ከሐምሌ 1 ቀን 2006 ዓ.ም. ተነሥተን ማለት ነው፡፡
የበጀት ዓመቱን ልናጠናቅቅ 16 ቀኖች ብቻ ይቀሩናል፡፡ በመደበኛው አቈጣጠር ዓመቱ ሊያበቃስ ስንት ቀን ይቀረዋል?
ባሕረ ሐሳቡን የቀን መቁጠሪያውን ጠንቅቀው የሚያውቁቱ፣ በየአራት ዓመቱ ጳጉሜን 6 እንደምትሆን የሚገነዘቡቱ 83
ቀን እንደሚቀር ያውቁታል፡፡ በተንጠልጣይ፣ በጠረጴዛ ላይ እና በአጀንዳ ባዘጋጇቸው የ2007 ዓ.ም. ቀን
መቁጠርያቸው ላይ በግልጽ አስቀምጠውታል፡፡
አንዳንድ ተቋማት መንግሥታዊም ሆኑ መንግሥታዊ ያልሆኑ ዘንድሮ ሠግር ዓመት (Leap year) መሆኗን ያላስተዋሉቱ ‹‹ዓመታቸው›› የሚያበቃው ከ82 ቀን በኋላ ጳጉሜን 5 ቀን ነው፡፡
እንዴት ነው ነገሩ?
የዘንድሮው 2007 ዓ.ም. ካለፉት ሦስት ዓመታት (2004፣ 2005፣ 2006) ለየት ያለ ዓመት ነው፡፡
እንዳለፉት ዓመታት ዓመቱን የሚፈጽመው በ365ኛው ቀን አይደለም፡፡ አንድ ዓመት የሚባለው መሬት ፀሓይን ዞራ
የሚፈጅባት የ365 ¼ኛ ቀን በአራት ዓመት ሩቡ አንድ ሙሉ ቀን ስለሚሆን በ366ኛው ቀን ላይ ነው፡፡ ይህም ሆኖ
ይህንን አጋጣሚ ያላስተዋሉ ጥቂት አይደሉም፡፡
የኢትዮጵያ አዲስ ዓመት በመጣ ቁጥር ልዩ ልዩ ተቋማት ለዓመት ጉዟቸው እንዲረዳቸው በኢትዮጵያ ባሕረ ሐሳብ
(ካሌንደር) ላይ የተመሠረተ አጀንዳ፣ ተንጠልጣይና የጠረጴዛ መቁጠሪያዎች ያዘጋጃሉ፡፡ በዚሁ መሠረት አጀንዳ
ካዘጋጁት መካከል የኢትዮጵያ መንግሥት አውራ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት (ፓርላማ) ግንባር ቀደሙ ነው፡፡
እጅግ በሚያምር ጥራዝ በወርቃማ ቀለም ከምቾት ጋር የተላበሰው ‹‹የኢፌዴሪ የሕዝበ ተወካዮች ምክር ቤት ፳፻፯
House of peoples’ Representatives of The FDRE 2014/15›› አጀንዳ የዘንድሮውን
2007 ዓ.ም. ማብቂያ ጳጉሜን 5 ላይ አስቀምጦታል፡፡ ጳጉሜን 6 ፈጽሞ በአጀንዳው ውስጥ የለችም፡፡ ፓርላማው
ጳጉሜን 6ን የመርሳት አባዜ ያልተላቀቀው ዘንድሮ ብቻ አይደለም፡፡ ከአራት ዓመት በፊትም ባሳተመው አጀንዳ ከጳጉሜን
6 ጋር ሳይገናኝ አልፏል፡፡
እንዴት ነው ነገሩ?
ዘንድሮም ተደገመ!
የካሌንደር ቃፊር ፓርላማው የለውም እንዴ?
በ1999 ዓ.ም. ጳጉሜን 6 ቀን መንፈቀ ሌሊት ላይ ያልገባውን ሦስተኛውን ሺሕ ዓመት (ሚሌኒየም) ‹‹በተሰጠኝ
ሥልጣን መሠረት›› ገብቷል ተብሎ እንደታወጀው ሁሉ የሕግ አውጪውን ፓርላማ አጀንዳ ተከትለን በጳጉሜን 5 ሐሙስ
ማግስት የሚመጣውን ዓርብ (ጳጉሜን 6 ቀንን) የ2008 ዓ.ም. መስከረም 1 ቀን ይገባል ይባልልን ይሆን?
እንደ ፓርላማው ሁሉ ዓመቱን ጳጉሜን 5 ላይ የዘጋው ቃሊቲ ብረታ ብረት ፋብሪካ (በአጀንዳውም በጠረጴዛ
ካሌንደሩም) ሐሙስ ጳጉሜን 5 ዓመቱ አብቅቶ በማግስቱ ዓርብ መስከረም 1 ቀን 2008 ዓ.ም. አዲሱ ዓመት
እንደሚውል በግልጽ አስፍሯል፡፡
እንዴት ነው ነገሩ? የካሌንደር፣ የዘመን መቁጠሪያ፣ የባሕረ ሐሳብ ጉዳይ ቸል ተባለሳ?
