Saturday, February 28, 2015

ዓድዋ ሲታሰብ -01 March 2015 ተጻፈ በ ሔኖክ ያሬድ


. . . አሁንም አገር የሚያጠፋ ሃይማኖት የሚለውጥ ጠላት እግዚአብሔር የወሰነልንን ባሕር አልፎ መጥቷል . . . . በእግዚአብሔር ረዳትነት አገሬን አሳልፌ አልሰጠውም፡፡ . . . ያገሬ ሰው . . . ጉልበት ያለህ በጉልበትህ እርዳኝ፡፡

ጉልበት የሌለህ ለልጅህ፣ ለምሽትህ፣ ለሃይማኖትህ ስትል በኀዘን እርዳኝ፡፡ . . . ይህ ኃይለ ቃል ዳግማዊ ዐፄ ምኒልክ ሕዝቡንና የየአካባቢውን መኳንንትና ገዢዎች በኢጣሊያ ላይ ያነሳሱበት የክተት አዋጅ ነበር፡፡ በዚህም አዋጅ መሠረትም ከ119 ዓመታት በፊት፣ የካቲት 23 ቀን 1888 ዓ.ም. ዓድዋ ላይ የኢጣሊያ ወራሪ ሠራዊት ድል ተመቶበታል፡፡ ኢትዮጵያውያን እርመኛ አርበኞች በጠቅላይ አዝማቹ በንጉሠ ነገሥት ዳግማዊ ምኒልክ አማካይነት ሕያው ታሪክ ያስመዘገቡበት ዓድዋ፡፡ 

