስሜት አሳድራብኝ አልፋለች፡፡ ሐሴትን ብቻ ሳይሆን ቅርታንም
ደብላብኛለች፡፡ የታላቁ ሰማዕትና ጳጳሱ አርበኛ ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ ሐውልት በባቡር መስመር ዝርጋታ ሳቢያ ከሥፍራው
ከተለየ ከሦስት ዓመት ግድም በኋላ ባማረ አደባባይ ሉዓላዊ በሆነ ሥፍራ ጥር 29 ቀን 2008 ዓ.ም. በታላቅ ሥነ
ሥርዓት በደማቅ ሥነ በዓል ተቀምጦ ሳይ ደስፈቅ (ደስታም ፍንደቃም) አድርጎኛል፡፡
ሐሩሩ በጠናበት ፀሓዩ ከነልጆቹ የወጣ በሚመስልበት የእሑድ ረፋድ እስከተሲኣት በዘለቀው የመልሶ ተከላውን ሁነት ባጀበው ሥነ ሥርዓት ላይ መገኘት ምንኛ መታደል ነው አሰኝቶኛል፡፡ በአደባባይ ዙሪያ ስመላለስ ከነቂስ መለስ ከወጣው እድምተኛ ፊት ይታይ የነበረው ፍካት በዕልልታ የታጀበና ልዩ ነበር፡፡ በአደባባዩ ከባልንጀሮቼና ከጓደኞቻቸው ጭምር ሳወጋ፣ ነገር በነገር ቢወሳ አይደንቅምና ሠላሳ ዓመት ወደ ኋላ የመለሰኝን ትውስታ አወጋሁላቸው፡፡
ማክሰኞ ሐምሌ 22 ቀን 1978 ዓ.ም. ከካዛንቺስ ለሥራ ተነስቼ ወደ መርካቶ ረፋድ ላይ ስዘልቅ የአዲስ አበባን የሕዝብ ማመላለሻ ትራንስፖርት እጥረትን ለማቃለል በድጋፍ ሰጪነት ከተሰማሩት ሎንቺናዎች በአንዱ ተሰቅዬ ጉዞ ጀምሬያለሁ፡፡ ፒያሳ ደጎል አደባባይን አልፈን በስተቀኝ ያ ድንቅ ተጫዋቾችን ያለማቋረጥ ያፈራ የነበረውን የማዘጋጃው የአራዳ ጊዮርጊስ ሜዳ (ያሁኑ ታጣሪው ሜዳ)፣ በስተግራ ‹‹ዘገየ ሕንፃ›› እንለው የነበረው በነሲኒማ ዓድዋ መቃብር ላይ እየተገነባ ግን ያልተገባደደውን ሕንፃ (ያሁኑ አራዳ ሕንፃ)፣ እንዲሁም ማዘጋጃ ሕንፃ በስተቀኝ አልፈን አቡነ ጴጥሮስ ሐውልት ከመድረሳችን በፊት ከርቀት ሰዎች ተሰባስበው ሳይ ምን ተፈጥሮ ይሆን ማለቴ አልቀረም፡፡ ቀረብ እንዳልኩ ‹‹ጫፍ ላይ አውርደኝ›› ብዬ ሥራዬን ትቼ ወደ ሐውልቱ ስጠጋ ያልጠበቅኩት ነገር አጋጠመኝ፡፡
