29 Jan, 2016
በአሁኑ
ወቅት የቤት ኪራይ ከምንም ነገር በላይ የብዙዎች ዋነኛ የኑሮ አጀንዳ ነው፡፡ ከዝቅተኛ ደረጃ እስከ ላይ ድረስ
የኪራይ ዋጋ ለተከራዮች ጉዳያቸው ብቻም ሳይሆን ራስ ምታታቸውም ጭምር ነው ቢባል ስህተት አይሆንም፡፡ የዚህ
ምክንያቱ ደግሞ በየጊዜው የዋጋ መጨመር፣ ቤት ልቀቁ መባል፣ የአከራዮች ቅድመ ሁኔታና የደላሎች ሚና ነው፡፡
በተቃራኒው በማከራየት ሒደት ዋነኛ ተዋናይ ለሆኑት ደላሎች ደግሞ የቤት ኪራይ ራስ ምታታቸው ሳይሆን ሎተሪያቸው መሆኑ ግልጽ ነው፡፡ ላለው ምክንያታዊ ያልሆነ የቤት ኪራይ የገበያ ዋጋ ብዙዎች ተጠያቂ የሚያደርጉት ደላሎችን ነው፡፡ አንዳንዶች ደግሞ ለቤት ኪራይ ብቻ ሳይሆን ደላሎች የሌሉበት ምንም ዓይነት እንቅስቃሴ ባለመኖሩ በአጠቃላይ ለኑሮ መወደድ የደላሎች ሚና ከፍተኛ መሆኑን ይደመድማሉ፡፡ ‹‹ደላሎች የሌሉበት እንቅስቃሴ ጠፍቷል፡፡ ምግብ መግዛትና ታክሲ መሳፈርም እንኳ በደላላ እየሆነ ነው፡፡ እነሱ የሚጨምሩት ምንም ዓይነት እሴት ግን የለም፤›› በማለት አስተያየት የሰጡም አሉ፡፡
እንደተባለው በብዙ መልኩ በተለያዩ እንቅስቃሴዎች የደላሎች ተፅዕኖ ከፍተኛ መሆኑ እየተስተዋለ ነው፡፡ እዚህ ላይ የኮንዶሚኒየም ቤት ኪራይ የደላሎች ወሳኝ የሥራ መድረክ ተደርጎ ሊታይ ይችላል፡፡ ከመደለል ባሻገር የባለቤቶች እንደራሴ ሆነው የሚንቀሳቀሱ ደላሎችም ጥቂት አይደሉም፡፡ እነዚህ ደላሎች ገበያውን ዓይተው የጓደኞቻቸውን ዕርምጃ እንደሚከተሉ፣ ዋጋ በመጨመር መሪ እንደሚሆኑም ብዙዎች ይናገራሉ፡፡
ለስድስት ዓመታት ገደማ ገርጂ ሰንሻይን አካባቢ ከሚገኘው ኮንዶሚኒየም ሳይት ተከራይቶ ኖሯል፡፡ በመጀመርያ ሲከራይ የገባው ስቱዲዮ ሲሆን፣ አሁን የሚኖረው ባለ አንድ መኝታ ኮንዶሚኒየም ውስጥ ነው፡፡ እሱ እንደሚለው ደላሎች ለባለቤቶች ዋጋ ያወጣሉ፣ በየጊዜውም እየደወሉ የገበያው ዋጋ መጨመሩን በመንገር ጭማሪ እንዲያደርጉ ያሳስባሉ፡፡ ይህም ብቻ ሳይሆን ከወራት በፊት ያስገቡትን ተከራይ የተሻለ ዋጋ የሚከፍል በማምጣት ያስወጣሉ፡፡ ይህን ሐሳቡን ሙሉ በሙሉ ብዙዎች ይጋሩታል፡፡
