አካዴሚው
እንደስሙ ትኩረቱ ዘመናዊ ሳይንስ ላይ ብቻ የሚያተኩር፣ ተግባራቱም በርሱ ላይ ብቻ የተገደበ መስሎ ይሰማኝ
ነበር፡፡ ዘመናዊ ትምህርት ወደ ኢትዮጵያ ከገባበት 19ኛው ክፍለ ዘመን በፊት ለዘመናት የዘለቀውና አሁንም አሻራው
ያለው ጥንታዊ ትምህርት ከቁብ የሚቆጥረው አይመስለኝም ነበር፡፡ ምክንያቱም ዘመናዊው ትምህርታችን እንደ ባህር
ማዶዎቹ በነባር ትውፊት ላይ ሳይመሠረት ምዕራብ ዘመት ሆኖ መዳከሩን አይቻለሁና፡፡ ከዚህ አንጋዳ ለመውጣትና ነባሩን
ከዘመኑ ጋር ለማስማማት ይረዳ ዘንድ አካዴሚው ‹‹የኢትዮጵያ ባህላዊ ትምህርት ምንነት፣ ባህርያትና ለዘመናዊ
ትምህርት ያለው አስተዋጽኦ›› በሚል መነሻ ኅዳር 15 ቀን 2007 ዓ.ም. በተዘጋጀው ጉባዔ የአንድ ቀን ውሎዬ
ማለፊያ ነገሮች ብቀስምም፣ ከዚህ በበለጠ በስፋትና በምልዓት ባህላዊውንና ዘመናዊውን ትምህርት ያጣመሩ ብቻ ሳይሆን፣
የጥንታዊው ትምህርት ሊቃውንት ተጋብዘውበት ቢሆን ኖሮ የተሻለ ግንዛቤ ማግኘት ይቻል ነበር፡፡
አካዴሚው እኔን ጨምሮ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ መምህራንና የሁለተኛና ሦስተኛ ዲግሪ ተማሪዎችን እንዲሁም ከሌሎች ቦታዎች ውስኖችን ብቻ (ከጥቂቶቹ በቀር አብዛኞቻችን ለአጃቢነት) መጋበዙ፣ ጥናት አቅራቢዎቹም በራሱ ግቢ ውስጥ ባሉት ምሁራን ላይ በማሳረፉ (በእርግጥ ጥቂቱ በነባሩ ትምህርት ያለፉና ያጠኑ ቢሆንም) በመሪ ቃሉ ላይ የተጠቀሱትን ሐረጎች አሳክቷል የሚል ግምት አልፈጠረብኝም፡፡ እንደስሙ የኢትዮጵያ አካዴሚ ከሆነ በአገሪቱ ካሉት ዩኒቨርሲቲዎች በተለይ ከጥንታዊው ትምህርት ጋር ትስስር ካላቸው፣ እንደ ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ዓይነቶች፤ እንዲሁም ከጥንታዊው ትምህርት ጋር ቁርኝት ያላቸው የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ሊቃውንት ከአክሱም፣ ከመቐለ፣ ከጎንደር፣ ከጎጃም፣ ከሸዋ ወዘተ. አካባቢ፣ በእስላማዊ ትምህርትም እንዲሁ መጋበዙን ለምን ተወው? ለጥናት አቅራቢነት ባይሠለፉ እንኳ የሚቀርቡትን አዳምጠው ቢተቹ ጉባዔው የበለጠ ስኬታማ ይሆን ነበር፡፡ በመሰለኝና በደሳለኝ ‹‹አጥናና አቅርብ ስለተባልሁ እንጂ ባለሙያ አይደለሁም›› እየተባለ የቀረበበትን ዕይታዊ መድረክ እንደ ቅኔ ቤት ልማዳቸው ‹‹የለም እንዲህ ነው›› ብለው ያርቁት ነበር፡፡
