Friday, May 22, 2015

ከ45 ዓመት በፊት የፓርላማ ምርጫን ያሸነፉት አራት ሴቶች



45 ዓመት በፊት የፓርላማ  ምርጫን ያሸነፉት አራት ሴቶች

ሰማንያ አራት ዓመት ባስቆጠረው የኢትዮጵያ ፓርላማ የመጀመርያው ሕዝብ በቀጥታ የተሳተፈበትና እንደራሴዎቹን የመረጠበት ምርጫ የተካሄደው 1948 .. ነበር፡፡ በቀዳሚው ምርጫ ካሸነፉት ተወዳዳሪዎች መካከል አንዷ / ስንዱ ገብሩ ናቸው፡፡ በታሪክ እንደተመዘገበው / ስንዱ የመጀመሪያዋ የሴት የሕግ መምሪያ ምክር ቤት አባልና የሕግ መወሰኛ ምክር ቤት ምክትል ፕሬዚዳንት ሆነው ለአራት ዓመት አገልግለዋል፡፡ ከወ/ ስንዱ በኋላ ጥቂት የማይባሉ ሴቶች እስከ 1965 .. ድረስ በተካሄዱት አምስት ምርጫዎች ተፎካክረዋል፡፡ 1961 .. በተካሄደው አራተኛው የሕዝበ እንደራሴዎች ጠቅላላ ምርጫ ከመላው ኢትዮጵያ ከተመረጡት 250 እንደራሴዎች መካከል አሸናፊ የነበሩት አራት ሴቶች ናቸው፡፡ ከተወዳደሩት ዕጩዎች መካከል 24 ሴቶች ነበሩ፡፡ 45 ዓመት በፊት አሸናፊ የነበሩት እንስቶች / የሺመቤት ወንድማገኘሁ (ደብረ ብርሃን) / ምንትዋብ ካሣ (ጎንደር) / ራቢያ አብድርቃድር (ሊሙ) እና / ምፅላል ገብረ ሕይወት (ተምቤን) ናቸው፡፡
(ሔኖክ መደብር )

No comments:

Post a Comment