እሱን ያከራየው ደላላ እንዳከራየው በጥቂት ወራት ውስጥ ማረሚያ ቤት በመግባቱ እዚያው ሳይት ላይ የሚኖሩ ሌሎች የሚያውቃቸው ሰዎች ያስገቧቸው ደላሎች ያደረሱባቸው ዓይነት ጫና አልደረሰበትም፡፡ በርግጥ ይህ የሆነው ያከራየው ደላላ ለሁለት ዓመታት ሳይቱ ላይ ባለመኖሩ ብቻም ሳይሆን አከራዩ መልካም ሰው በመሆኗ ጭምር እንደሆነ ያምናል፡፡ ከረዥም ጊዜ በኋላ እዚያው አካባቢ ሲገናኙ ሰላም ብሎ አልፎ ተከራዩ እዚያው ያስገባው ቤት መሆኑን አረጋግጦ ወዲያው ለባለቤቱ ደውሎ በመንገር ለማስወጣት የሚንቀሳቀስ ደላላ ሁሉ አለ፤›› በማለት ደላሎች ዋጋ ለመጨመር የማያደርጉት ሙከራ እንደሌለ ይገልጻል፡፡
ምንም እንኳን የመጀመርያውን ዕርምጃ የሚወስዱት ደላሎች ቢሆኑም የኮንዶሚኒየም ባለቤቱም ኪራይ፣ የቤቱን ዕዳ የሚከፍልበት ኑሮውን የሚኖርበትም በመሆኑ መጨመሩን እንደማይጠላውና ከደላሎቹ ጋር እንደሚተባበር ይናገራል፡፡ አንዳንድ አከራዮች በተለያየ ምክንያት የሦስት ወይም የስድስት ወር ቅድሚያ የሚጠይቁ ቢሆንም እንደዚህ የወራት ቅድሚያ መጠየቅ ከተወሰነ ጊዜ ወዲህ የተለመደ አሠራር እየሆነ የመጣው በደላሎች ምክንያት እንደሆነም ያስረዳል፡፡ እሱ እንደሚለው ሌሎች እንደሚገልጹትም በዚህ የደላሎች ኮሚሽን የሚሰላው በተፈጸመው የወራት ክፍያ መሠረት ነው፡፡
ብዙ ባይሆኑም ጥቂት ኮንዶሚኒየም ሳይቶች ላይ የሚገኙ ኮሚቴዎችና ማኅበራት የቤት ኪራይ ሥርዓትን ፈር ለማስያዝ፣ የሚባለውን ያልተገባ የደላሎች ሚና ለመቀነስ ተንቀሳቅሰዋል፡፡ የኮሜት (ሳሪስ አቦ) ኮንዶሚኒየም ኅብረት ሥራ ማኅበር በዚህ ረገድ ሊጠቀስ ይችላል፡፡ የማኅበሩ ጽሕፈት ቤት አስተዳደር ኃላፊ አቶ እዮብ ኑሬ እንደገለጸው በሳይቱ 16 ብሎኮች ሲኖሩ 80 በመቶ የሚሆኑት ቤቶች የተከራዩ ሲሆኑ፣ ቀሪው 20 በመቶ የሚሆነው ባለቤቶች የሚኖሩባቸው ናቸው፡፡
በሳይቱ ደላሎች የማከራየት ሚና የላቸውም፡፡ ቤት ፈላጊ መከራየት የሚችለው ከመኅበሩ ጽሕፈት ቤት ተመዝግቦ ነው፡፡ ቤት ፈላጊዎች የሚፈልጉን ቤት ዓይነት ይናገራሉ፡፡ መታወቂያ የመሰሉ ማስረጃዎችን አሳይተው ስልካቸውን እንዲተው ይደረጋል፡፡ ተራቸው ሲደርስ ይደወልላቸዋል፡፡ መተዳደሪያ ደንብ ተሰጥቷቸው ሲስማሙ ውል ፈጽመው እንዲገቡ ይደረጋል፡፡ እዚያው ተከራይ የሆነ ሌላ ቤት ሲፈልግም እንዲመዘገብ ይደረጋል፡፡ ነገር ግን ቅድሚያ ይሰጠዋል፡፡ ከአሠራር ውጭ የቤት ባለቤቶች በፈለጉት ጊዜ የፈለጉትን ሰው የማስገባት መብት የላቸውም፡፡ እህትንና ወንድምን ማስገባት የመሰሉ ፍላጎች ሲኖሩ ኬዙ በልዩ ሁኔታ ይታያል፡፡ ይህም ቢሆን ግን ማኅበሩ የመታወቂያ ካርድን በመመልከትና በሌላም መንገድ እውነት እህት ወይም ወንድም መሆናቸውን እንደሚያረጋግጥ አቶ እዮብ ይናገራል፡፡
