Sunday, January 4, 2015

በጋ ዛሬ ገባክቡራትና ክቡራን በዛሬዋ ቅድስት (ልዩ) ዕለት፥ እሑድ፥ በፀሐይ ታኅሣሥ 26 ቀን 2007 ዓ.ም. (7507 ዓመተ ዓለም) በጨረቃ ጥር 13 ቀን 2015 (በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን አቆጣጠር)፣ ረቢ ዐወል (በግእዝ ረቢ ቀዳማይ) 13 ቀን 1436 ዓመተ ሒጅራ (በኢትዮጵያ እስልምና አቆጣጠር)፣ ተቬት 13 ቀን 5775 ዓመተ ፍጥረት (በቤተ እስራኤል አቆጣጠር)፣ የበጋ ወቅትን (ሐጋይ) ተቀብለናል።
 ትናንትና ታኅሣሥ  25 ቀን የአበባና የነፋስ ወቅት የሆነው መፀውን ሸኝተናል። ሐጋይ- በጋ የፀሐይ፣ የድርቅ (ደረቅ) ወቅት ነው፡፡ ፀሐይ የምትበረታበት ወቅቱ እስከ መጋቢት 25 ይዘልቃል። በጋ በመፀው ያሸተውና ያፈራው መከሩ የሚታጨድበት የሚሰበሰብበት ወዘተ. ነው። “አንተ የምድርን ዳርቻ ሁሉ ሠራህ። በጋንም ክረምትንም አንተ አደረግህ” እንዲል መዝሙረኛው። እንኳን አሸጋገራችሁ፣ ሠናይ በጋ ይሁንልን። መጋቢት 26 ለሚብተው የፀደይ (ከፊል በልግ) ወቅት ኤሎሂም ያድርሰን። (ሔኖክ መደብር)

No comments:

Post a Comment