የወቅቱ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ተክለሃይማኖት ከሊቃነ ጳጳሳትና ከካህናት፣ ከምዕመናንም ጋር ባንድነት ሆነው የአቡነ ጴጥሮስን ሰማዕትነት 50ኛ ዓመት በጠባቡ የሐውልቱ ቅጥር ውስጥ ሆነው እያከበሩት፣ እያሰቡት ነበር፡፡ ከሐውልቱ ግራና ቀኝ የነበሩት የኢትዮጵያ ራዲዮም ሆነ የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ትኩረት አለመስጠታቸውንም አስታውሳለሁ፡፡
ሁለተኛው ትውስታዬንም ከትዝታ ጓዳ መጨለፉን ቀጠልሁላቸው፡፡ ይኸ እንኳን ከስድስት ዓመታት በፊት የተከናወነ ነበር፡፡ ሐሙስ ሐምሌ 22 ቀን 2002 ዓ.ም. በአዲስ አበባ በ‹‹ባሕር›› አቅጣጫ (በሰሜናዊ ምዕራብ አቅጣጫ) ጉለሌ አካባቢ ካንድ ዐውደ ጥናት ተገኝቼ በ10 ሰዓት አካባቢ ወደ ፒያሳ ሳመራ ቀልቤን የገዛ ክስተት ተመለከትኩ፡፡ የቀድሞውን የኢትዮጵያ ራዲዮ ጣቢያ፣ የአሁኑን የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጋዜጠኝነትና ኮሙኒኬሽን ፋኩልቲ እንዳለፍኩ፣ በርካታ ሰዎች የተሰባሰቡበት ትዕይንት እየተካሄደ መሆኑን አስተዋልኩ፡፡
የአቡነ ጴጥሮስን ሐውልት ከከበቡት ሰዎች መካከል ልብሰ ጵጵስና የለበሱ ከመሐል ሆነው በርቀት ሲናገሩ ይታየኛል፤ የሚኒባስ ታክሲ ሾፌሩን እንዲያወርደኝ አድርጌ ታዳሚውን ተቀላቀልኩ፡፡ ዕለቱ አቡነ ጴጥሮስ ከ74 ዓመታት በፊት በፋሺስት ኢጣሊያ ወታደሮች ሰማዕት የሆኑበት ዕለት መሆኑንም አስታወሰኝ፡፡ ለካ ልብሰ ጵጵስና የለበሰው ወጣቱ ተዋናይ ነበር፡፡
ጸሐፌ ተውኔትና ባለቅኔው ሎሬት ፀጋዬ ገብረ መድኅን ከጻፋት ‹‹ጴጥሮስ ያችን ሰዓት›› ከተሰኘች ተውኔት አንዷን ቃለ ተውኔት እያላት ነበር፡፡ ዱሮ ወጋየሁ ንጋቱ፣ በኋላም አብራር አብዶ የተወኑትን ወጣቱ በተራው ተረክቦ በአደባባዩ እያስተጋባ ይለው ነበር፡፡
‹‹አዬ፣ ምነው እመብርሃን? ኢትዮጵያን ጨከንሽባት?
ምነው ቀኝሽን ረሳሻት?
እስከ መቼ ድረስ እንዲህ፣ መቀነትሽን ታጠብቂባት?
ልቦናሽን ታዞሪባት?
ፈተናዋን፣ ሰቀቀንዋን፣ ጣሯን ይበቃል ሳትያት?