ይህ አሠራር የተዘረጋው ከ2005 ዓ.ም. ጀምሮ ነው፡፡ በማኅበሩ ጽሕፈት ቤት የቤት ባለቤቶች ፋይል በተደራጀ መልኩ ተቀምጦ ይገኛል፡፡ ማኅበሩ ለሥራ ማስኬጃና ለጽሕፈት ቤቱ ማስተዳደሪያ ይሆን ዘንድ በኪራይ ከአከራይም ከተከራይም አምስት በመቶ አምስት በመቶ ኮሚሽን የሚወስድ መሆኑን የሚናገረው አቶ እዮብ ደላሎች ግን ከሁለቱም ወገን አሥር በመቶ አሥር በመቶ ይወስዱ እንደነበር ያስታውሳል፡፡ ‹‹የምንቀበለው እያንዳንዱ ክፍያ በሕጋዊ ደረሰኝ የሚፈጸም ነው፡፡ በየወሩም ኦዲት ይደረጋል፡፡ ማኅበሩ በቦርድ የሚተዳደር ሲሆን፣ የቦርድ አባላት በየሁለት ዓመት የሚመረጡት ማንነታቸው ታውቆ ነው፤›› የሚለው አቶ እዮብ ማኅበሩ ሥራውን በግልጽ እንደሚሠራ ያስረዳል፡፡ ለምሳሌ ተራ ለደረሳቸው ሰዎች ስልክ የተደወለበት ሰዓት ይመዘገባል፡፡ ይህ አልተደወለልኝም ወይም ሌላ ነገር በማለት የሚፈጠርን ችግር ይፈታል፡፡
ከነዋሪዎች ለመረዳት እንደሞከርነው ከሌሎች ጋር ሲነፃፀር የቤት ኪራይ ዋጋ ጥሩ ሊባል የሚችል ነው፡፡ በግቢው ዋጋ ስቱዲዮ 22 ካሬ 2,000 ብር፣ ባለ አንድ መኝታ 36 ካሬ 3,000 ብርና ባለሁለት 48 ካሬ 4,000 ብር ይከራያል፡፡ የማኅበሩ ጽሕፈት ቤት አከራዮች የግቢውን ዋጋ መሠረት እንዲያደርጉ አስተያየት ከመስጠት ውጭ ዋጋ የማውጣት መብት ሙሉ በሙሉ የባለቤቱ ነው፡፡ ቢሆንም ግን የማኅበሩ አሠራር ባንድም ይሁን በሌላ መንገድ ከፍተኛ የዋጋ ጭማሬ እንዳይኖርና ወጥ ባልሆነ አሠራር ተከራዮች ላይ ሊፈጠር የሚችል ጫናን አስቀርቷል፡፡ አሠራሩ በብዙ መልኩ ለአከራይም ለተከራይም ጠቅሟል፡፡ በእርግጥ በተለያየ አጋጣሚ ባለቤቶች መብታችን ተነካ የሚል ቅሬታ ማንሳታቸው አልቀረም፡፡
በጀሞ፣ ጎፋና ጎተራ ኮንዶሚኒየም ሳይቶች ባለቤት በሆኑ አከራዮች እንደተገለጸልን በየጊዜው በደላሎች እየተደወለ ዋጋ እየጨመረ መሆኑ ይነገራቸዋል፡፡ ተከራይ እንደሚያመጡና በተሻለ ዋጋ እንደሚያከራዩ ቃል የሚገቡ ደላሎችም አሉ፡፡
በጀሞ ሳይት ባለ አንድ መኝታ ቤት የምታከራየው ባለቤት በቅርቡ ያጋጠማትን ነግራናለች፡፡ እዚያው ሳይት የምትኖረው ሌላ የራሷ ቤት ውስጥ ነው፡፡ አጠገቧ ያለን የሌላ ሰው ስቱዲዮም ኃላፊነት ወስዳ የምታከራየው እሷ ነች፡፡ ቀደም ሲል የነበሩት ተከራዮች ወጡና ደላላ አዲስ ተከራይ አመጣ፡፡ አዲሱ ተከራይ ለስቱዲዮ እንዲከፍል የተደረገው 2,500 ብር ነበር፡፡ እሷ እዚያ ሳይት ላይ የሚገኘውን ባለ አንድ መኝታ የምታከራየው በ2,100 ስለነበር በመገረም ደላላውን እንዴት ነው ነገሩ? ስትል ጠየቀችው፡፡ የደላላው መልስ ባለ አንድ የሚከራየው እንደዚያ እንዳልሆነ ስለዚህም 3,200 ብር የሚከፍል ተከራይ እንደሚያመጣ ነገራት፡፡ በቀጥታ ለተከራዮቿ የተነገራትን በመግለጽ ዋጋ እንደምትጨምር አሳወቀቻቸው፡፡ ኪራዩን ከ2,100 ወደ 2,800 ብር ከፍ አደረገችው፡፡ ይህን አጋጣሚ በመጥቀስ የቱን ያህልም የተከራይን ሁኔታ ላገናዝብ ቢባል ደላሎች የሚያቀርቡት ዋጋ የአከራዩን ልብ እንደሚያማልል ትናገራለች፡፡
በጎፋ ኮንዶሚኒየም ደላላ የሆነው አቶ ደሳለኝ ዘውዴ ደግሞ ምንም እንኳ የተወሰኑ ደላሎች ዋጋ በማስጨመር ተከራዮች እንዲወጡ፣ አከራዮችም በየጊዜው እንዲጨምሩ የሚያደርጉ ቢሆንም የቤት ኪራይ እንዲጨመር ማድረግ በዋነኝነት የአከራዮች ፍላጎት ነው በማለት ይከራከራል፡፡ እሱ እንደሚለው በሳይቱ ደላሎች ተከራይ ያመጣሉ የኮንዶሚኒየም ማኅበሩ ውል ያዋውላል፡፡ ተከራይ ለተዋዋለበት ለማኅበሩ፤ የደላላውን ደግሞ ለደላላው ኮሚሽን ይከፍላል፡፡ ተከራዩ ለሁሉቱም መክፈሉ ተገቢ ነው ብሎ እንደማያምን ግን ይህ ነው የሚባል አሠራር እስከሌለ እነሱ ምንም ማድረግ እንደማይችሉ ይናገራል፡፡
‹‹የቤት ኪራይን በተለይም ኮንዶሚኒየም እንዲጨምር ያደረገው የደላላ ሥራ ብቻ አይደለም፤ አንዳንድ ጊዜ ባለቤቶች የሚያስቀምጡት ዋጋ ለእኛም ለመናገር እንኳ ይከብደናል፤›› ይላል አቶ ደሳለኝ፡፡ የቤት ኪራይ ዋጋ እንዲጨምር የባለቤቶች ሚናም ከፍተኛ መሆንን በሚመለከት ጉለሌ ክፍለ ከተማ ውስጥ የሚገኘው የመድኃኒዓለም የጋራ መኖሪያ ቤቶች ማኅበር ሥራ አስኪያጅ አቶ ታደሰ አንተነህም የደላላውን አቶ ደሳለኝን ሐሳብ ይጋራሉ፡፡
የተጋነነ ዋጋ ማስቀመጥ፣ በመጀመርያ የሦስት ወይም የስድስት ወር ከተቀበሉ በኋላ ቅድመ ሁኔታ እያስቀመጡ በየጊዜ ተከራይን ማስወጣት በቤት ባለቤቶች በኩል ምን ያህል ዋጋ የመጨመር ፍላጎት እንዳለ እንደሚያሳይ አቶ ደሳለኝ ያምናል፡፡ በደላላዎች በኩል ደላሎች የሚፈልጉት የዕለት ገንዘብ ማግኘት ስለሆነ ዋጋ አከራይ የሚችለው ሆኖ የድርሻውን አግኝተው ቢወጡ እንደሚመርጡ ይናገራል፡፡ ‹‹ሰው እያለቀሰ የማገኘው ገንዘብ ለእኔም ሰላም አይሰጠኝም፡፡ መንግሥት በካሬ ሜትር ተምኖ የሆነ ዓይነት ግልጽ አሠራር ቢቀመጥ ለተከራዩም ለእኛም ጥሩ ይሆናል፤›› በማለት ወጥ የሆነ አሠራር እንዲኖር እንደሚፈልግ፤ ደላሎችም ዕውቅና አግኝተው መስመር ውስጥ ይገባሉ የሚል እምነት እንዳለው ይናገራል፡፡
