የግእዝ እና የሌሎች ብራናዎችን ከአይኤስ የታደጉ ካህን
‹‹አይኤስአይኤስ›› (ISIS) በሚል ምሕፃረ ቃል የሚታወቀው የኢራቅና የሶሪያ እስላማዊ መንግሥት አራማጅ ሸማቂ ቡድን፣ ከሁለቱ አገሮች አልፎ የዓለም ሥጋት መሆን ከጀመረ ከራርሟል፡፡
‹‹አይኤስአይኤስ›› (ISIS) በሚል ምሕፃረ ቃል የሚታወቀው የኢራቅና የሶሪያ እስላማዊ መንግሥት አራማጅ ሸማቂ ቡድን፣ ከሁለቱ አገሮች አልፎ የዓለም ሥጋት መሆን ከጀመረ ከራርሟል፡፡
ንፁሓኑን ከመቅላት ከመፍጀት አልፎ ዘመንን ባሸመገሉ
ጥንታዊ ውርሶች፣ በዩኔስኮ በተመዘገቡ የዓለም ብርቅዬ ቅርሶችን ሲያወድም እየታየም ነው፡፡ ዩኔስኮ ‹‹ኧረ መላ
በሉ›› ቢልም የሰማው የለም፡፡
ሺሕ ዓመታትን ያስቆጠሩ ሐውልቶችን በሙዚየም ውስጥ የሚገኙ የዕደ ጥበብ ውጤቶች
መውደም የተመለከቱ በኢራቅ ሞሱል ከተማ ይኖሩ የነበሩ አንድ ካህን ቅርስን ማውደም እንደሰደድ እሳት የያዘው አይኤስ
በሞሱል ከተማ ታላቅ ገዳም ውስጥ የሚገኙ ብራናዎችን ከማጥፋት እንደማይለመስ በመገንዘብ የፈጠሩት መላ
ተሳክቶላቸዋል፡፡
ኤፒ እንደዘገበው፣ ኢራቃዊው የዶሚኒካን መነኩሴ አባ ነጂብ ሚካኤል ለ25 ዓመታት የኖሩባት ሞሱል
በአይኤስ እጅ ከመውደቋ በፊት በሚኖሩበት ገዳም ሙዚየም ውስጥ ተሰባስበው ያሉ ታሪካዊ፤ ሃይማኖታዊና ፍልስፍናዊ
ጽሑፎችን የያዙ በግእዝ፣ በአራማይስጥ፣ በሱርሰጥ፣ በዓረቢኛና በአርመንኛ የተጻፉ ብራናዎችን መክረሚያውን በኩርዶች
በኩል ድንበር አቋርጠው እንዲወጡ አድርገዋል፡፡ በስድስት ሳጥኖች የታጨቁት ብራናዎች ከ13ኛው እስከ 19ኛው ምእተ
ዓመት ዕድሜ ያስቆጠሩ ናቸው፡፡
(ሔኖክ መደብር)
በሪፖርተር ጋዜጣ የእሑድ ግንቦት 30 ቀን 2007 ዓ.ም. እትም የወጣ
No comments:
Post a Comment