ለነገሩ ፓርላማው ብቻ አይደለም ‹‹ሁሌም የሚተማመኑበት ባንክ›› እያለ የሚያስነግረው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
በገበታ ካሌንደሩ ጳጉሜን 6 አላመለከታትም፡፡ አላወቃትም፡፡ ዘንድሮ ብቻ አይደለም የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጳጉሜን
6ትን የመጣል አባዜ የተፈጠረበት፤ ከአራት ዓመት በፊት ባንኩ ያሳተመው የጠረጴዛ ቀን መቁጠርያ ዓመቱን በጳጉሜን 5
ነው ያጠረው፡፡ ጎርጎርዮሳዊውን ቀመር የሚከተለው ባንኩ የአገርኛው ቀመር ቃፊር የለውም እንዴ? በንዋይ
የሚተማመኑበት ባንክ ለካሌንደሩስ ምን ቅፅል ይሰጠው ይሆን?
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይልም በተመሳሳይ ዓመቱን ጳጉሜን 5 ላይ ከርችሞታል፡፡ ሸገር ሬዲዮም፣ ጅማ ዩኒቨርሲቲ እንዲሁ፡፡
እንዴት ነው ነገሩ?
ጳጉሜን 6 የረሱ አጀንዳዎችና ካሌንደሮች ቤት ይቁጠራቸው፡፡ የካሌንደር ጉዳይ በተለይ በቅርበት የሚመለከታቸው
ባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር፣ ቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለሥልጣን፣ ትምህርት ሚኒስቴርና የመሳሰሉት በየአራት ዓመቱ
እየተፈጠረ ያለውን መፋለስ እንዳይደገም ጥንቃቄ የሚያደርጉት መቼ ነው?
ቱሪስቶችን የሚያስመጡት አስጎብኚዎቹ ቱር ኦፕሬተሮች ካሌንደሩን በቅጡ ካልመዘገቡት መፋለስ እንደሚመጣ ልብ ይሏል፡፡
ከአራት ዓመት በፊት ጳጉሜን 6 የረሳ አንድ ቱር ኦፕሬተር የ2004 ዓ.ም. ደመራና መስቀል የሚውሉበትን
መስከረም 16 እና 17፣ በጎርጎርዮሳዊው (አውሮፓ) ቀመር ‹‹ሴፕቴምበር 27 እና 28 ይከበራሉ›› ብሎ ከመግለጽ
ይልቅ እንዳለፉት ሦስት ዓመታት ሴፕተምበር 26 እና 27 ብሎ ቡክ በማድረጉ ቱሪስቶቹ መስተጓጐላቸው ይነገራል፡፡
እንዴት ነው ነገሩ?
ለአገሪቱ የገጽታ ግንባታ ሁነኛ ስፍራ ያለው ቱሪዝም ከጊዜ ጋር ያለው ቁርኝነት ይበልጥ ዘልቆ የሚሰማቸው
ካሌንደር ሕይወታቸው ለሆነው የባሕር ማዶ ቱሪስቶች ነው፡፡ እነርሱን በአግባቡ ማስተናገድ አለመቻል ትልቅ መፋለስን
ይፈጥራልና ሃይ የሚል የለም እንዴ? እንዴት ነው ነገሩ?
ከአራት ዓመት በፊት የጳጉሜን 6 ሰለባ የነበሩት ቱሪስቶች ብቻ አልነበሩም፡፡ የ2004 ዓ.ም. የሰንደቅ ዓላማ ቀን ክብረ በዓል ጭምር እንጂ፡፡
2003 ዓ.ም. ቅዳሜ ጳጉሜን 5 ያበቃል የሚለውን የፓርላማውንና የራሱን አጀንዳ በመከተል ከአዲስ አበባ ከተማ
አስተዳደር ነሐሴ 14 ቀን (ኢዜአ እንደዘገበው) በወጣው መግለጫ፣ ‹‹መስከረም 9 ቀን 2004 ዓ.ም.
የሚከበረውን በዓል በልዩ ድምቀት ለማክበር›› ተብሎ ዝርዝሩ መቅረቡ በዓሉ ከሰኞ ወደ ማክሰኞ ተቀየረ ወይ አስብሎ
ነበር፡፡
እንደ 2003ቱ አጀንዳ ጳጉሜን 5 ቅዳሜ አብቅቶ የ2004 መስከረም 1 እሑድ ሆነ፡፡ መስከረም 2 ሰኞ ብሎ
በማስላት ሁለተኛውን ሰኞ መስከረም 9 ላይ አመለከተ፡፡ ይሁን እንጂ ጉዱ የታወቀው ቆይቶ ነው፡፡ ‹‹ኧረ ጳጉሜ 6
ነች፣ መስከረም 1ም ሰኞ ነው የሚለው ተሰምቶ ማስተካከያ የተደረገው በዓሉን ከአዋጅ ውጭ ወደ ሦስተኛ ሰኞ በመውሰድ
መከበሩ ነበር፡፡ ሰበብ የተደረገውም፣ ‹‹የቀኑ መተላለፍም በቂ ዝግጅት [ለ] ማድረግ›› በሚል ነበር፡፡
እንዴት ነው ነገሩ?