በመድኃኒዓለም የጋራ መኖሪያ ቤቶች ሳይትም ደላሎች በማከራየትም ይሁን በሽያጭ በሳይቱ መንቀሳቀስ አይችሉም፡፡ ይህ የሆነው 2006 ዓ.ም. መጨረሻ ላይ ባለቤቶች ተሰብስበው ውሳኔ ላይ በመድረሳቸው ነው፡፡ ኪራይ በደላላ ሳይሆን በምዝገባ ነው፡፡ ኪራይ ሲሆን ማኅበሩ ከአንድ ወር ኪራይ አሥር በመቶ ኮሚሽን ይወስዳል፡፡ ከሽያጭ ደግሞ አንድ በመቶ ይወስዳል፡፡ በደላላ ግን ኪራይ ሲሆን አሥር በመቶ ከሁለቱም ወገን ከሽያጭ ደግሞ ሁለት በመቶ ኮሚሽን ይከፈላል፡፡
የማኅበሩ ሥራ አስኪያጅ አቶ ታደሰ እንደሚያስታውሱት በፊት በሳይቱ ነዋሪ ሆነው የሚደልሉም ብዙ ስለነበሩ ችግሮች ነበሩ፡፡ ውል ላይ የባለቤቶችን ሳይሆን የራሳቸውን ስልክ ቁጥር በማስቀመጥ የባለቤቶች እንደራሴ ሆነው እንዳሻቸው ተከራይ የሚያውሰጡና የሚያስገቡ፣ ዋጋ የሚጨምሩ ደላሎች ነበሩ፡፡ በደላሎች ከመስመር የወጣ ዕርምጃ ወደ ክስ የተሄደባቸው አጋጣሚዎችም ነበሩ፡፡ በእነዚህና በሌሎች ሁኔታዎች ነው በግቢው ቤት የሚከራየው በደላላ ሳይሆን በምዝገባ እንዲሆን ውሳኔ ላይ የተደረሰው፡፡
ባለቤቶች በየጊዜው ዋጋ መጨመራቸውን ለማኅበሩ እንደሚያሳውቁ፤ በሌላ በኩል ተከራዮችም ዋጋ ተጨመረብን ቅሬታ እንደሚያቀርቡ የሚናገሩት አቶ ታደሰ ለባለቤቶች የግቢውን ዋጋ መሠረት በማድረግ ዋጋቸውን ምክንያታዊ እንዲያደርጉ ጥረት ሲያደርጉ ባለቤቶች ምን አገባችሁ እንደሚሏቸው ይገልጻሉ፡፡ ስለዚህ እሳቸውም እንደ ደላላው አቶ ደሳለኝ ወጥ የሆነ አሠራር ቢመጣ መልካም መሆኑንና ለማስፈጸምም ዝግጁ መሆናቸውን ይገልጻሉ፡፡
ካነጋገርናቸው ብዙዎቹ ዋጋ በካሬ ሜትር የሚተመንበት ወጥ አሠራር ቢኖር እንደሚመርጡ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡ የቤት ባለቤቶች መብትን በመጋፋት ወይም ደላሎችን ከሥራ ውጪ በማድረግ ሳይሆን አግባብ ያልሆነ አሠራርን የሚያስቀርና የዋጋ ጭማሪን ምክንያታዊ እንዲሆን የሚያደርግ ወጥ አሠራር መዘርጋትን ነው የብዙዎች ችግር ለሆነው የቤት ኪራይ ዋጋ ውድነት መፍትሔ የሚሉት፡፡

- ምሕረት አስቻለው's blog
- 2554 reads
No comments:
Post a Comment