በ 27 03 2004 ዓ.ም. ሪፓርተር ጋዜጣ ላይ የወጣ
ዛሬ 190ኛ ዓመታቸው በዚያው ይዘከራልየአሥራ ዘጠነኛው ምእት ዓመት ኢትዮጵያዊ ሊቅና ቀልደኛው አለቃ ገብረ ሐና ታሪክ የሚገልጽ መጽሐፍ በአውስትራሊያ ታተመ፡፡
‹‹ሊቁ አለቃ ገብረ ሐና ከ፲፰፻፲፬-፲፰፻፺፰ ዓ.ም.›› የሚል ርእስ ያለውን መጽሐፍ ያዘጋጁት አቶ መሰለ ለማ ሀብተ ወልድ ናቸው፡፡ ደራሲው ከአውስትራሊያ ኲዊንስ ላንድ ብርስመን ከተማ ለሪፖርተር በቴሌፎን እንደተናገሩት፣ መጽሐፉ የአለቃ ገብረ ሐናን ሙሉ ታሪክ፣ 80 የአነጋገር ለዛና ቀልዶቻቸውን አካትቶ የቀረበበት ነው፡፡
ባለፉት ስምንት ዓመታት በእንግሊዝና በፈረንሣይ በሚገኙ ታላላቅ አብያተ መጻሕፍትን ጨምሮ በሌሎችም ተቋማት በአለቃ ገብረ ሐና ዙርያ ጥናት ማድረጋቸውንም ደራሲው ገልጸዋል፡፡
ባለፉት ስምንት ዓመታት በእንግሊዝና በፈረንሣይ በሚገኙ ታላላቅ አብያተ መጻሕፍትን ጨምሮ በሌሎችም ተቋማት በአለቃ ገብረ ሐና ዙርያ ጥናት ማድረጋቸውንም ደራሲው ገልጸዋል፡፡
በአቶ መሰለ አገላለጽ፣ የአለቃ ገብረ ሐና የአነጋገር ለዛዎችና ቀልዶችን የሚያነብ ከስምንት መቶ ዓመት ወዲህ የነበሩትን ዝነኛ ብልሆችና ፈልሳሚዎች የ13ኛውን ምእት ዓመት ፋርሳዊ ሙላ ነስረዲን፣ የ16ኛውን ፈረንሣዊ ፍራንሷ ራቤሌን እና የ17ኛውን ምእት ዓመት ጃፓናዊ መቱሶ ባሾ ያስታውሳል፡፡
በኢትዮጵያ ሙዚቃ፣ ሥነ ጽሑፍ፣ ቋንቋና ታሪክ ሁነኛ ስፍራ የነበራቸው አለቃ ገብረ ሐና፣ በኅብረተሰቡ ከሚታዩበት ቀልደኝነታቸው የተነሣ ‹‹በምናብ የተፈጠሩ፣ እንደ ስንዝሮ የተፈጠሩ ናቸው›› የሚሉ ቢኖሩም፣ ከአፄ ቴዎድሮስ እስከ አፄ ምኒልክ ድረስ የኖሩ በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ምሉዕ ትምህርት የነበራቸው፣ ከፍትሐ ነገሥት ሊቅነታቸው ሌላ በያሬዳዊ ዝማሬ ውስጥ ‹‹የተክሌ አቋቋም›› ተብሎ የሚጠራውን ስልት በልጃቸው ስም የፈጠሩ መሆናቸው ይታወቃል፡፡
በደብረ ታቦር ናባጋ ጊዮርጊስ በኅዳር 1814 ዓ.ም. የተወለዱት አለቃ ገብረሐና በአክሱም ጽዮን፣ በትግራይ ውስጥ በሚገኙ ገዳማት በጨለቆት ሥላሴ፣ በአዲስ አበባ እንጦጦ ራጉኤል፣ በጎንደርና ጎጃም አገልግሎት የሰጡ ናቸው፡፡