ጊዜን ቀመርን በአግባቡ መጠቀም መሠረታዊ ነገር መሆኑ አይሳትም፡፡ አራት ነገሮችን የያዘ አንድ ቀዋሚ ጥንታዊ
አገላለጽ አለ፡፡ ንግግር ለማድረግ ሐሳብን በጽሑፍ ለማስፈር ሰዋስው (ግራመር) የቋንቋ ሥርዓት አስፈላጊ ነው፡፡
ለአምልኮትም ይሁን ለክብረ በዓል ሙዚቃ ከነሥርዓቱ ያስፈልጋል፡፡
አገር ከነጓዙ ለመምራት ሕግና ቀኖና መሠረታዊው ነገር ነው፡፡
በዓላትና የዘመን መለወጫን በፀሐይም ሆነ በጨረቃ መንገድ ለማወቅ ካለንደር መሠረታዊ ነገር ነው፡፡
ከእነዚህ አራት ምሰሶዎች በኢትዮጵያችን ክፍተት ያለው የዘመን አቈጣጠር፣ ባሕረ ሐሳብ ላይ ነው፡፡ መንጋደዱ
ጳጉሜን 6ን የመርሳቱ ነገርን ለማረቅ አራተኛው ምሰሶ ላይ አገሪቱ ትኩረት የምትሰጠውስ መቼ ነው?
እንዴት ነው ነገሩ?
Wednesday, August 5, 2015
Saturday, July 11, 2015
በዓለ ሐዋርያት- (Apostle's Feast)
ዛሬ ሐምሌ 5 ቀን፣ በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ታላቅ በዓል ነው፡፡ በዓለ ሐዋርያት፡፡ ለሐምሌ ወር የመጀመሪያው እሑድ፣ ሰኔ 26 ቀን የገባው የክረምትም ሁለተኛ እሑድ ነው፡፡ ክርስቶስ በተነሣ በ50ኛው ቀን ከዋለው የጰንጠቆስጤ (ጰራቅሊጦስ) በዓል ማግስት የተያዘው ጾመ ሐዋርያት ያበቃበትና የጴጥሮስ ወጳውሎስ ሰማዕትነት መታሰቢያ ዕለትም ነው፡፡ ለዕለቱ የተሠራው ሥርዓተ አምልኳዊ ምንባብ እነሆ፡፡-
መዝሙረ ያሬድ- ‹‹አሠርገዎሙ ለሐዋርያት በሰማያት››-
በሰማያት ሐዋርያቱን ሸለማቸው/ አከበራቸው፡፡
መዝሙረ ዳዊት- ‹‹አልቦ ነገር ወአልቦ ነቢብ ዘኢተሰምዐ ቃሎሙ፤
ውስተ ኵሉ ምድር ወፅአ ነገሮሙ፤
(ምስባክ) ወእስከ አጽናፈ ዓለም በጽሐ ነቢቦሙ፡፡››
-ነገራቸው ያልተሰማበት ቦታ የለም፤ ድምጻቸው ወደ ምድር ሁሉ ወጣ፤
ቃላቸውም እስከ ምድር ዳርቻ ወጣ፡፡ (መዝ. 18፡4-5)
ከዝክረ ዕለቱ ጋር ተያይዞ የሚገኘው፣ እግዚእነ ኢየሱስ ክርስቶስንና ቅዱሳኑን ጴጥሮስና ጳውሎስን የሚያሳየው የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ሐበሻዊ ጥንታዊ ሥዕል ነው፡፡ ከብራና ላይ የተገኘው የ12ቱ ሐዋርያት ሥዕልም ይታያል፡፡
(ሔኖክ መደብር)
the first Sunday of Hamle/ Abib (Apostle's Feast)
The Martyrdom of Sts. Peter and Paul, the Apostles.
On this day (Hamle 5), the two great saints Peter and Paul,
were martyred. Peter was from Bethsaida, and he was a fisherman. The
Lord chose him on the second day of His baptism after He chose Andrew
his brother. He had fervent faith and strong zeal. When the Lord asked
His disciples: "Who do men say that I am?" So they answered, "Some say
John the Baptist, some Elijah, and others Jeremiah or one of the
prophets." ... Simon Peter answered and said, "You are the Christ, the
Son of the living God." (Mat. 16:13-20) After he received the grace of
the Holy Spirit, he went around in the world preaching of the crucified
Christ, and he converted many to the faith. God wrought great and
innumerable signs and wonders by his hands. He wrote two catholic
Epistles to the believers. When he came to the city of Rome, he found
there St. Paul the Apostle. Through their preaching, most of the people
of Rome believed, so Nero seized Peter and commanded to crucify him.
Peter asked them to crucify him head downwards, and he delivered up his
soul into the hand of the Lord.
As of St. Paul the Apostle, he was born in Tarsus two years before the
advent of the Savior. He was a Jew, of the tribe of Benjamin, a
Pharisee, the son of a Pharisee. He was well learned in the Law of the
Torah, and he was jealous for it. He persecuted the Christians.
When they stoned St. Stephen, Paul was guarding the clothes of those who were stoning him. He took from Caiaphas, the high priest, letters to the synagogues of Damascus, to bind the Christians and bring them to Jerusalem. As he journeyed, he came near Damascus, and suddenly a light shone around him from heaven. Then he fell to the ground, and heard a voice saying to him, "Saul, Saul, why are you persecuting Me?" And he said, "Who are You, Lord?" And the Lord said, "I am Jesus, whom you are persecuting. It is hard for you to kick against the goads." Then He ordered him to go to Ananias in Damascus, who baptized him, and he received his sight at once. He was filled by the grace of the Comforter, and he proclaimed boldly the Faith. He went around in the world preaching of the crucified Christ. He suffered much beatings, imprisonment, and was bound with fetters, some of which are mentioned in the book of the Acts of the Apostles and in his Epistles.
He went to Rome and proclaimed the Faith there and many believed by his hands. He wrote for them the Epistle to the Romans which was the first of his fourteen Epistles.
Finally, Nero seized him, tortured him severely and ordered his head cut off. While St. Paul was passing along with the executioner, he met a damsel who was a kinswoman of the Emperor Nero, and who had believed through him. She walked along with St. Paul, weeping, to where they carried out the sentence. He comforted her and asked her for her veil. He wrapped his head with the veil, and asked her to return back. The executioner cut off his head and left it wrapped in the veil of the young girl, and that was in the year 67 A.D. The young girl met the executioner on his way back to the Emperor, and asked him about Paul and he replied, "He is lying where I left him and his head is wrapped in your veil." She told him, "You are lying, for he and Peter had just passed by me, they were arrayed in the apparel of kings, and had crowns decorated with jewels on their heads, and they gave me my veil, and here it is." She showed it to the executioner, and to those who were with him. They marvelled, and believed on the Lord Christ.
God wrought by the hands of Peter and Paul many great signs and wonders, that they even carried the sick out into the streets ... that as Peter came by ... his shadow might fall on them ... and they were all healed. (Acts 5:15) The handkerchiefs or aprons were brought from Paul's body to the sick, and the diseases left them and the evil spirits went out of them. (Acts 19:12)
May their prayers be with us, and Glory be to God forever. Amen.
Ethiopic/ Coptic Synaxarium
When they stoned St. Stephen, Paul was guarding the clothes of those who were stoning him. He took from Caiaphas, the high priest, letters to the synagogues of Damascus, to bind the Christians and bring them to Jerusalem. As he journeyed, he came near Damascus, and suddenly a light shone around him from heaven. Then he fell to the ground, and heard a voice saying to him, "Saul, Saul, why are you persecuting Me?" And he said, "Who are You, Lord?" And the Lord said, "I am Jesus, whom you are persecuting. It is hard for you to kick against the goads." Then He ordered him to go to Ananias in Damascus, who baptized him, and he received his sight at once. He was filled by the grace of the Comforter, and he proclaimed boldly the Faith. He went around in the world preaching of the crucified Christ. He suffered much beatings, imprisonment, and was bound with fetters, some of which are mentioned in the book of the Acts of the Apostles and in his Epistles.
He went to Rome and proclaimed the Faith there and many believed by his hands. He wrote for them the Epistle to the Romans which was the first of his fourteen Epistles.
Finally, Nero seized him, tortured him severely and ordered his head cut off. While St. Paul was passing along with the executioner, he met a damsel who was a kinswoman of the Emperor Nero, and who had believed through him. She walked along with St. Paul, weeping, to where they carried out the sentence. He comforted her and asked her for her veil. He wrapped his head with the veil, and asked her to return back. The executioner cut off his head and left it wrapped in the veil of the young girl, and that was in the year 67 A.D. The young girl met the executioner on his way back to the Emperor, and asked him about Paul and he replied, "He is lying where I left him and his head is wrapped in your veil." She told him, "You are lying, for he and Peter had just passed by me, they were arrayed in the apparel of kings, and had crowns decorated with jewels on their heads, and they gave me my veil, and here it is." She showed it to the executioner, and to those who were with him. They marvelled, and believed on the Lord Christ.
God wrought by the hands of Peter and Paul many great signs and wonders, that they even carried the sick out into the streets ... that as Peter came by ... his shadow might fall on them ... and they were all healed. (Acts 5:15) The handkerchiefs or aprons were brought from Paul's body to the sick, and the diseases left them and the evil spirits went out of them. (Acts 19:12)
May their prayers be with us, and Glory be to God forever. Amen.