በጉባዔው ላይ የተገኙ አንድ አስተያየት ሰጪ አካዴሚው ለባህላዊው ትምህርት ትኩረት ሰጥቶ ጉባዔ ማዘጋጀቱን ሲያወድሱ ‹‹ዓይን እቅርቡ ያለውን ቅንድብ አየ›› ማለታቸውን ሰምቻለሁ፡፡ እርግጥ ምሳሌው እስካሁን ነባሩ ትምህርት ካጠገቡ ተቀምጦለት ላላየው ባለ አምስት ዓመቱ አካዴሚው ማየቱን ተከትሎ መመሰሉ ተገቢነት ይኖረዋል፡፡ ግን ዓይን (አካዴሚው) እቅርቡ ያለውን ቅንድብ (ነባር ትምህርት) ለማየት የሚችለው በስማ በለው ሳይሆን ባለዕውቀቶችን አራት ዓይናዎችን ከቤተክህነት ጉባዔዎች [ዩኒቨርሲቲዎች] እና አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲን ጨምሮ ከሌሎች ዩኒቨርሲቲዎችና መንፈሳዊ ኮሌጆች ማሰባሰብ ሲችል ነው፡፡ በመድረኩ ከተገኙት ቢበልጡ እንጂ የማያንሱ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የኢትዮጵያ ንቋዎችና ባህሎች አካዴሚ፣ የኢትዮጵያ ጥናት እንዲሁም ቋንቋዎች ጥናቶች ተቋሞች መገኘት የሚገባቸው ልሂቃንን አልተመለከትኩም፡፡
ከቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለሥልጣን በጉባዔው እንዲገኙ መጋበዝ የሚኖርባቸው የቅሬተ አካል ተመራማሪዎች ናቸው? ወይስ ለጉዳዩ ቀረቤታ ያላቸው የጥንታዊው የግእዝ ሥነ ጽሑፍና ባህላዊ ትምህርት ከፍተኛ ተመራማሪዎች? ለምን እንዲህ ሆነ? አካዴሚው ውስጥ ጅረት ይኖር ይሆን? ከስድስቱ ጥናት አቅራቢዎች አንዱ በነባሩ ትምህርት በተለይም በቅኔ ቤት ያለፉ፣ ያስመሰከሩ፣ መጻሕፍትን ያመሠጠሩ፣ በዘመናዊው ትምህርት እስከ ዶክትሬት የደረሱ ናቸው፡፡ በጉባዔው የተገኙ አንድ የዩኒቨርሲቲው ማኅበረሰብ አባል ላቀረቡት ጥናት የተንደረደሩበት መንገድ አቅራቢውንም፣ ተሳታፊውንም አሳዝኗል፡፡ ‹‹ቅኔውን የሚያውቁ ይመስላል›› ማለታቸውን ተከትሎ አቅራቢው ‹‹መቼም እንደ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በየትም ቦታ አልተዋረድኩም›› ብለው ዩኒቨርሲቲው ውስጥ የሚታየውን ዝንባሌ እግረ መንገዳቸውን ጎነጥ አድርገው አልፈውታል፡፡ መድረክ መሪውም ተናጋሪውን ኮንነውታል፡፡ ይልቅስ ተናጋሪው ከባለቅኔው ይልቅ ‹‹አጥናና አቅርብ ስለተባልሁ እንጂ ባለሙያ አይደለሁም›› ስላሉት አጥኚ አንድም ያልተነፈሱት ለምን ይሆን? በተከበረ የጥናት ጉባዔ ላይ በሙጫ ፀያፍ ነገርን ማጣበቅ የሚጠበቅ ነገር አይደለም፡፡ በቅኔ ቤት ‹‹ችፍርግ ለዝግባ ልጅህን ለልጄ›› (አቃኒት ለአከት ሀበ ዕፀ ቄድሮስ) የተባለውን ብሂል አስታውሶኛል፡፡ በመሰለኝና በደሳለኝ፣ ምላስና ምራቅ ይዞ ይዞ ሊቁን ማቃለል አይገባም፡፡ ወዴት እየሄድን እንደሆነ ያሳስባል፡፡