አለቃ ገብረ ሐና የተወለዱበትን 190ኛ ዓመት ምክንያት በማድረግም በአውስትራሊያ በሚገኘው የኢትዮጵያ ማኅበረሰብ ራዲዮ አማካይነት ስለ አለቃ ሕይወትና ሥራ አዲስ ስለታተመው መጽሐፍም አስመልክቶ ልደታቸው በልዩ ዝግጅት እንደሚዘከር አቶ መሰለ ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡
‹‹ሊቁ አለቃ ገብረ ሐና›› የተሰኘውን መጽሐፍ ያሳተመው ኣይ ዩኒቨርስ የተሰኘ አሳታሚ መሆኑን፣ ከሕትመት ሌላ በድረ ገጽ በሽያጭ እንደሚሰራጭ አዘጋጁ ገልጸዋል፡፡
******************************************************************
አለቃ ገብረ ሐና
ግብረ ሕያው
የትላት የነገው
አለቃ ገብረሐና
ሊቁ ባተሌው፡፡
ተረት ሆኖ ልሳንህ
እንቆቅልሽ መስሎ ገድልህ
ተዛምደህ ከስንዝሮ
ሕያው ካልሆነ ተፈጥሮ
ግና! ለካስ ስጋ ነበርክ እንደኛው
ያውም ሻል-ያልክ ሁነኛው፡፡
ግብረ ሕያው
የትላት የነገው
አለቃ ገብረሐና
ሊቁ ባተሌው፡፡
ኦ! ውቢት ናባጋጊዮርጊስ የፎገራ -የጎንደር
አፈራሽ ሊቅ ስመጥር - ስመ ሕብር
በ፲፰፻፲፬ - በኅዳር
ዝናው የገነነ ከአድማስ - አድማስ
- እንደ ሙላ ንስረዲን
- እንደ ማቱሶ ባሾ
- እንደ ፍራንኮ ራቤሊስ፡፡
ግብረ ሕያው
የትላት የነገው
አለቃ ገብረሐና
ሊቁ ባተሌው፡፡
ታላቅ ጠቢብ ጨዋታ አዋቂ
አሳቂ፣ አመራማሪ፣ ሀቅን አሳዋቂ
አንጋፋ ፈላስፋ ለዛ አቋቋም -ዝማሜ
የላቀ፣ የበቃ በመጻሕፍት ትርጓሜ
- በለዛ ሙግት ቅኔ
ማን! እንደ አለቃ ገብረ ሐና
ማንስ ታሰበና ማንስ ሆነና፡፡
መሰለ ለማ ሀብተወልድ
ግብረ ሕያው
የትላት የነገው
አለቃ ገብረሐና
ሊቁ ባተሌው፡፡
ተረት ሆኖ ልሳንህ
እንቆቅልሽ መስሎ ገድልህ
ተዛምደህ ከስንዝሮ
ሕያው ካልሆነ ተፈጥሮ
ግና! ለካስ ስጋ ነበርክ እንደኛው
ያውም ሻል-ያልክ ሁነኛው፡፡
ግብረ ሕያው
የትላት የነገው
አለቃ ገብረሐና
ሊቁ ባተሌው፡፡
ኦ! ውቢት ናባጋጊዮርጊስ የፎገራ -የጎንደር
አፈራሽ ሊቅ ስመጥር - ስመ ሕብር
በ፲፰፻፲፬ - በኅዳር
ዝናው የገነነ ከአድማስ - አድማስ
- እንደ ሙላ ንስረዲን
- እንደ ማቱሶ ባሾ
- እንደ ፍራንኮ ራቤሊስ፡፡
ግብረ ሕያው
የትላት የነገው
አለቃ ገብረሐና
ሊቁ ባተሌው፡፡
ታላቅ ጠቢብ ጨዋታ አዋቂ
አሳቂ፣ አመራማሪ፣ ሀቅን አሳዋቂ
አንጋፋ ፈላስፋ ለዛ አቋቋም -ዝማሜ
የላቀ፣ የበቃ በመጻሕፍት ትርጓሜ
- በለዛ ሙግት ቅኔ
ማን! እንደ አለቃ ገብረ ሐና
ማንስ ታሰበና ማንስ ሆነና፡፡
መሰለ ለማ ሀብተወልድ
No comments:
Post a Comment