Ethiopic/ Coptic Synaxarium
Saturday, July 4, 2015
በዩኔስኮ የተመዘገበው ያልታወቀው ባለ79 ዓመቱ የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ሰነድ - ተጻፈ በሔኖክ ያሬድ -05 July 2015
‹‹… ከእግዚአብሔር መንግሥት በቀር የፍጡር
መንግሥት ሁሉ አንዱ ከአንዱ የማይበልጥ ሥራ የለውም፡፡ ነገር ግን በምድር ላይ ኃይለኛ የሆነው መንግሥት ምንም
በደል የሌለበትን የሌላውን መንግሥት ሕዝብ ለማጥፋት የሚገባው
መስሎት በተነሳበት ጊዜ ተጠቂው ወገን ለመንግሥታት ማኅበር የተበደለውን የሚያቀርብበት ሰዓት ነው፡፡ እግዚአብሔር ታሪክ ለምትሰጡት ፍርድ ለመንግሥት ማኅበርም ምስክር ሆነው ይመለከታሉ…››
ከ80 ፈሪ ዓመት፣ ማለትም ከ79 ዓመት በፊት ሰኔ 23 ቀን 1928 ዓ.ም. የመጨረሻው የኢትዮጵያ ንጉሠ
ነገሥት መንግሥት (1923 – 1967) ርእስ የነበሩት ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ የፋሺስት ኢጣሊያን ወረራ አስመልክቶ
በጄኔቭ የመንግሥታቱ ማኅበር (ሊግ ኦፍ ኔሽንስ) ሸንጎ ላይ ካደረጉት ንግግር የተወሰደ ኃይለ ቃል ነው፡፡
በዳግማዊ ምኒልክ ዘመን (1888 ዓ.ም.) ዓድዋ ላይ ድል የተመታው የኢጣሊያ ወራሪ ሠራዊት ከ40 ዓመት ቆይታ
በኋላ በፋሺስቱ ቤኔቶ ሙሶሎኒ አማካይነት ኢትዮጵያን መውረሩና በተለይ በዓለም የተከለከለው የመርዝ ጋዝ በመጠቀም
የኢትዮጵያን ሠራዊት በ1928 ዓ.ም. መፈታቱ ይታወሳል፡፡
እርመኛ አርበኞች የአገሪቱን ነፃነት ለማስከበር የሕዝቡን ልዕልና ለማስጠበቅ መራር ተጋድሎ ማድረጋቸውም
ባይዘነጋም የፋሺስት ወንጀለኞች በታኅሣሥ 1928 ዓ.ም. የኢትዮጵያን ሠራዊት የፈቱበት፣ በተምቤንና በሐሸንጌ
በመርዝ ጋዝ ያደረሱት እልቂት ይጠቀሳል፡፡
በስደት ወደ አውሮፓ የዘለቁት ንጉሠ ነገሥቱ አፄ ኃይለ ሥላሴ ከክብር ተከታዮቻቸው ጋር ሆነው ዲፕሎማሲያዊ
ተጋድሎ ማድረጋቸው በታሪክ ተመዝግቧል፡፡ አንዱና ቀዳሚዋ ኢትዮጵያ አባል ለሆነችበትና መቀመጫውን ስዊዘርላንድ ጄኔቭ
ላደረገው የመንግሥታቱ ማኅበር (ሊግ ኦፍ ኔሽንስ) የግፍ ወረራውን በመቃወም ለሥዩማኑ አቤት ማለት ነበር፡፡
በአንድ በኩል የኢጣሊያው አምባገነን ቤኒቶ ሙሶሎኒ ኢትዮጵያን በመጠቅለል በአፍሪካ የኢጣሊያ ግዛት መመሥረቱን
አገሪቱንም መያዙን ሲያውጅ፣ አዲስ አበባንም ፋሺስቶች ሚያዝያ 27 ቀን 1928 ዓ.ም. ከመያዛቸው አስቀድሞ
የተሰደዱት ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ የሙሶሎኒን መግለጫ በመቃወም ለመንግሥታቱ ማኅበር አቤት ቢሉም ድጋፍ አላገኙም፡፡
አብዛኛዎቹ የሊግ ኦፍ ኔሽንስ አባል አገሮች ለኢጣሊያ ወረራ እውቅና ሰጥተው ነበርና፡፡
ይሁን እንጂ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ በአገር ባህል ልብስ ተውበው፣ ሰኔ 23 ቀን 1928 ዓ.ም. በጄኔቭ የምክር
ቤቱ አዳራሽ በመገኘት ትንቢታዊና አስደናቂ ንግግር ያደረጉት በአማርኛ ቋንቋ ነበር፡፡ እንዲህም ብለው ነበር፡፡
‹‹ዛሬ የመንግሥታት ማኅበር ዋና ጉባዔ በፊቱ ያለው ጉዳይ ኢጣልያ በአጥቂነት የሠራችውን ለመጨረስ ብቻ
አይደለም፡፡ በሙሉ የዓለምን መንግሥታት የሚነካ ጉዳይ መሆኑን አረጋግጬ አስታውቃለሁ፡፡ ይህም ጉዳይ ለዓለም ጸጥታ
እንዲሆን መንግሥታት ለመረዳዳት የሚገባቸው ሴኩሪቲ ኰሌክቲፍ የተባለው የመንግሥታት ማኅበር ሕይወት፤ የዓለም
መንግሥታት ለተዋዋሉት ውል መስጠት የሚገባቸው እምነት፤ ትንንሾቹም መንግሥታት አገራቸውና ነጻነታቸው እንዳይነካ
የተቀበሉት ቃል ኪዳን የሚከበርበትና ዋጋው የሚገመትበት፤ የመንግሥቶች ትክክልነት የተመሠረተበት መሠረት፤ ይህን
ለማድረግ ወይም ትንንሾች መንግሥቶች የኃይለኞች መንግሥቶች ተገዢ ለመሆን መቀበል ይገባቸው እንደሆነ ለመፍረድ
ነው፡፡
‹‹በአጭር ቃል የተነካውና የተበደለው የዓለም ሕዝብ የሚገባ አንዋወር ነው እንጂ ኢትዮጵያ ብቻ አይደለችም፡፡
በአንድ ውል ላይ የተፈረሙ ፊርማዎች ዋጋቸውን የሚያገኙት የፈረሙት መንግሥቶች አንዱ በሌላው ላይ የግል ጥቅሙን
በቀጥታና በፍጥነት ለማግኘት ለመፈጸምም እንዲችል እንዲረዱት ሲሆኑ ነውን?