አላንቺ እኮ ማንም የላት?››፡፡
ዘንድሮ በአጋጣሚ ሳይሆን አስቤና አልሜ በተገኘሁበት የአቡነ ጴጥሮስ ሐውልት ዳግም ተከላ ላይ ሎሬት ፀጋዬ ገብረመድኅን በሥራቸው ሕያው የሆኑበት ‹‹ጴጥሮስ ያቺን ሰዓት›› አንድ አንጓ አንድ ቃለ ተውኔት ታዋቂው አርቲስት አብራር አብዶ ሲተውነው፣ ሲያነበንበው ለጉድ ነበር፡፡ ብዙዎችን ያነቃቃ ነበር፡፡ የዕለቱን ሥነ በዓል ሲመራ የነበረው አስተዋዋቂ አጋፋሪነቱ የተሟላ እንዳይደለ ካሳበቁበት አንዱ ተዋናዩን አብራር አብዶ ብቻ ያጎላበት፣ ደራሲውን ፀጋዬ ሥራዎቹን ማስታወስ ቀርቶ ስሙን እንኳ ድርሰቱ የርሱ መሆኑን አለመጥቀሱ አስገምቶታል፡፡ (ምንም እንኳ ይህ ሥነ ግጥም የሎሬት ፀጋዬ መሆኑ በብዙኃኑ ቢታወቅም) በየአዳራሹ ሚሌኒየም ጨምሮ ለሌላ አግባብ የሚውለው 3፣2፣1 እያለ በተርታ መንገድ ሳይሆን የአቡኑን ዐውደ ታሪክ ባዛመደ መልኩ የሐውልቱን ገለጣ አጅቦ ቢሆን ኖሮ ምንኛ ባማረ፡፡ ምንኛስ በሰመረ፡፡
‹‹ነውን ለማወቅ ነበርን ጠይቅ›› እንዲሉ እንዲህ ያሉ ታላላቅ መድረኮች አጋፋሪ የሚሆኑ በጥንቃቄ መመረጥ ይገባቸው ነበር፡፡ አስተዋዋቂው ከመዘምራኑም ሆነ ከማርሽ ባንዱ ጋር ያለመናበብ ክፍተት መፈጠሩንም አይተናል፡፡ በደረቅ አማርኛ ‹‹መዘምራን አቁሙ›› ከማለት ይልቅ ‹‹የጀመራችሁትን ካበቃችሁ በኋላ ዕረፍት እንድታደርጉ እንጠይቃለን›› ቢል አይሻልም ኖሯል፡፡
እስከ ስምንት ሰዓት ሁሉ ነገር ይጠናቀቃል ተብሎ ወደ 10 ሰዓት ግድም እንዲዘልቅ ያደረገው የዲስኩር መብዛቱ ከአጋፋሪው ሌላ ዘጠኝ ንግግሮች መደረጋቸው ምነው አሰኝቷል፡፡ ከሁለቱ የሃይማኖት መሪዎችና ከአርበኞች ማኅበር ፕሬዚዳንት ሌላ ስድስቱ ያደረጉት ንግግር ተመሳሳይ ይዘት ብቻ ሳይሆን ቋንቋውም አንዳይነት ከሆነ፣ ምናለ በሁለት ተናጋሪ ተጠቅልሎ በአደባባይ ለተገኘው ኅብረተሰብ የሰማዕቱን አርበኛ ጳጳስ ታሪክና ተጋድሎ በ80ኛ ዓመቱ ላይ እጥር ምጥን አድርጎ ቢቀርብ ኖሮ የሚሉ አስተያየቶች ሲደመጡ ነበር፡፡
እንዲያውም በሥነ በዓሉ ከተገኙት ከ80 ዓመት በፊት አቡነ ጴጥሮስ ሰማዕት ሲሆኑ የ10 ዓመት ልጅ ሳሉ በዓይናቸው የተመለከቱት እማሆይ አበበች ኃይሌን ትውስታቸው እንዲናገሩ መጋበዙ ቀርቶ ከተቀመጡበት ድንኳን ውስጥ ‹‹ለእንግዶቻችን ልቀቁልን›› ተብለው ከአደባባዩ ጥግ እንዲቆሙ መደረጉ አቤት ጉድ አሰኝቷል፡፡
ይልቅስ ከስድስት ዓመት በፊት ያየሁት ታዳጊ ወጣት የባለቅኔው ሎሬት ፀጋዬ ‹‹አዬ፣ ምነው እመብርሃን? ኢትዮጵያን ጨከንሽባት?...›› የሚለውን መነባንብ የድል በዓል በያመቱ ሚያዝያ 27 ሲከበር አራት ኪሎ እየተገኘ እንደሚያቀርበው ለዚህኛውም ተጋብዞ ቢሆን ኖሮ ዳግም ተከላውን ምንኛ ባደመቀው ነበር፡፡
(ዞሲማስ ሚካኤል፣ ከራስ ሙሉጌታ መንገድ)

No comments:
Post a Comment