ፀሐይዋ እየጠለቀች ያለው ‹‹በስሜን ተራራ›› ነው? ወይስ ‹‹በሰሜን ተራራ?›› ብዙ ጊዜ በጽሑፍም ሆነ በንግግር
‹‹ሰሜን ተራራ ብሔራዊ ፓርክ›› እየተባለ የሚጠቀሰው ስህተት ነው፡፡ የኅብረተሰብአዊት ኢትዮጵያ ጊዜያዊ ወታደራዊ
መንግሥት (ደርግ) ከ40 ዓመት በፊት ክፍለ ሀገሩን ጎንደር (በኢሕዲሪ ዘመን ሰሜን ጎንደር እና ደቡብ ጎንደር
መባሉን ልብ ይሏል) ብሎ ከመሰየሙ በፊት፣ በኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት መንግሥት በጌምድርና ስሜን ጠቅላይ ግዛት ይባል
ነበር፡፡ ፓርኩም ስሜን ይባል ነበር፡፡
ደጃዝማች ካሳ ኃይሉ አፄ ቴዎድሮስ ተብለው ከመንገሣቸው በፊት የመጨረሻውን መስፍን ራስ ውቤን ለማስገበር ከመሄዳቸው በፊት ተከታዮቻቸው፣ ‹‹መንገሦ አልቀረም ስምዎ ማን ይባላል?›› ሲሏቸው የሰጡት ምላሽ ‹‹ስሜን ስሜን እነግርሃለሁ ነበር፡፡›› ሀገሪቷ የስም ቃፊር የላትም እንዴ? እንዴት ነው ነገሩ? ‹‹ምእት ዓመት›› (ሲተረጐም መቶ ዓመት) የሚባለውን በዘፈቀደ ‹‹ምዕተ ዓመት›› (ሲተረጐም የዓመት መቶ) እያሉ ሚሌኒየም ለሚለውና ሺሕ ዓመት የሚል ፍች ላለው ማደባለቅና መደንጐር መቼ ያበቃ ይሆን? ለነገሩ ያለቋንቋ ፖሊሲ እየተጓዝን አይደል! የኔታ እንዳሉት ‹‹እስከ ማዕዜኑ ተሐነክሱ?›› (እስከ መቼ ታነክሳላችሁ?) በመናገሻ ከተማችን ዛሬ ኅዳር 12 ቀን በፀሐይ፣ ሌሊቱ 25 በጨረቃ ኅዳር 29/ 2007 ዓ.ም. ጻፍነው፡፡
‹‹ሔኖክ መደብር››

No comments:
Post a Comment