ባለፈው ረቡዕ ሪፖርተር ጋዜጣ እንደዘገበው፣ ከቀረቡት ወረቀቶች አራቱ ከጥናታቸው ጋር ግንኙነት ያላቸውና በውስጡም ያለፉ መሆናቸው የተነገረ ሲሆን፣ በሥነ ከዋክብት ጥናት፣ በአየር ትንበያና በዘመን አቆጣጠር ላይ ወረቀት ያቀረቡት እንደተናገሩት፣ ሁለቱ አቅራቢዎች የማቲማቲክስ ባለሙያ መሆናቸው [የባህላዊ] ትምህርቱ ባለሙያ አለመሆናቸውን ተናግረዋል፡፡ ‹‹የዚህ ባለሙያ አይደለሁም፤ አጥናና አቅርብ ስለተባልሁ ነው፤ አንዳንድ ነገሮችን አላውቅም ማለት አይደለም፤›› ማለታቸውን ያስተዋሉት አንድ የጉባዔው ተሳታፊ፣ አካዴሚው የባህላዊውን ትምህርት ዘርፍ ብዙ ባህርያትና አስተዋጽኦ በጥልቀት የሚፈትሹ ትንተናዎች በጉባዔው ይቀርባሉ ካለው ጋር እንዴት ሊታረቅ ይችላል? ማለታቸውን እኔም እጋራዋለሁ፡፡
አካዴሚው እንዲህ ዓይነት ነፀብራቆች እንዳይኖሩ መትጋት ይገባዋል፡፡ አልያ አካዳሚ ሆኖ እንዳይቀር፡፡ የአካዴሚውን አወቃቀር በቅጡ ባላውቀውም የአገሪቱን ነባር ትምህርት ከዘመናዊው ጋር አስተባብሮ የሚያውቅ ሊቅ ወንበሩን ሊያስተባብር ይገባል የሚል እምነት አለኝ፡፡ ለነባሩ ትምህርት እንግዳ ለትውፊቱ ባዳ የሆኑትን ዘርፉን እንዲመሩ ማድረግ ይበጃል የሚል እምነት የለኝም፡፡ ይኸን ያሰኘኝ በመድረኩ ላይ አንዱ ባለሙያ ከነባሩ ትምህርት ጠቅሶ የሙያ ቃላቱን (ተርሞችን) እያጣቀሰ አስተያየት ሲሰጥ ‹‹ይኼኮ የተባለ ነው›› እያሉ የአካዴሚው ዋና ሥራ አስፈጻሚ በንግግሩ ላይ ጣልቃ የገቡበት አካሄድ፣ ዓውዱን አለመረዳታቸውና ከነባሩ ትምህርት ጋር ያላቸው ትስስር የት ላይ እንደሆነ አሳብቆባቸዋል፡፡ ዋናው ሥራ አስፈጻሚው በማጠቃለያ ንግግራቸው ላይ እንዳዳመጥኳቸው፣ ጉባዔውን ለማካሄድ ከተኬደበት ሒደት ውስጥ ያሳሰባቸው ለ100 ያህል ታዳሚ ለሻይ ሰዓትና ለምሳ አቅርቦት የተኮናተሩት ማዕድ የታሰበውን ያህል ተጋባዥ ካልመጣ ኪሳራ ላይ እንዳይወደቅ ነበር፡፡ እንደኔ ግን ሥጋት ሊሆንባቸው የሚገባው የተጠሩት ጉባዔተኞች ምን ያህሉ ከነባሩ ትምህርት ጋር ይተዋወቁ ይሆን? ጥናት እንዲያቀርቡ መጋበዝ ሲገባቸው ያልተጋበዙ ይኖሩ ይሆን? በጉባዔውም እንዲሳተፉ መጠራት ሲገባቸው ያልተጠሩ ይኖሩ ይሆን? የሚል ቢሆን ይመረጥ ነበር፡፡
(ጉዱ ካሳ፣ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ስድስት ኪሎ)

No comments:
Post a Comment