‹‹በረቂቅ መንገድ መበላለጥ ዋናውን ነገር ሊለውጠው ወይም የክርክሩን መንገድ በሌላ በኩል ሊመራው አይገባም፡፡ ይህንንም ማመልከቻ ለመንግሥታት ማኅበር ዋና ጉባዔ የማቀርበው በእውነተኛነትና ከልቤ ነው፡፡
‹‹ሕዝቤ ዘሩ ሊጠፋ በደረሰበት የመንግሥታት ማኅበርም እርዳታ ከጥፋት ለማዳን በሚችልበት ጊዜ ማናቸውንም
ሳላስቀርና፤ የመንግሥታት ማኅበር ማኅበርተኞች መንግሥቶች ሁሉ ያላቸው የትክክለኛነት ደንባቸው እንደሚያስገድደኝ፤
ሳላቆይና ሳላስቀር በተዘዋዋሪ ቃል ሳይሆን እውነቱን አውጥቼ እንድናገር ሊፈቀድልኝ የተገባ ነው፡፡
‹‹ከእግዚአብሔር መንግሥት በቀር የፍጡር መንግሥት ሁሉ አንዱ ከአንዱ የማይበልጥ ሥራ የለውም፡፡ ነገር ግን
በምድር ላይ ኃይለኛ የሆነው መንግሥት ምንም በደል የሌለበትን የሌላውን መንግሥት ሕዝብ ለማጥፋት የሚገባው መስሎት
በተነሳሣበት ጊዜ፤ ተጠቂው ወገን ለመንግሥታት ማኅበር የተበደለውን የሚያቀርብበት ሰዓት ነው፡፡ እግዚአብሔርና ታሪክ
ለምትሰጡት ፍርድ ለመንግሥታት ማኅበርም ምስክር ሆነው ይመለከታሉ፡፡››
በቁም ጽሕፈት የተጻፈው የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ንግግር (ዲስኩር) ከፈረንሣይኛ ትርጉሙ ጋራ ግራና ቀኝ ሆነው
በሊጉ ቤተ መዛግብት ተጠብቆ ኖሮ በ1938 ዓ.ም. በጄኔቭ ወደ ሚገኘው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጽሕፈት ቤት
ተዘዋውሮ ተቀምጧል፡፡ የመንግሥታቱ ድርጅት የትምህርት የሳይንስና የባህል ድርጅት (ዩኔስኮ) ከአምስት ዓመት በፊት
በ2002 ዓ.ም. የዓለም ቅርስ አድርጎም መዝግቦታል፡፡
ወርልድ ዲጂታል ላይብረሪ (World Digital Library) በድረ ገጹ ያሰፈረውም፣ ‹‹The text is
preserved in the archives of the League, which were transferred to the
United Nations in 1946 and are housed at the UN office in Geneva. They
were inscribed on the UNESCO Memory of the World register in 2010›› ይህንኑ
ያንፀባርቃል፡፡
ኢትዮጵያ የንግግሩ ሰነድ መመዝገቡን ታውቃለች?
ኢትዮጵያ የዓይነተ ብዙ ቅርስ ባለቤት መሆኗ ይታወቃል፡፡ በጉያዋ የያዘቻቸውን ስፍር ቁጥር የሌላቸውን ቅርሶች
ትተን በዩኔስኮ የተመዘገቡት ብንቆጥር ዘጠኝ ተፈጥሯዊና ሰው ሠራሽ ቅርሶች፣ አንድ የማይዳሰስ ቅርስ (የመስቀል
በዓል) የብዝኃ ሕይወት አራት ቦታዎችና የሥነ ጽሑፍና የመዛግብት ቅርሶች መኖራቸው ከሚመለከታቸው አካላት በየጊዜው
ሲነገረን ቆይቷል፡፡
በሥነ ጽሑፍ ዘርፍ የሚመዘገቡት ቅርሶች የሚመለከተው ብሔራዊ ቤተ መዛግብትና ቤተ መጻሕፍት ኤጀንሲ 12
የኢትዮጵያ የጽሑፍ ቅርሶች መመዝገባቸው ከልዩ ልዩ ሰነዶች ባሻገር በቅጥር ግቢው የሰቀለው ሰሌዳ (ቢልቦርድ)
ያመለክታል፡፡
ከአገሮች ሌላ ዓለም አቀፍ ድርጅቶችም መዝገቦቻቸውንና ልዩ ልዩ ሰነዶቻቸውንም አስመዝግበዋል፡፡ ከእነዚህም
መካከል የቀድሞው የመንግሥታቱ ማኅበር ሊግ ኦፍ ኔሽንስ ይገኝበታል፡፡ ጄኔቭ በሚገኘው ጽሕፈት ቤቱ እ.ኤ.አ.
