ዛሬ መጋቢት 6 ቀን 2007 ዓ.ም. 4ኛ እሑድ ከፋሲካ በፊት እና የዓቢይ ጾም 4ኛ እሑድ፡ እኩለ ጾም፡ እሑድ ዘደብረ ዘይት፡፡
የዛሬው እሑድ ደብረ ዘይት ይባላል፡፡ ደብረ ዘይት በምሥራቅ
ኢየሩሳሌም የሚገኝ ኮረብታማ ስፍራ ሲሆን፣ ስሙን ያገኘው ከስፍራው በብዛት ከሚበቅለው የወይራ ዛፍ ነው፡፡ መጻሕፍት እንደሚነግሩን፣
ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የጸለየበት፣ እመቤታችን
ቅድስት ማርያም የተቀበረችበት ጌቴሰማኒ የተባለውም የአትክልት ቦታ በዚህ ሥር ነው የሚገኘው፡፡ የደብረ ዘይት እሑድ
የሚያስታውሰን እግዚእ (ጌታ) በቦታው ስለዳግም ምጽአቱ ለጴጥሮስ፣ ለያዕቆብና
ለዮሐንስ ያስተማረውን ነው፡፡ [ጳጉሜን ውስጥ እሑድ ሲውልም በተመሳሳይ የሰንበቱ ቀለም ዳግም ምጽአት ነው]
የእኩለ ጾም እሑድን ‹‹ደብረ ዘይት›› ብሎ የሰየመው
የ6ኛ ክፍለ ዘመኑ ቅዱስ ያሬድ ሲሆን የመዝሙሩ ርእስም ‹‹እንዘ ይነብር እግዚእነ ውስተ
ደብረ ዘይት›› (ጌታችን በደብረ ዘይት ተቀምጦ ሳለ) ነው፡፡
መዝሙር- መዝሙረ
ያሬድ- 29ኛ
‹‹እንዘ ይነብር
እግዚእነ›› (ጌታችን ተቀምጦ
ሳለ)
ምስባክ- መዝሙረ
ዳዊት (49፡ 3 ሀለሐ)
‹‹እግዚአብሔርሰ ገሀደ ይመጽእ፣ ወአምላክነሂ
ኢያረምም፣ እሳት ይነድድ ቅድሜሁ››
(እግዚአብሔር በግልጥ ይመጣል፡፡
አምላካችንም ዝም አይልም፤ እሳት በፊቱ ይነዳል፡፡)
ምንባባት፡ (1ኛ
ተሰሎንቄ 4፡13-18፤ 2ኛ ጴጥሮስ 3፡8-18፤ ሐዋርያት ሥራ 24፡9-21፤ ማቴዎስ 24፡1-35)
Today
March 15, 2015: 4th Sunday
before Easter and 4th Sunday of the Great Fast: mid-Lent: Sunday of
the Mount of Olives. This Sunday reminds us of the eschatological discourse of
our Lord as he was conversing with Peter, James and John on the Mount of
Olives.
The
Lord- our hope! (1 Thes) - will come back and judge (Mt, Ps, 1 Thes, 2 Pt) the
living and the risen dead (1 Thes, Ac), uniting to himself for ever those who
are eager to welcome him (1 Thes) and bringing to completion the purpose of all
creation (2 Pet). He delays his coming for the sake of sinners (2 Pet) but let
us get ready!
(Source:
The Liturgical Year of the Ethiopian Church The Temporal: Seasons and Sundays- by
Aba Emmanuel Fritsch, CSSp)
የዕለቱ ልዩ ምግብ- ‹‹በቆልት››
ከትውፊት
እንዳገኘነው፣ ዛሬ ከቁርስ በፊት የሚቀመሰው በቆልት ነው፡፡ ሰሞኑን
በውሃ ውስጥ ተዘፍዝፎ የቆየው ባቄላ መብቀሉ ከተረጋገጠ በኋላ በአዋዜና በሰናፍጭ ተቀላቅሎ ለማዕድ የሚቀርብበት ነው፡፡ ተምሳሌታዊ
ፍችው የባቄላው መብቀል ዳግም ምጽአትን የሚያሳስብ ነው፡፡ በዕለተ ምጽአት ጌታችን በመለኮታዊ
ግርማ በሰው መጠን ሲመጣ ሙታን የሚነሡበትና የሚለዩበትን ያመለክታል፡፡ የበቀለው ባቄላ ‹‹ያባቴ ቡሩካን›› የተባሉትን በቀኝ በኩል የሚሆኑትን ሲወክል፣
የማይበቅለውና በሱም ምክንያት ከአፋችን አውጥተን የምንወረውረው ባቄላ በግራ በኩል የሚሆኑትን ይወክላል፡፡ ‹‹በጎቹን በቀኝ ፍየሎቹን
በግራ. . .›› እንዲል፡፡
ምንጭ፡- መጽሐፍ ቅዱስ የዕሥራ ምእቱ፣
መጽሐፈ ግጻዌ ሐዲስ ዘአለቃ ያሬድ ፈንታ፣ ሥርዓተ አምልኮ ዘኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ዘመምህር ልዑለቃል አካሉ፡፡
(ሔኖክ መደብር )
No comments:
Post a Comment