Saturday, February 21, 2015

7ኛ እሑድ ከትንሣኤ (ፋሲካ) በፊት እና የዐቢይ ጾም 1ኛ እሑድ- ቅድስት እሑድ



 
·        (ማኅሌት) ጎሕ ቀዶ ንጋት ሆኗልና ይህችን ክብራችን የሆነች እናታችን ቅድስት ቤተ ክርስቲያንን ሰላም እንበላት፡፡

7ኛ እሑድ ከትንሣኤ (ፋሲካ) በፊት እና የዐቢይ ጾም 1ኛ እሑድ፡ ሰንበት ዘቅድስት [ዕለት]
ያለፈው ሳምንት ከዘወረደ ሰኞ ዠምሮ የነበሩት ዕለታት የዝግጅት ጾም ነበሩ፤  ነገ (የካቲት 16) ወደ ምንጀምረው ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ጾመው የ40 ቀን ጾም ያሸጋግሩን ናቸው፡፡
የዛሬዋ እሑድ ቅድስት  ትባላለች፡፡ በጾመ ድጓ ውስጥ ስያሜውን የሰጣት ቅዱስ ያሬድ ነው፡፡ በዋዜማ፡ ዛቲ ዕለት ቅድስት ይእቲ  እንዲል፡፡ ከቅድስት ሰኞ (የካቲት 16) ጀምሮ እስከ መጋቢት 25 ኒቆዲሞስ ዓርብ ድረስ ጾመ ዐርብዓ (የ40 ቀን ጾም) ጾመ ኢየሱስ ይባላል፡፡ ቅድስት መባሏ ጌታችን በጾመው 40 ቀን ስለቀደሳት፤ ነው ሰንበትንም ከዕለታት ሁሉ ለይቶ ስላከበራት ነው፡፡ በዕለቷም ለሰው ልጆች ድኅነት  ተገኝቶባታል፡፡
   የየካቲት 15 ዕለተ ሰንበት የመዝሙር ርእስ፡  26ኛ መዝሙር - እግዚአብሔርን አመስግኑ፤ ስሙንም ጥሩ  (ግነዩ ለእግዚአብሔር ወጸውኡ ስሙ)
ለዕለቱ የሚነበቡ ቅዱሳት መጻሕፍት
ከብሉይ- መዝሙር 104፡ 1-10፣ ከጳውሎስ- 1ኛ ተሰሎንቄ 4፡1-12፣ ከኩላዊ (ዩኒቨርሳል) መልእክታት- 1ኛ ጴጥሮስ 1፡ 13-25፣ ሐዋርያት ሥራ 10፡ 17-23፣ ወንጌል- ማቴዎስ  6፡ 16-24፣
ምስባክ- ከዳዊት መዝሙር 95፡5-6
እግዚአብሔርሰ ሰማያት ገብረ- እግዚአብሔር ግን ሰማያትን ሠራ፤
አሚን ወሠናያት ቅድሜሁ-  ምስጋና ውበት በፊቱ ነው፤
ቅድሳት ወዕበየ ስብሐት ውስተ መቅደሱ- ቅዱስነትና ግርማ በመቅደሱ ውስጥ ናቸው፡፡
አንድምታ ትርጓሜ
እግዚአብሔርሳ ምን አደረገ ትለኝ እንደሆነ እግዚአብሔርስ አምላክ ነውና ሰባቱን ሰማያት ፈጠረ፡፡ ሃይማኖት ምግባር በፊቱ ነው ማለት ሃይማኖት ምግባርን የያዘ ሰው ይወዳል፡፡ አሚን ወሠናይት ያለውን ደገመው፤ አንድም (ቅድሳት) ቅዱስ ቅዱስ ተብሎ መመስገን፤ (ዕበየ ስብሐት)  ዓቢየ ስብሐት መባል ገንዘቡ ነው፡፡
·        (ሰላም)
በዚህች እግዚአብሔር በሠራት ዕለት እንደሰት፤ ሐሤትም እናድርግ፡፡ እርሱ ሕያው ነውና ሰንበቱን በሰላም እናክብር ትእዛዙንም ደግሞ አንጣስ፡፡
ምንጭ፡
-      መጽሐፍ ቅዱስ (1953 ቀኃሥ እትም)
-      መዝሙረ ዳዊት ንባቡና ትርጓሜው (1950፣ ወዘአኅተሞ አባ ቴዎፍሎስ ጳጳስ ዘሐረር ወዘኵሉ አድያሚሃ)
-      መጽሐፈ ግጻዌ ሐዲሰ ዘተሰናአወ በአርባዕቱ ክፍላተ አዝማን (1997፣ ዘአለቃ ያሬድ ፈንታ ወልደ ዮሐንስ)
-      ጸሎተ ሰዓታት በኢትዮጵያ ሥርዓተ ጸሎት መሠረት የተዘጋጀ (1990፣ ትርጉም እና አርትኦት  በአለቃ ያሬድ ፈንታ ወልደ ዮሐንስ)
በመናገሻ ከተማችን ተጻፈ፤  እሑድ፣ የካቲት 15 ቀን 7507 ዓመተ ዓለም፣ 2007 ዓመተ ሥጋዌ፣ 2015 ዓመተ ምሕረት (በፀሐይና በጨረቃ)፣ 1731 ዓመተ ሰማዕታት፣ 3 ዓመተ ወንጌላዊ ዘሉቃስ፣ ሌሊቱ 29፣ ጨረቃ 3 በሚያድርበት/ የጨረቃ መጋቢት 3ኛ ፣ በአይሁድ (ቤተ እስራኤላውያን) የአዳር ወር 3ኛ ቀን 5775 ዓመተ ዓለም፣ በኢስላም ጁማዳ አወል ወር 3ኛ ቀን (ጀማዲ ቀዳማይ እንዲል ባሕረ ሐሳባችን) 1436 ዓመተ ሒጅራ፡፡
ክብረት ይስጥልኝ!!!

-      ሔኖክ መደብር


Saturday, February 14, 2015

የካቲት 8 ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ቤተ መቅደስ የገባበት በዓል


በየካቲት 8 ቀን የምናከብረው በዓል ኤታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የሙሴን ሕግ ይፈጽም ዘንድ ከከበረ ልደቱ ከአርባ ቀኖች በኋላ ወደ ቤተ መቅደስ የገባበትን ዕለት ነው፡፡

Sunday, February 1, 2015

ጾመ ነነዌ (ጥር 25-27 ቀን 2007/ 2015 ዓመተ ምሕረት)



በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ሥርዓተ አምልኮ  (ሊጡርጊያ) መሠረት ዛሬ ጥር 25 ቀን 2007 ዓመተ ሥጋዌ በፀሐይ አቈጣጠር፣ 2015 ዓመተ ምሕረት በፀሐይና በጨረቃ ጥምር መሠረት ‹‹ጾመ ነነዌ›› ተብላ የምትታወቀው የሦስት ቀኖች  ጾም ተጀምራለች፡፡ የነነዌ ጾም ሦስት ቀን ብቻ ነው፡፡ እነርሱም ሰኞ፣ማክሰኞና ረቡዕ ናቸው፡፡ ጾሙ የሚፈታበት ቀን ኀሙስ ነው፡፡