ከ1919-1946 (ከ1911 ዓ.ም. – 1938 ዓ.ም.) የተሰባሰቡ መዛግብት በዩኔስኮ ሲመዘገቡ አንዱ የተመዘገበው
የ1928 ዓ.ም. የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ንግግርን የያዘው ሰነድ ነው፡፡ ይህ ባለ 20 ገጽ በአማርኛና በፈረንሳይኛ
የተጻፈው የንጉሠ ነገሥቱ ንግግር ብሔራዊ ቤተ መዛግብት ቤተ መጻሕፍት ኤጀንሲ እንደ 13ኛ ቅርስ ያልያዘው
ምዝገባው በርሱ በኩል ባለመከናወኑ ነው ወይስ በሌላ ምክንያት?
Friday, July 3, 2015
‹‹የዝናብ ኮቴ ተሰማ››
‹‹የዝናብ
ኮቴ ተሰማ››
(ደምፀ
እገሪሁ ለዝናም)
በኢትዮጵያ
ባሕረ ሐሳብ መሠረት ዛሬ ሰኔ 26 ቀን 2007 ዓ.ም. የክረምት ወቅት ገብቷል፡፡ ትናንት ሰኔ 25 ቀን የሸኘነው የፀደይ (በልግ)
ወቅት ነበር፡፡ ወቅቱ ዝናብ የዝናብ ወራት ነው፡፡ በፀደይና በመፀው መካከል ያለ ክፍለ ዓመት ሲሆን እስከ መስከረም 25 ድረስ
ይቈያል፡፡
‹‹ሰማዩን
በደመናት ይሸፍናል፤ ለምድርም ዝናብን (ክረምትን) ያዘጋጃል፤ሣር በተራሮች ላይ ያበቅላል፤ ለምለሙን ለሰው ልጆች ጥቅም፡፡››
‹‹ዘይገለብቦ
ለሰማይ በደመና፤ወያስተዴሉ ክረምተ ለምድር፤ ዘያበቍል ሣዕረ ውስተ አድባር፡፡›› (መዝሙር 146፡8)፡፡
በኢዮብ
እንደተጻፈውም (37፡5-6)፣ ‹‹እግዚአብሔር በድምፁ ድንቅኛ ያንጐደጒዳል፤እኛም የማናስተውለውን ታላቅ ነገር ያደርጋል፡፡ በረዶውንና
ውሽንፍሩን ብርቱንም ዝናብ በምድር ላይ ውደቁ ይላል፡፡››
(ማመሳከሪያ፡- መክ 3፤11፡፡‹‹ነገሩን ሁሉ በጊዜው ውብ አድርጎ ሠራው››፤ኢዮብ
36፡ 29፡፡ ‹‹የደመናትን ንብርብር፣ ከድንኳኑንም የሚሰማውን ነጐድጓድ ማን ሊያስተውል ይችላል?››፤ መዝ 147፡6፡፡ ‹‹በረዶውን
እንደ ፍርፋሪ ያወርዳል፤ በበረዶውስ ፊት ማን ይቆማል፡?›› አሞጽ 9፡6፡፡ አዳራሹን በሰማይ የሠራ፣ ጠፈሩንም በምድር ላይ የመሠረተ፣
የባሕርንም ውሃ ጠርቶ በምድረ ፊት ላይ የሚያፈስሰው እርሱ ነው፤ ስሙም እግዚአብሔር ነው፡፡)
ልበ
እግዚአብሔር ዳዊት እንዳለውም (73፡16-17)፣ ‹‹አንተ ፀሐይንና ጨረቃን አዘጋጀህ፤ አንተ የምድር ዳርቻን ሁሉ ሠራህ፤ በጋንም
ክረምትንም አንተ አደረግህ፡፡››
በክረምት
ውስጥ የምንቈየው ለ96 ቀኖች ነው፡፡ ዘንድሮ ጳጉሜን ስድስት በመሆኗ የአንድ ቀን ጭማሪ አለ፡፡ ክፍለ ዓመቱ ክረምት እስከ መስከረም
25፣ 2008 ዓ.ም. በሚኖረው ቆይታ ዘጠኝ ንኡሳን ክፍሎችን ያስተናግዳል፡፡ ለአሁን ግን እስከ ዓመቱ (2007) መካተቻ ጳጉሜን
6 ድረስ ያሉትን እንዘረዝራለን፡፡
(ሀ)
ከሰኔ26- ሐምሌ18 -‹‹ዘር፣ ደመና››
(ሁ)
ከሐምሌ19- ነሐሴ9 -‹‹መብረቅ፣ ነጐድጓድ፣ ባሕር፣ አፍላግ (ወንዞች)፣ ጠል››
(ሂ)
ከነሐሴ10- 27 - ‹‹ዕጒለ ቋዓት (የቁራ ጫጩት)፣ ደስያት (ደሴቶች)፣ዐይነ ኵሉ (የሁሉም ዓይን)››
(ሃ)
ከነሐሴ 28- ጳጉሜን 5 ወይም 6- ‹‹ጎህ (ወጋገን)፣ ነግህ (ንጋት)፣ ጽባሕ (ጠዋት)፣ ብርሃን፣ መዓልት (ቀን)፣ ልደት››
ፀደዩን
እንዳስፈጸመን ክረምቱንም በሰላም አስፈጽሞ ለመፀዉ ያብቃን፡፡ ደኅና ያክርመን፡፡
ሰላም
ወሰናይ፡፡፡፡
ምንጭ፡-
በአራቱ ወቅቶች ላይ የተመሠረተው የአለቃ ያሬድ ፈንታ ወልደ ዮሐንስ ‹‹መጽሐፈ ግጻዌ ሐዲስ ዘተሰናአወ በአርባዕቱ ክፍላተ አዝማን››
(1997)
የአለቃ
ኪዳነ ወልድ ክፍሌ ‹‹መጽሐፈ ሰዋስው ወግስ ወመዝገበ ቃላት ሐዲስ›› (1948)
-
ሔኖክ መደብር
Thursday, July 2, 2015
Speech by the His Majesty Haile Selassie I, Emperor of Ethiopia, at the Assembly of the League of Nations, at the Session of June–July 1936
Speech by the His Majesty Haile Selassie I, Emperor of Ethiopia, at the Assembly of the League of Nations, at the Session of June–July 1936
Description
In the early 1930s, Italian dictator Benito
Mussolini was determined to expand Italy’s African empire by annexing
Ethiopia. In December 1934, a clash, provoked by the Italians, occurred
