18 January 2015
ተጻፈ በ
ሔኖክ ያሬድ
የግብፅ ፕሬዚዳንት አብዱልፈታህ አልሲሲ አገሪቱን
ሰሞኑን ለጎበኙት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ፣
ዓባይ (ናይል) ለግብፅ “የደም ሥር” እንጂ የልማት ምንጭ አይደለም አሉ።
ፕሬዚዳንት አልሲሲ ፓትርያርክ አቡነ ማትያስን ባለፈው
ሰኞ በካይሮ ፕሬዚዳንታዊ ቤተ መንግሥት አብረዋቸው ከተጓዙት ልዑካናቸውና በግብፅ የኢትዮጵያ አምባሳደር መሐመድ
ድሪር ጋር ተቀብለው ባነጋገሩበት ጊዜ፣ ግብፅ የኢትዮጵያ ሕዝብን ልማት ለማደናቀፍ እንደማትቆም ተናግረዋል፡፡ ይህም
የዓባይ ወንዝ ለኢትዮጵያውያን የልማት ምንጭ ቢሆንም፣ ለግብፅ ግን ልማት ብቻ ሳይሆን የደም ሥር መሆኑን
መናገራቸውን አህራም ኦን ላይን ዘግቧል።
በሁለቱ አገሮች መካከል ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ውጥረት የሰፈነው ኢትዮጵያ በዓባይ ወንዝ ላይ እየገነባችው ያለው የታላቁ ኢትዮጵያ ህዳሴ ኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ግድብ ፕሮጀክት ተፅዕኖ ያሳድራል የሚል ድምፅ ከካይሮ በመሰማቱ ነው።
ኢትዮጵያ በተደጋጋሚ ጊዜ የኃይል ማመንጫ ግድብ ግንባታው በግብፅ ጥቅም ላይ አንዳች የሚያሳድረው አሉታዊ ተፅዕኖ እንደሌለ መናገሯ ይታወሳል። ሁለቱ አገሮች ከሱዳን ጋር በመሆን በጋራ የቴክኒክ ኮሚቴያቸው አማካይነት የግድቡ ግንባታ ሒደትና የሚኖረውን ገጽታ የሚያጠና ዓለም አቀፍ አማካሪ ድርጅት በመምረጥ ሒደት ላይ መሆናቸው ይታወቃል።
ፕሬዚዳንት አልሲሲ ከፓትርያርክ አቡነ ማትያስ ጋር በተወያዩበት ወቅት አጽንኦት ሰጥተው የተናገሩት፣ በዓባይ ላይ የሁለቱ አገሮች መብቶችና ጥቅሞች በተመለከተ ፖለቲካዊ ስምምነት በሕጋዊ ማዕቀፍ ውስጥ መኖር እንዳለበት ነው።
አቡነ ማትያስ በበኩላቸው፣ በጠንካራ ትስስር ላይ የተመሠረተው የሁለቱ አገሮች ግንኙነት ከዓባይ የሚመነጭ ውኃ የማያቋርጥ የጋራ ሀብት በመሆኑ በፍትሐዊነትና በእኩልነት ተጠቃሚ የሚኮንበት ነው ብለዋል። የኢትዮጵያ ፐብሊክ ዲፕሎማሲ ልዑካን ባለፈው ታኅሳስ በካይሮ ባደረጉት ጉብኝት በተገኘው ውጤት መርካታቸውን የገለጹት ፓትርያርኩ፣ አልሲሲ ኢትዮጵያን ለመጎብኘት የያዙትን ዕቅድ የኢትዮጵያ ሕዝብ እየጠበቀ መሆኑን መግለጻቸውን አህራም ዘግቧል።
በውይይቱ ላይ የተገኙት የኮፕቲክ ፓትርያርክ አቡነ ቴዎድሮስ ዳግማዊ ቤተ ክርስቲያናቸው በግብፅ ሕዝብ ስም በኢትዮጵያ ውስጥ በሚኖሯት የልማት ፕሮጀክቶች፣ ለኢትዮጵያ ልማት አስተዋጽኦ እንደሚያደርጉና በሁለቱ አገሮች መካከል ጠንካራ ግንኙነት እንደሚፈጥር ተናግረዋል።
ከጥር 2 ቀን 2007 ዓ.ም. ጀምሮ ለስድስት ቀናት ግብፅን ለመጀመርያ ጊዜ የጎበኙት ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ፣ የአገሪቱን ከፍተኛ የሃይማኖትና የፖለቲካ መሪዎች ጠቅላይ ሚኒስትር ኢብራሂም ማህላብን ጨምሮ ማነጋገራቸው ታውቋል።