between Italian and Ethiopian armed forces at Walwal on the Ethiopian
side of the frontier with Italian Somaliland. Mussolini declared the
incident “an act of self-defense” and thus not subject to arbitration
under international agreements. Italy demanded compensation and formal
recognition of the area as Italian. When Emperor Haile Selassie refused
to yield to these demands, Italy began mobilizing its forces. As a
member of the League of Nations, Ethiopia brought the case before the
Council, but Mussolini ignored all League proposals to resolve the
crisis. On October 3, 1935, Italian forces invaded Ethiopia from Eritrea
and Italian Somaliland. The capital of Addis Ababa fell in May 1936.
Emperor Haile Selassie, who was in Geneva at the time, went to the
Assembly and asked for help, but to no avail; the League refused to act
and most member countries recognized the Italian conquest. Presented
here is the text of the emperor’s impassioned speech to the Assembly,
which he delivered on June 30, 1936. He spoke in Amharic, the text of
which is on the left side of the pages. The French translation is on the
right. The text is preserved in the archives of the League, which were
transferred to the United Nations in 1946 and are housed at the UN
office in Geneva. They were inscribed on the UNESCO Memory of the World
register in 2010.
Saturday, June 13, 2015
Saturday, June 6, 2015
Friday, May 22, 2015
Saturday, April 4, 2015
ጥንተ ስቅለት- መጋቢት 27፣ 34 ዓ.ም.
ጥንተ ስቅለት- መጋቢት 27፣ 34 ዓ.ም.
የዛሬ አንድ ሺሕ ዘጠኝ መቶ ሰባ ሦስት ዓመት በዕለተ
ዓርብ መጋቢት 27 ቀን 34 ዓመተ ምሕረት (5534 ዓመተ ዓለም) የክብር ባለቤት ጌታችን
መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስለ ዓለም ድኅነት በሥጋ የተሰቀለበት ዕለት ነው፡፡ በመጽሐፍ ቅዱስ እንደተጻፈው፡
‹‹ከስድስት ሰዓት ጀምሮም እስከ ዘጠኝ ሰዓት ዓለም ሁሉ ጨለማ ሆነ›› (ማቴዎስ 27፡45) ፈጣሪዋ በዕንጨት መስቀል ላይ ተሰቅሎ
ባየችው ጊዜ ፀሐይ ጨለመች፡፡ እርሱም ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም የነሣትን
ለባዊት ነባቢት የሆነች ነፍሱን ከሥጋው ለያት፡፡ ሐዋርያ ጴጥሮስ በሥጋ ምውት
ሲሆን በመለኮት ሕያው ነው እንዳለ፤ ነፍሱ ከመለኮት ሳትለይ ከሥጋ ተለየች፤ በዚያ ጊዜ ሥጋ ከመለኮት ሳይለይ በዕንጨት መስቀል ላይ ተሰቅሎ ነበር፡፡ እንዲሁም ነፍስ
ከመለኮት ጋር አንድ ሁና እሥረኞች ነፍሳትን ትፈታቸው ዘንድ ወደ ሲኦል ወረደች፡፡ (1 ጴጥሮስ 3፡18-19)
እርሱ ከሰማያት በላይ ከፍ ከፍ ያለ ልዑለ ባሕርይ ከአብ ከመንፈስ ቅዱስ ጋራ በጌትነቱ ዙፋን ተቀምጦ ያለ፣ ለእርሱም ምስጋና የክብር ክብር
ገንዘቡ የሆነ ራሡን ሰውቶ ያዳነን የመንግሥቱን ደጆች በፈሳሽ ደሙ የከፈተልን ለእርሱ ስግደት አምልኮት ይገባዋል፡፡
ለዘለዓለሙ የመስቀሉም በረከት በላያችን ይደር፤ አሜን፡፡
(የመጋቢት 27 ቀን ስንክሳር )
-
ሔኖክ መደብር
Subscribe to:
Posts (Atom)