በካይሮ አባሲያ በሚገኘውና ከ47 ዓመታት በፊት በኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት በነበሩት ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴና በፕሬዚዳንት ጋማል አብዱል ናስር በተመረቀው የቅዱስ ማርቆስ ካቴድራል በተደረገላቸው አቀባበል ላይ ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ኤክስፐርቶችና ጥናቶች እንዳረጋገጡት፣ ለሁሉም በርካታ ጠቀሜታ ያለውና ግብፅና ሱዳን ላይ አንዳች ጉዳት አያደርስም ያሉት አቡነ ማትያስ፣ “ሁላችንም ከአንድ ዓባይ ውኃ እንጠጣለን፡፡ ይህም በመጣጣምና በመተሳሰር ለመኖር አስችሎናል፡፡ ጥንታዊው ዝምድናችንም ለዘለዓለሙ እንደሚፀና እምነቴ ነው፤” ብለዋል። የእስክንድርያ ፓትርያርክ ቴዎድሮስ በበኩላቸው፣ ሁለቱ አብያተ ክርስቲያናት በዓባይ ወንዝ አማካይነት መልክዓ ምድራዊ ትስስር መፍጠራቸውን ተናግረዋል።
በሌላ በኩልም ሁለቱ ፓትርያርኮች በጋራ ባወጡት መግለጫም በምሥራቅና በኦሬንታል (መካከለኛ ምሥራቅ) ኦርቶዶክስ አብያተ ክርስቲያናት መካከል የላቀ ትብብርና አንድነት እንዲፈጠር ጥሪ ማድረጋቸውን ኦርቶዶክሲ ኮግኔት ፔጅ (ኦሲፒ) በድረ ገጹ ዘግቧል። ለኦርቶዶክሳዊ አንድነቱ ምክረ ሐሳብ ያቀረቡት አቡነ ማትያስ የምሥራቅና የኦሬንታል ጉባዔ በእስክንድርያ በቅርቡ እንዲካሄድ ጥሪ ያቀረቡ ሲሆን፣ በሁለቱም ወገኖች መካከል በሃይማኖት፣ በምጣኔ ሀብትና በማኅበራዊ ልማት ትብብር ለማድረግ ይበጃል ብለዋል። ሁለቱም ፓትርያርኮች መደላድሉን ለመፍጠር መስማማታቸውም ታውቋል።
የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን የምትገኝበት የኦሬንታል አብያተ ክርስቲያናት ፓትርያርኮች ጉባዔ ከ1,500 ዓመት በኋላ ለመጀመርያ ጊዜ በ1957 ዓ.ም. በአዲስ አበባ ከተማ በአፍሪካ አዳራሽ በቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ አማካይነት መካሄዱ ይታወሳል።
የኢትዮጵያና የኮፕት (ግብፅ) አብያተ ክርስቲያናት ግንኙነት በአራተኛው ክፍለ ዘመን የተጀመረው በዘመኑ ፓትርያርክ የነበሩት አቡነ አትናቴዎስ የአክሱሙን አቡነ ሰላማ ከሣቴ ብርሃንን (ፍሬምናጦስ) ጳጳስ አድርገው ከሾሙ በኋላ ነው።
በሁለቱ አብያተ ክርስቲያናት መካከል ለዘመናት የዘለቀው ግንኙነት በ1967 ዓ.ም. የኢትዮጵያ መንግሥት ሥልጣንን በጨበጠው የደርግ መንግሥት መሰናክል የተፈጠረበት ቢሆንም፣ ከለውጡ በኋላ ከ1984 ዓ.ም. ጀምሮ አምስተኛው ፓትርያርክ በነበሩት በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ዘመን ተጠናክሮ መቀጠሉ ይታወሳል፡፡
http://www.ethiopianreporter.com/index.php/news/item/

No comments:
Post a Comment